ለከፍተኛ መንግሥት ሹሞች የተመደቡ 3 ተሸከርካሪዎች ሃላፊዎቹ ሥራ ከለቀቁ በኋላ ለመንግሥት እንዳልተመለሱ ሸገር የፌደራል ዋና ኦዲተርን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ 14 ተሽከርካሪዎች ደሞ ከሊብሬያቸው ውጭ መኪኖቹ በአካል በመስሪያ ቤቶቹ አልተገኙም፡፡ በተለያዩ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ከ370 በላይ ተሸከርካሪዎች ያለ ሥራ ተበላሽተው እንደቆሙም ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡ ያልተመለሱና የጠፉ መኪኖችን አስመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉለትም መስሪያ ቤቶችን አዟል፡፡

Via ሸገር 102.1/wazema
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia