TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ክብረወሰን ሰበረች!

በአለም አቀፍ ደረጃ በህንድ ተይዞ የነበረው 66 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል ክብረ ወሰን ዛሬ ኢትዮጵያ ከ234ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሰፊ ቁጥር መስበሯ ይፋ ሆኗል።

ቢቢሲ በድረገጹ እንዳስነበበው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ በአገር አቀፍ ደረጃ በርሃማነትን ለመቀነስ ያለመ አካሄድ መሆኑን ገልጾ፤ 1 መቶ ሚሊዮን ህዝብ በነፍስ ወከፍ ቢያንሰ ሁለት ይተክላል በሚል የታሳቢ ቢሆንም ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራቸውን እዚያው በማድረግ እየተከሉ መሆናቸውን ጠቅሷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/200M-07-29

ፎቶ፦ ከትምህርት ሚኒስቴር/TIKVAH-ETH/
#አረንጓዴ_አሻራ በሀገር ደረጃ እስካሁን በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን 232 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን ያስታወቁት በወላይታ ሶዶ ከተማ ከአካባቢው የህብረተስብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

#አሁን በደረሰን መረጃ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ በኦሮሚያ 132 ሚሊዮን ፣ በደቡብ 45 ሚሊዮን፣ በትግራይ ስምንት ሚሊዮን 400ሺህ አማራ 38ሚሊዮን እና አዲስ አባባ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የተከናወኑ ይገኙበታል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ ጥዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ለመትከል የታቀደው 200 ሚሊዮን ቢሆንም እስካሁን የተከናወነው ከዚህ በላይ መድረሱን ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ለማወቅ የተቻለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ #ከፍተኛ_ጥንቃቄ_ይደረግ

ፌስታሉን ካልሰበሰብነዉና ካላነሳነዉ ሌላ ዘመቻ ያስፈልገናል 200 ሚሊዮን ፌስታል ለመልቀም ~ የሚተክል ያስተዉል፤ ጉዳዩ ጥንቃቄ ያሻዋል!!

#ሼር #share

Via #ዝንቅ
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምን ያህል ችግኝ ተተከለ?

√ኦሮሚያ 132 ሚሊዮን
√አማራ 38 ሚሊዮን
√ደቡብ 45 ሚሊዮን
√ትግራይ 8 ሚሊዮን 400 ሺህ
√አዲስ አባባ ከ3 ሚሊዮን በላይ

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በወላይታ ሶዶ እያደረጉት ባለው ስብሰባ ደርሷቸው የገለፁት ነው። #PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መግለጫ_ይሰጣል

በዛሬው ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ በተተከለው የዛፍ ችግኝ መጠን ላይ በደቂቃዎች ውስጥ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የዘመቻው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ያሰባሰበውን ዳታ በማጣራትና በማደራጀት ላይ መሆኑን ኮሚቴው ጨምሮ ገልጿል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሶዴፓ

የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ «ከአጋርነት ወደ ሀገራዊ ፓርቲ የሚያሸጋግረውን» የኢሕአዴግ ጥናት ገምገሞ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል። የማዕከላዊ፣ የክትትልና ኦዲት ኮሚቴዎችና አባላቱ ውይይት አድርገው የሚጨመርና የሚቀነስ ይለያሉ ብሏል።

Via #Eshet_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
353,633,660 ችግኝ ተተክሏል!

#በአረንጓዴ_አሻራ ቀን 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኝ ተተከለ። ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ አስተባባሪ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ በእለቱ የተተከለው ችግኝ ከእቅድ በላይ መሆኑ ተጠቅሷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መረጃው ትክክል አይደለም"👆

በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት የአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤ እስካሁን በኤርትራ መንግሥት ተቀባይነት አላገኝም በሚል ወጣው መረጃ ትክክል አይደለም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባብሏል።

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከአንድ ዓመት በፊት በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸው በኤርትራ መንግሥት ተቀባይነትን አላገኝም የሚለው ዜና በስፋት መነጋገሪያ ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/RD-07-29
#አረንጓዴ_አሻራ

23 ሚሊዮን የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ላይ አሻራቸውን አሳርፈዋል። የችግኝ ተከላው አስተባባሪ ኮሚቴ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ በተከላው 23 ሚሊዮን የሚገመት የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፏል ብሏል። በዛሬው ዕለትም ከ353 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።

ዕለቱ ህዝቡ የመሪውን ጥሪ ወደ ተግባር ለመቀየር ቀና አመለካከት እንዳለው ያሳየበት መሆኑም ነው በመግለጫው የተነገረው። የችግኝ ተከላው ከልጅ እስከ አዋቂ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የውጭ አገራት ኤምባሲ ሰራተኞች ጭምር የተሳተፉበት ነው።

በእያንዳንዱ የችግኝ ተከላ ቦታ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ መደረጉም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲተከል እገዛ ማድረጉ ተገልጿል። ዝናብ፣ ጭቃና የቦታ ርቀት እንዲሁም የችግኝ እጥረት በዛሬው ዕለት ያጋጠሙ ችግሮች ሲሆኑ በአጭር ጊዜ ለመፍታት በተወሰደ መፍትሔ ከታሰበው በላይ ማሳካት ተችሏል ነው የተባለው።

Via #ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኛም ችግኞች ነን በእውነትና ፍቅር ላይ ትከሉን!" #ማርሲል

ፎቶ: TIKVAH-ETH/#Maste/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ ቀን የተመዘገበውን ስኬት አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኅብረተሰቡ በዕለቱ ለመከወን የተያዘውን እቅድ በማለፍ ላስገኘው አመርቂ ውጤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም የመዲናዋ ነዋሪዎች በትላንትናው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ እለት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ

የወላይታ ህዝብ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም የከፈለውን መስዋእትነት አሁንም ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት ለተጀመረው ጥረት ሊጠቀምበት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ከወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ በከተማው ስታዲየም ተገኝቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የወላይታ ህዝብ የአገሩን ዳር ድንበር በማስጠበቅ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው ብለዋል። ”ዛሬ እኔ እዚህ የተገኘሁት ሰኔ 16 ቀን በአዲስ አበባ በተሞከረው ጥቃት እኔን ለማዳን ሲል ራሱን በሰዋው ዮሴፍ አያሌው ስም ነው” በማለት ገልፀዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለከፍተኛ መንግሥት ሹሞች የተመደቡ 3 ተሸከርካሪዎች ሃላፊዎቹ ሥራ ከለቀቁ በኋላ ለመንግሥት እንዳልተመለሱ ሸገር የፌደራል ዋና ኦዲተርን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ 14 ተሽከርካሪዎች ደሞ ከሊብሬያቸው ውጭ መኪኖቹ በአካል በመስሪያ ቤቶቹ አልተገኙም፡፡ በተለያዩ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ከ370 በላይ ተሸከርካሪዎች ያለ ሥራ ተበላሽተው እንደቆሙም ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡ ያልተመለሱና የጠፉ መኪኖችን አስመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉለትም መስሪያ ቤቶችን አዟል፡፡

Via ሸገር 102.1/wazema
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ_ፖሊስ

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራቸው የለቀቁ የቀድሞ ባልደረቦቹን ወደ ሥራቸው ለመመለስ መዘጋጀቱ ተነገረ። መንግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰጠውን አቅጣጫ፣ እንዲሁም ይቅርታ እና ምሕረት መሠረት በማድረግ የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ አሁን መልሶ ለመቀበል ወደ ሥልጠና ያስገባቸው 112 የሚሆኑ የቀድሞ አባላቱን ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬትም ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡›› አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለዕድለኛው የመንግስት ሰራተኛ!

የመንግስት ሰራተኛው የዳንግላ ከተማ ነዋሪ በልዩ ሎተሪ ግማሽ ሚሊዮን ብር እድለኛ ሆነ፡፡ በአማራ ክልል ዳንግላ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ፈቃዱ አሰማኸኝ በልዩ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ በ20 ብር በቆረጣቸው ሁለት ሎተሪዎች 500,000 ብር ዕድለኛ ሆኗል፡፡ ዕድለኛው ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን በደረሰው ገንዘብ ቤት የመኖሪያ ቤት ለመስራት እንዳሰበ ተናግሯል፡፡

Via የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸

የTIKVAH-ETHIOPIA #2ተኛ ዓመት በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት!! #TIKVAH_ETH

📸ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና
📸ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ/የWKU ፕሬዘዳንት/
📸አቶ ኦባንግ ሜቶ/የሰብዓዊ መብት ተሟጋች/

"ኢትዮጵያዊቷ ማዘር ትሬዛ" "ማዘር ኦፍ አፍሪካ"

🎂ሃምሌ 21 ስለነበረው አከባበር ተጨማሪ ፎቶዎች እና መረጃዎች እንዲሁም ምስጋና የምናቀርብላቸውን ሰዎች ወደበኃላ ወደናተ አደርሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሜ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ዳሎ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰውም ከሻሸመኔ ወደ ቡታጂራ በማቅናት የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሰበታ ወደ ሻሸመኔ ለቀስተኞችን ይዞ ይጓዝ ከነበረ ሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው ተብሏል።

በተከሰተው አደጋም የስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የወረዳው ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሳጅን አህመድ ቃለቶ ተናግረዋል። በአደጋው ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በባቱ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ሳጅን አህመድ ጠቁመዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

የዙና ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ300 ሺህ ብር ተቀጡ። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት የዙና ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ጌታሰውን ጉዳይ ተመልክቷል። አቶ ዘሪሁን ከ109 ግለሰቦች ሲኖትራክ ተሽከርካሪ አስመጣለሁ በማለት በአጠቃላይ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ በማጭበርበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዙና ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታ ሰው ላይ 122 ክሶችን መመስረቱም ይታወሳል።በዚህም ከ109 ግለሰቦች ከ 2ሚሊየን 600 ሺህ እስከ 314 ሺህ ብር መኪና አስመጣለው በማለት ባጠቃላይ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ ተቀብሎ መሰወሩ በክሱ ተመላክቶ ነበር። በክሱ መሰረትም አቃቤ ህግ አለኝ ያለውን የሰነድ ማስረጃ እና የግል ተበዳዮችን ምስክርነት አቅርቦ አሰምቷል።

ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 13 ክሶችን ውድቅ በማድረግ ተከሳሹን በ109 ክሶች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።በዚህ መሰረትም ፍርድ ቤቱ የዙና ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው በ14 ዓመት ፅኑ እስራትና በ300 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ወስኗል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብራዚል እስር ቤት ውስጥ በተነሳ ጠብ ቢያንስ 57 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። ጠቡ የተካሄደው በተቀናቃኝ የወንበዴ ቡድኖች መካከል ነው የተባለ ሲሆን ለአምስት ሰዓታት ያህል ቀጥሎ እንደነበር ባለስልጣናት ተናግረዋ። ጠቡ የተፈጠረው ፓራ ግዛት ውስጥ አልታሚራ በተባለ እስር ቤት ውስጥ ሲሆን አንደኛው የወንበዴዎች ቡድን ወደ ሌላኛው የወንበዴዎች ክልል በመሄድ ጠብ መቆስቆሱን ተናግረዋል። ከሞቱት መካከል አስራ ስድስቱ አንገታቸው ተቀልቶ ቀሪዎቹ ደግሞ በተነሳ እሳት ታፍነው መሞታቸውን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

Via #BBC
#update የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫን በተመለከተ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በሚያካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ላይ የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባንክ ሥራ እና የጉምሩክ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለይም ውይይት ያደርጋል፡፡

የከተማ ልማት፣ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን እና ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ እንደሚመረምር ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia