ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው!

በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ ኤችአይቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ለቢቢሲ ገለፀ።

ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራና ቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በኤችአይቪ ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቫይሱ በወረርሽኝ ደረጃ የማይገኝባቸው የሶማሌ፣ የኦሮሚያና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሕግ መሰረት ይላሉ አቶ ዳንኤል፤ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከአንድ በመቶ በላይ በበሽታው ከተያዘ እንደ ወረርሽኝ እንደሚቆጠር በመግለጽ እነዚህ ክልሎች ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን ይላሉ አቶ ዳንኤል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው የስርጭት መጠን ሲታይ ወረርሽኝ ላይ ነው ማለት እንደማይቻል አስረድተዋል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia