Audio
#JawarMohammed #DW

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ እንደ ፖለቲከኛ እንዴት እንደሚወዳደር እስካሁን እንዳልወሰነ አስታወቀ። አቶ ጀዋር ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃለ ምልልስ የራሱን ፓርቲ መስርቶ ወይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መወዳደርን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቶ እንደሚወስን ተናግሯል። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።

@tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia