TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የተወሰኑ ሰዎች በፈጠራ ወሬ አገር ሲያተራምሱ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም!" - ኡስታዝ አህመዲን ጀበል (የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ)
.
.
የተወሰኑ ግለሰቦች የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በፈጠራ ወሬ አገር ሲያተራምሱና ግጭት ሲያቀጣጥሉ እየታየ ዝም ሊባል እንደማይገባ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ገለፀ፡፡

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ (EPA)
እንደገለፀው፤ ከ100 እና 200 የማይበልጡ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ችግር ሲፈጥሩ ዝም ከተባለ ነገ ከባድ ችግር ይፈጠራል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች እውነትነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ዜና አድርገው በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ የት ሆኖ እንደጻፉትና እንደለጠፉት (ፖስት እንዳደረጉት) በቀላሉ መለየት የሚቻልበት ቴክኖሎጂ እያለ ብሄርን፣ ሀይማኖትን፣ ተቋማትንና ግለሰብን ስም ሲያጠፉና ሲሰድቡ ዝም ብሎ መመልከት ተገቢ አይደለም፡፡ አጥፊውን በህግ ተጠያቂ እንዲሆን በማድረግ ሌላውን ማህበረሰብ ማስተማር ያስፈልጋል ብሏል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በሀዋሳ 600 ሚለዮን ብር በሆነ ወጪ ዘመናዊ ሞል ሊገነባ ነው!

በሀዋሳ ከተማ 600 ሚለዮን ብር በሆነ ወጪ መዝናኛና ሌሎችንም አገልግሎትችን በአንድ ማዕከል ያካተተ ዘመናዊ ሞል ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀመረ። ግንባታው የሚካሄደው በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ አትዮጵያዊንና ትውልደ አትዮጵውያን  “ውዘርን ጌት ኢንቨስትመንት ” በሚል ስያሜ በመሰረቱት  አክሲዮን ማህበር ሲሆን የግንባታው ስራም በይፋ ተጀምሯል። በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው ግንባታው  በሁለት ምዕራፎች ሆኖ በሶስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ነው የታቀደው።

(ENA)

@tikvahethiopiabOt @tikvahethiopia
ተክለ ብርሃን አምባዬ በ73 ሚሊዮን ብር ግብር ስወራ ተከሰሰ!

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽንን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ ተቋራጮችን በግብር ስወራ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በስምንተኛ እና ዐስረኛ ወንጀል ችሎቶች ክስ መሰረተ።

በኢትዮጵያ ካሉ የደረጃ አንድ ተቋራጮች መካከል እንዲሁም ከፍተኛ አቅም ካላቸው መካከል የሆነው ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን፣ ከ 2005 እስከ 2008 ባለው ጊዜ መክፈል የነበረበት እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች የተገኘ 70.3 ሚሊዮን ብር የትርፍ ግብር ባለመክፈሉ ክሱ ተመሥርቷል።

የንግድ ግብሩ ግዢ ባልተፈፀመባቸው ሐሰተኛ ደረሰኞች በመጠቀም የተሰወረ እንደሆነ እና ደረሰኞቹንም የቆረጡት ድርጅቶች በአካል የሌሉ መሆናቸውን ጠቅሶ ነው ዐቃቤ ሕግ ክሱን የመሠረተው። ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ከ 25 ሚሊዮን እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገቢን ድርጅቱ ሰውሯልም ሲል ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሰምቷል።

በተጨማሪም ከተለያዩ አገልግሎቶች የተሰበሰበ ሦስት ሚሊዮን ብር የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ በተመሳሳይ ከ 2005 እስከ 2008 ባለው ዓመት ለመንግሥት ሳይከፍሉ ቀርተዋል ሲልም ነው ዐቃቤ ሕግ ክሱን በስምንተኛ የጉምሩክ ችሎት የመሠረተው።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-02

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው!

በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ ኤችአይቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ለቢቢሲ ገለፀ።

ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራና ቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በኤችአይቪ ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቫይሱ በወረርሽኝ ደረጃ የማይገኝባቸው የሶማሌ፣ የኦሮሚያና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሕግ መሰረት ይላሉ አቶ ዳንኤል፤ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከአንድ በመቶ በላይ በበሽታው ከተያዘ እንደ ወረርሽኝ እንደሚቆጠር በመግለጽ እነዚህ ክልሎች ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን ይላሉ አቶ ዳንኤል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው የስርጭት መጠን ሲታይ ወረርሽኝ ላይ ነው ማለት እንደማይቻል አስረድተዋል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በየማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እየተዘዎወረ የሚገኘው መረጃ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው!" - ADP

በአሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች መሪነት እየተካሄዱ ባሉ የውይይት መድረኮች ላይ በአዴፓ ም/ሊቀመንበር አቶ ዩሃንስ ቧያለው ተገልጿል በሚል በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እየተዘዎወረ የሚገኘው መረጃ ፈፅሞ የተሳሳተ እና ሆን ተብሎ እና ተቀነባብሮ የውይይት መድረኮቹን አላማና ግብ ለማዛባት ታስቦ እየተሰራጨ ያለ መረጃ እንደሆነ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ADP) ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ካመጠቀች በዓመት ለኪራይ ታወጣው ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪን ያስቀርላታል!

https://Twitter.com/Etrss_ethiopiahttps:
//fb.me/Etrssethiopia
https://publielectoral.lat/ETRSS_ethiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግርን_እንግታ

አሳሳቢ የጥላቻ ገለጻዎች በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት!

(Center for Advancement of Rights and Democracy-CARD)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላይታ ክልልነት ጥያቄ...

ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ክልል የመሆን ጥያቄ ካቀረበው የወላይታ ዞን ባለሥልጣናት እና የማህበረሰቡ ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በውይይቱ የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቢ፤ የሰላም ምኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የሐይማኖት መሪዎች ጭምር ተገኝተው ነበር።

ለውይይቱ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር «ፍሬያማ ውይይት አድርገናል» እንደነበር አይዘነጋም። በውይይቱ የተሳተፈው እና የላጋ የተባለው የወላይታ ወጣቶች ማኅበራዊ ንቅናቄ መሥራቾች አንዱ የሆነ አቶ አሸናፊ ከበደ «ወላይታ ራሱን ችሎ ክልል ከመሆን ሌሎች አማራጮች ይኖራሉ አይኖሩም? የሚሉ ጉዳዮች እና ሌሎች ተያያዥ አማራጭ የሆኑ ጉዳዮች ምንድናቸው? እዚያ ላይ እንወያይ» ማለታቸውን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግሯል። 

ተሳታፊዎች «የአስራ አምስት ሚሊዮን የዎላይታ ሕዝብ አቋም እና ፍላጎት ህገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት የዎላይታ ሕዝብ ራሱን ችሎ በራሱ ክልል የመሆን አማራጭ ተወዳዳሪ እና አቻ የለውም» የሚል ምላሽ ለጠቅላይ ምኒስትሩ እንደሰጡ አሸናፊ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስረድቷል። 

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-02-2

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ በ47 ተከሳሾች ላይ የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ትዕዛዝ ተሰጠ!

ፍርድ ቤቱ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ በ47 ተከሳሾች ላይ የዓቃቤ ህግን ምስክሮችን ለመስማት ትዕዛዝ ሰጠ።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ የ47 ተከሳሾች ጉዳይ ተመልክቷል። በዚህም ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግን የመጀመሪያ ዙር የምስክር ቃል ለመስማት ከጥር 14 እስከ 22 ቀን 2012ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት በዋለው ችሎት እስከ አሁን ያልተያዙ 10 ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው እንዲሁም 3 ተከሳሾች በፖሊስ ተይዘው ባዛሬው ችሎት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ በጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው 10ሩም ሆኑ ሶስቱ ተከሳሾች በዛሬው ችሎት አለመቅረባቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ከተባሉት 3 ተከሳሾች ውስጥ ሁለቱ ከሀገር ውጭ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፥ አንደኛው ተከሳሽ ግን በቁጥጥር ስር ውሎ ለፌዴራል ፖሊስ መሰጠቱ ተገልጿል። ፍርድ ቤቱ ከሀገር ውጭ ናቸው የተባሉት ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው እንዲቀርቡና ለፌዴራል ፖሊስ ተላልፎ የተሰጠው ተከሳሽም በቀጣይ ችሎት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

(FBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Germany #Ethiopia

ጀርመን ለኢትዮጵያ የ352.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለገሰች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የጀርመን የኢኮኖሚያዊ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር ገርድ ሙለርን እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሁበርተስ ሄሊን በእንግድነት ተቀብለዋል። በተጨማሪም የጀርመን መንግሥት የግብርናን ዘዴ ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ 144 የግብርና መሣሪያዎችን ከነመለዋዎጫቸው ለግሷል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአቶ ለማ መገርሳ ቀጣይ የፖለቲካ ተሳትፎ ዕጣፈንታ...

#VOA #LemmaMegersa

ቪኦኤ : ኦቦ ለማ እንደሚያውቁት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ODP) ፈርሷል፤ የእርሶ የፖለቲካ ተሳትፎ ዕጣፈንታ ምን ይሆን?

ኦቦ ለማ : "ከዚህ ድርጅት ውጣልን ብለው እስካልወሰኑ ልዩነቴን ይዤ እሟገታለሁ። እኔ ብቻ ስላሆን ቅራኔ ያላቸው፣ የሚከራከሩ ብዙ አሉ። ከሆነልን እናስተካክላለን፤ ካልሆነ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተመካክረን የሚበጀንን እናደርጋለን።"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NEBE የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ዋናው (የመጨረሻው ውጤት) የያዝነው ሳምንት ሳይጠናቀቅ ይፋ እንደሚደረግ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። ውጤቱ የዘገየው ቅድመ ውጤቱ ይፋ የተደረገበት ቀን በመገፋቱ እንደሆነ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የጣና ገዳማት በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ተገለፀ!

የጣና ገዳማት በተደጋጋሚ ቅርሶቻቸው እንደተዘረፉባቸው የየገዳማቱ አስተዳዳሪዎች አስታወቁ፡፡ የኪዳነ ማርያም ብርጊዳ ማርያም ሀመረ ኖህ አንድነት ገዳም አስተዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ኪዳነ ማርያም እንደተናገሩት፤ ገዳሟ በተደጋጋሚ በሌቦች አደጋ ደርሶባታል፡፡ ለዘመናት ጠብቃ ያኖረቻቸው የብራና መፅሐፍትና የተለያዩ ቅርሶች ተዘርፈዋል፡፡

"ለሀገር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ሊሰጡ የሚችሉ የአባቶች ጥበብን የያዙ መፅሐፍት የት እንደደሩሱ አይታወቅም፡፡ በተደጋጋሚ ለመንግስት ብናመለክትም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘንም የሚሉት የገዳሟ አስተዳዳሪ ቅርሶችን ለመታደግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እርብርብ ማድረግ አለበት"ብለዋል፡፡

የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም አስተዳዳሪ መምህር ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ያሳይ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ በጣና ሀይቅ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ገዳማት በጀልባ በታገዙ ሌቦች በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ በርካታ ገዳሞች ቀደም ሲል የተለያዩና ብዙ ቅርሶች ያሏቸው ቢሆንም በአሁን ወቅት በየገዳማቱ የሚገኙ ቅርሶች የተቀበሩ ብቻ ናቸው፡፡

ወደፊት መንግስተ ጥበቃ የማያደርግ ከሆነ በየገዳማቱ የሚገኙ ቅርሶች ሊወድሙ እንደሚችሉ አሳስበዋል፡፡ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ መላኩ አላምረው በዚህ ዙሪያ በሰጡ ምላሽ፤ ቅርሶች መዘረፋቸውንና በተደጋጋሚ ለክልሉ መንግስት የድረሱልን ጥሪ መድረሱን አምነው በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ ይሰራል ብለዋል፡፡

በዋናነት የዚህ ሁሉ ችግር ክልሉ የባህር ላይ ፖሊስ ያለው አለመሆኑ ነው ያሉት አቶ መላኩ፤ በቀጣይ ይህን መሰል ዝርፊያ ለማስቆም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንሰራለን ብለዋል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከሀሰተኛ ገፆች ተጠንቀቁ!! 29,000 like ያለው ይህ በEritrean Press ስም መረጃዎችን የሚያሰራጭ ገፅ ሃሰተኛ ነው!! @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

ከቀናት በፊት 29,000 ገደማ Like ያለው በ "Eritrean Press" ስም የተከፈተው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ዜናዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ ገልፀንላችሁ ነበር። ይኸው ገፅ በዛሬው ዕለት "ኢዜማ እና ብልፅግና ፓርቲ" ለመዋሃድ ንግግር ጀምረዋል የሚል ሃሰተኛ ዜና ይዞ ወጥቷል። ትክክለኛው Eritrean Press የፌስቡክ ገፅ ከ250,000 በላይ Like ያለው ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ከሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ እንመክራለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተመሳሳይ ... Mereja. com የተባለው የፌስቡክ ገፅ ከ3,000,000 በላይ ተከታዮች አሉት ተመሳሳይ ሀሰተኛ መረጃ ለህዝብ አሰራጭቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በየአመቱ 23 ሺህ ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ ይያዛሉ!

በየአመቱ 23 ሺህ ሰዎች በኤች አይቪ ቫይረስ ይያዛሉ” ሲል የኢፌዴሪ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት በሽታውን ለመቆጣጠርና ለመከላከል እየሰራ ያለው ስራ መቀዛቀዝ በማሳየቱ በሽታውን የመቆጣጠሩ ስራ አዝጋሚ እንደሆነ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ የስርጭት ምጣኔ 0 ነጥብ 91 በመቶ ሲሆን ከ649 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ የ2019 አገራዊ የኤች አይ ቪ ስርጭት ያሳያል።

(ENA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
(ERDF Official)

የተሳሳተ መረጀ!

የብልጽግና ፓርቲ ከኢዜማ ጋር መደራደር ጀምሯል፤ በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጀ የተሳሳተ ነው፡፡ አዲሱ ውህድ ፓርቲ፤ ፕሮግራሙን ይፋ ከደረገ በኋላ ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስረት ዝግጁ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡ ሆኖም እስከሁን ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ጋር ንግግርና ድርድር አለመጀመሩን መግለጽ እንወዳለን፡፡

(EPRDF Official)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ለማ መገርሳ🛬አሜሪካ ገቡ!

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመከላከያ ሚኒስትሩ የተመራው ልኡኩ በዛሬው እለት ዋሽንግተን ዲ.ሲ መግባቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።

ጉብኝቱም የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አምባሳደር ፍጹም ገልፀዋል።

(አምባሳደር ፍፁም አረጋ - FBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ህዳር29

በትግራይ ክልል የብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ። አፈ ጉባኤው አቶ ሩፋኤል ሽፈረ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  “በዓሉ በክልሉ ህገ መንግሰታዊ ስርዓታችን ለዘላቂ ሰላምና ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ህዳር 29 ይከበራል” ብለዋል፡፡ በዓሉ የሚከበረው  በክልሉ  ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ  ልማት ስራዎች በሚያሳይና በስፖርታዊ ውድድር ነው።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ጉዳይ ላይ የሚመክረው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የቴክኒክ ስብሰባ ዛሬ ህዳር 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በካይሮ መካሄድ ተጀምሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
#JawarMohammed #DW

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ እንደ ፖለቲከኛ እንዴት እንደሚወዳደር እስካሁን እንዳልወሰነ አስታወቀ። አቶ ጀዋር ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃለ ምልልስ የራሱን ፓርቲ መስርቶ ወይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መወዳደርን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቶ እንደሚወስን ተናግሯል። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።

@tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia