#አረንጓዴ_አሻራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ ቀን የተመዘገበውን ስኬት አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኅብረተሰቡ በዕለቱ ለመከወን የተያዘውን እቅድ በማለፍ ላስገኘው አመርቂ ውጤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም የመዲናዋ ነዋሪዎች በትላንትናው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ እለት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia