TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert በጎንደር ከተማ ከ3000 በላይ የመትረየስ ጥይት ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ ተያዘ። በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከ3000 በላይ የብሬን መትረየስ ጥይት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋወር ተገኝቷል የተባለ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የከተማው ፖሊስ መምሪያው የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ኮማንደር ማረልኝ ወንድም ለኢዜአ እንደተናገሩት ግለሰቡ የተያዘው ጥይቱን በከተማው ቀበሌ 16 ክልል በአንድ ባጃጅ በድብቅ ጭኖ ሲዘዋወር ነው፡፡ ሕገ ወጥ ከሆነው ጥይቱ ጋር ሐምሌ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ በድንገት በተካሄደ ፍተሻ መያዙም ታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመከላከያ፣ የፌድራልና የክልል ፖሊስ አዛዦች፣ የዞንና ልዩ ወረዳዎች የጸጥታ ኃላፊዎች የተካተቱበት የደቡብ ክልል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት በሐዋሳ እየተወያየ ነው። በሥራ ላይ የሚቆይበት የጊዜ ገደብና ዝርዝር የሕግ ክልከላዎች ውሳኔ ያገኛሉ ተብሏል።

Via Eshete Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን ጎብኝተዋል፡፡ በተጨማሪ ‹‹ቃለ አብ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ››ን ጎብኝተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢቦላ #ኢትዮጵያ

የኢቦላ ወረርሽኝን ቀድሞ ለመከላከል የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ለቅድመ መከላከል ስራውም ከ290 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን ነው ኢንስቲቲዩቱ የገለፀው።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በየነ ሞገስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል እና የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዚህም በቦሌ፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ እና ባህር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች የተጓዦችን የሰውነት ሙቀት በመለካት የልየታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በየብስ ትራንስፖርት ወደ አገር ወስጥ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ደግሞ በ21 የፍተሻ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመጡ መንገደኞች ነጻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እስከ 21 ቀን ድረስ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። እስካሁንም ከ17 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ልየታ የተደረገባቸው መንገደኞች የ21 ቀን ክትትል ተደርጎላቸው ነጻ መሆናቸው ታውቋል።

በአጠቃላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ኬላዎች የልየታ ማዕከል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዕርዳታ ያሰባሰበውን 116 ሚሊዮን ብር (አራት ሚሊዮን ዶላር)፣ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች እንደመደበ አስታውቋል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሶሳ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነው በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ ለዜጎቿ የሰጠችው ማስጠንቀቂያ??

አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ሶማሌ ክልል ከመጓዝ ጨርሶ እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለተጓዥ ዜጎች መረጃ በሚያቀብልበት ድረ-ገፅ በትናንትናው ዕለት ባወጣው ማስጠንቀቂያ በክልሉ የብጥብጥ ፣ የሽብርተኝነት ፣ የእገታ እና የተቀበረ ፈንጂ ሥጋት እንዳለ ገልጿል።

ማስጠንቀቂያው ከሶማሌ ክልል በተጨማሪ ወደ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል ወደ ምሥራቅ ሐረርጌ እና ጉጂ ዞኖች፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ምዕራብ ኦሮሚያን ወደሚያዋስኑ አካባቢዎች ለመጓዝ ያሰቡ እቅዳቸውን እንዲያገናዝቡ መክሯል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ እንዳለው በተጠቀሱት አካባቢዎች የታጠቁ ኃይሎች ግጭት እና ብጥብጥ ሊኖር ይችላል።
ከዚህም በተጨማሪ በኬንያ፣ ሱዳን፤ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ የድንበር አካባቢዎች ተመሳሳይ ስጋት እንዳለ አስታውቋል። ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚጓዙ ዜጎቹም በአደጋ ጊዜ ለመድረስ ውስን አቅም እንዳለው ይዘረዝራል።

የካናዳ እና የብሪታንያ መንግሥታትም እንዲሁ ሰሞኑን ለዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። የካናዳ መንግሥት እስካሁን ድረስ ፅኑ ባደረገው ማስጠንቀቂያ ዜጎቹ ወደ ኬንያ፣ ሱዳን፤ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ድንበሮች እና የደንከል በርሃ ጨርሶ እንዳይጓዙ ያስጠነቅቃል።
የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደ ጋምቤላ ክልል እና ሶማሌ ክልል ከመጓዝ እንዲታቀቡ ዜጎቹን አስጠንቅቋል። መሥሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ እና ከኬንያ ከምትዋሰንባቸው ድንበሮች መቶ ኪሎ ሜትሮች ያነሰ እንዳይቀርቡ ብሏል።

Via DW Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...copy-paste from last year's advisory."

#AddisStandard

#Ethiopia: #Somali region asks the @USEmbassyAddis to retract July 29 travel warning issued based on what the region said was an "outdated" data.@oladmohamed said the region has also communicated it's disappointment with the embassy & was informed that it was based on an old data.

The emb. issued a renewed travel warning advising US citizens against traveling to the region "due to potential for civil unrest, terrorism, kidnapping, and landmines." #oladmohamed said the advisory "seems to be a copy-paste from last year's advisory.

@tsegabwolde @tikvahethiopua
#አብን

በእነ አስጠራው ከበደ እና በእነ ሲያምር ጌቴ መዝገብ የተከሰሱት የአብን አባላትና አመራራሮች በብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ተፈቀደላቸው ሲል አብን በፌስቡክ ጉፁ አሳወቀ። ከታሰሩ ከ1 ወር በላይ የሆናቸውና በእነ አስጠራው ከበደ መዝገብ የተከሰሱት 26ቱ የአብን አመራሮችና አባላት ዛሬ ማለትም ሐምሌ 23/2011 ዓ.ም 8:00 ላይ ለ3ኛ ጊዜ አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው የነበረ ሲሆን እያንዳንዳቸው በ1ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወስኗል ብሏል ንቅናቄው። በሌላ በኩል በእነ ሲያምር ጌቴ መዝገብ የተከሰሱት ሲያምር ጌቴ በ3ሺህ ብር እንዲሁም ሌሎች እያንዳንዳቸው በ2 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ንቅናቄው በፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናሳ አዳዲስ ፕላኔቶችን ማግኘቱን ይፋ አደረገ!

የአሜሪካው የጠፈር ሳይንስ ምርምር "ናሳ" በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች ጋር ፍፁም የማይመሳሰል ፕላኔትን ጨምሮ ሦስት አዳዲስ ፕላኔቶችን ማግኘቱን ይፋ አደረገ። እነዚህ ሦስቱ ምሥጢራዊ ፕላኔቶች TOI-270 የተሰኘ ስርዓት አካል ሲሆኑ፣ በባህርያቸውም እንደ ማርስ እና እንደ ምድር ድንጋያማ እንዲሁም እንደ ሳተርን እና እንደ ጁፒተር ጋዛማ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የፕላኔቶቹ መገኘት አዳዲስ ዓለማትን ለማግኘት ለሚጥሩ ተመራማሪዎች መልካም ዕድል ሊሆን እንደሚችል ሳይንቲስቶች ጠቁመዋል። በአዳዲሶቹ ፕላኔቶች ህይወት ያላቸው አካላት ሊኖርባቸው እንደማይችሉም ተገምቷል።

ምንጭ፦ ኢንዲፔንደንት/#etv/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሬ የማገኘውን መረጃ እሰጣችኃለሁ! #12 #10

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ

በደቡብና ሱማሌ ክልሎች፣ በምዕራብ ኦሮሚያና የኦሮሚያ-ቤንሻንጉል አዋሳኝ ቦታዎች የጸጥታ ስጋት መኖሩን ጠቅሶ ዜጎቹ ወደተጠቀሱት ቦታዎች እንዳይጓዙ የአሜሪካ ኢምባሲ ትናንት አስጠንቅቋል፡፡ ምስራቅ ሐረርጌና ጉጅ ዞኖችም በስጋት ቀጠናነት ተካተዋል፡፡ በተለይ በሱማሌ ክልል የብጥብጥ፣ የሽብር፣ የሃይል እገታና የፈንጂ ሥጋት አለ ብሏል፡፡ በኤርትራ ድንበርም ተመሳሳይ ስጋት እንዳለ ገልጧል፡፡ የእንግሊዝና ካናዳ ኢምባሲዎችም በድረ ገጾቻቸው ተመሳሳይ የጉዞ ማስጠንቀቂያዎችን አውጥተዋል፡፡ ሱማሌ ክልል ግን መረጃው ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ጠቅሶ ኢምባሲው ማስጠንቀቂያውን እንዲያነሳ መጠየቁን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ የሜዲያና ኮምኒኬሽን አማካሪ ሞሐመድ ኦላድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና...

በዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 53 ሺ 163 ተማሪዎች ማለፋቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናገረ፡፡ ይህም ከአጠቃላይ ተፈታኞች የ72 ነጥብ 6 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 73 ሺ 210 ተማሪዎች ተቀምጠው ነበር፡፡ ከእነዚህ መካከል 20 ሺ 47ቱ ወይንም 27 ነጥብ 4 በመቶዎቹ ወደ ቀጣይ ክፍል #ያልተዘዋወሩ ናቸው፡፡ የፈተና ውጤቱን ወደየክፍለ ከተሞች አሰራጭቻለሁ ያለው ትምህርት ቢሮ ተማሪዎችም ከነገ ጀምረው ከየትምህርት ቤቶቻቸው ውጤታቸው እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፏል።

Via #shegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምስጋና

ለአበበች ጎበና ሕጻናት ማሳደጊያና ልማት ማህበርና ለመላ ሰራተኞቹ
ድርጅቱን ለማገዝ ከፈለጉ 011 155 3622/ 011 869 4629
የእንጀራ እና የባልትና ምርታቸውንም ከልማት ስራዎቻቸው ጥቂቱ ነው፡፡

ግራፊክስ ዲዛይነሮቻችን

👉 AMG(Amanuel Girma) @AGraphics 0928406521or 0924163982
👉 ሰለሞን(sc) ግራፊክስ @Scgpx +251912831494

በሳውንድ ሲስተም

ዲጄ ጆ ለሰርግና ለፓርቲ በቂ እቃዎችን ያቀርባል፡፡ +251911432922

በብዙ የተባበረን የዛው ሰፈር ልጅና የቤተሰባችን አባል
አብዱልከሪም ሁሴን +251 91 173 0261

ሽልማቶችን በመሸለም ለተባበሩን
👉 ቲ ማክስ ፍላሽ
👉 ሴንቸሪ ሲኒማ /@Century_Cinema/
👉 ቴድ ቴክኖሎጂ @Tedtechofficial
👉 @habmartofficial /ሀብማርት

በስራ እያገዙን ለነበሩት፦ ሜዳ ቻት ግሩፕ /@medachat/

እንዲሁም፦

√የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
√ፋና ቴሌቪዥን...የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia