TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Kenya

የኬንያ ፖሊስ 41 ኢትዮጵያውያንን ናይሮቢ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።

ግለሰቦቹ ወደ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች አገራት ለመዘዋወር በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ቀናት ያህል ሲጠባበቁ ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም መያዛቸውን ገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑን በሕገ ወጥ መንገድ ሊያዘዋውሩ ነበሩ የተባሉ ሁለት አዘዋዋሪዎችም በዚሁ አጋጣሚ የተያዙ ሲሆን አንደኛው #ኢትዮጵያዊ መሆኑም ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው እነዚህ የሕገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች በርካታ ዝውውሮች ጀርባ እንዳሉበት ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ በዚህ ሳምንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ወደ ኬንያ እንዴት እንደገቡ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት በእስር እንዲቆዩ መታዘዙን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#TikTok #Kenya

በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ሀገሪቱ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

ስምምነቱ የተደረሰው " ቲክቶክ ያልተገቡ ቪዲዮዎችን ያሰራጫል " በሚል እንዲታገድ ከአንድ ግለሰብ ለሀገሪቱ ፓርላማ ከቀናት በፊት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡

የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያው ኩባንያ ቲክቶክ፣ በመድረኩ ላይ የሚወጡትን ቪዲዮዎች መቆጣጠርን በተመለከተ ከኬንያ ጋር በጋራ ይሠራል ሲል የፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት አመልክቷል።

ይህን በተመለከተም ከኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾ ዚ ችው ጋር መነጋገራቸውን ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት፣ " ያልተገቡ ናቸው " የሚባሉ ቪዲዮች ከመድረኩ እንደሚወገዱ ታውቋል።

በአፍሪካ በቲክቶክ ላይ የሚወጡትን የቪዲዮዎች ይዘት በተመለከተ ቁጥጥር ለማድረግ ኩባንያው በኬንያ ቢሮ እንደሚከፍት ዋና ሥራ አስፈጽሚው ሾ ዚ ችው ይፋ ማድረጋቸውም ታውቋል።

ቲክቶክ ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፤ ህዝቡንም እያሳሳተ ነው በሚል ቲክቶክ እንዲታገድ አዛለች። እግዱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በተመሳሳይ ቴሌግራምም እንዲታገድ ውሳኔ ከተሰጠባቸው መተግበሪያዎች አንዱ ነው።

ሶማሊያ አሸባሪ ድርጅቶችና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውሏል በሚል ነው እንዲታገዱ ያዘዘችው።

@tikvahethiopia
#Kenya

የጎረቤት ኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ለማውጣት ዜጎች ክፍያ እንዲፈጽሙ መንግሥት ያወጣውን መመሪያ #አገደ

የኬንያ መንግሥት ይህን መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ ዜጎች ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ማጋሬ ጊኬንይ የተባሉ ሐኪም ናቸው መንግሥት አዲሱን መመሪያ ያወጣው “ድንገተኛ እና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ” ነው ሲሉ የሕዝብ ድምፅ በማሰባሰብ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት።

የተሰበሰበው የሕዝብ ድምፅ እንደሚለው በአዲሱ መመሪያ መሠረት፤ በርካታ ዜጎች መታወቂያ ካርድ በቀላሉ ማግኘት አይችሉም።

ከዚህ ቀደም በነፃ ይሰጥ የነበረው ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ አሁን 1 ሺህ ሺልንግ [370 ብር ገደማ] እንዲሆን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አዟል።

መታወቂያ ለማሳደስ ደግሞ ኬንያዊያን 2 ሺህ ሺልንግ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል።

ኬንያዊያን እያሻቀበ ባለው የኑሮ ግሽበት ምሬታቸውን እየገለጡ ባሉበት ወቅት ነው መንግሥት ገቢውን ለማሳደግ ሲል ዜጎች ከዚህ ቀደም በነፃ አሊያም በርካሽ የሚያገኟቸውን አገልግሎቶች በበለጠ ክፍያ እንዲሆን ያደረገው።

በርካታ ኬንያዊያን በሚከፍሉት ግብር አማካይነት ተግባራዊ እየሆኑ ላሉ የመንግሥት ግልጋሎቶች ተጨማሪ ክፍያ መጠየቃችን ተገቢ አይደለም እያሉ ናቸው።

አዲሱ መመሪያ መታወቂያ ካርድ ብቻ ሳይሆን ፓስፖርት፣ የጋብቻ ወረቀት፣ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሁም የልደት እና ሞት ምስክር ወረቀት ለማውጣትም ክፍያ ይጠይቃል።

አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት አሊያም ለማሳደስ ይጠየቅ የነበረው ክፍያ 50 በመቶ ሲያድግ የልደት እና ሞት ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቅ ክፍያ በአራት እጥፍ አድጎ 200 ሺልንግ ገብቷል።

መንግሥት በተጨማሪ ዜግነት አሊያም የመኖሪያ ፈቃድ ለማስጠት የሚጠይቀውን ክፍያ እጥፍ አድርጎታል።

ከኬንያዊያን ዜጎች በውጭ ሃገር የተወለዱ ልጆች የኬንያ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚጠየቁት ክፍያ 1 ሚሊዮን ሺልንግ ሆኗል።

በደንገት የተጫኑት የክፍያ መመሪያዎች አቅም የሌላቸው ዜጎች የመንግሥትን ግልጋሎት ተጠቅመው አስፈላጊ ወረቀት ለማግኘት ሊቸገሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ጭሯል።

ባለፈው ዓመት መስከረም ወደ ሥልጣን የመጡት የፕሬዝደንት ሩቶ መንግሥት በርካታ የግብር ዓይነቶችን ዜጎች ላይ የጣለ ሲሆን የነዳጅ ዋጋ ከፍ እንዲልም አድርጓል።

የብሔራዊ ፓርክ መግቢያ ዋጋን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶች ክፍያ ከፍ እንዲልም ሆኗል።

ባለፈው ሳምንት የገቢዎች መ/ቤት ባለሥልጣናት ወደ ኬንያ የሚመጡ ዜጎችም ሆኑ ጎብኝዎች ከ500 ዶላር በላይ ተመን ያለው ዕቃ ይዘው ከተገኙ ይቀረጣሉ ብሏል።

ፕሬዝደንት ሩቶ እስካሁን ስለ ዋጋው ጭማሪ ያሉት ነገር ባይኖርም ሐሙስ ዕለት ለሃገሪቱ ዜጎች ባስተላለፉት መልዕክት ኬንያዊያንን ከዕዳ ጫና ለማላቀቅ " ቀላል ያልሆኑ ግን አስፈላጊ " ውሳኔዎችን ለመውሰድ ተገድጃለሁ ብለዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia #Kenya

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ እያደረጉት በሚገኘው ይፋዊ ጉብኝት በፕሬዝዳነት ዊልያም ሩቶ በስቴት ሀውስ ኬንያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፤ " የአቀባበል ስነስርዓቱ ሁለቱ መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖቻቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ እያደርጓቸው ያሉ ጉልህ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ጅማሮ ነው። " ብሏል።

ሁለቱ መሪዎች በድይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ጥልቅ እና ታሪካዊ ግንኙነት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር አንስተው ይኽንኑ በቁርጠኝነት ማጠናከር እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተነግሯል።

" ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወሳኝ አጋጣሚ ሆኖ የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የበለጠ ለማዳበር ብሩህ መፃዒ ጊዜን ያመላከተ ሆኗል " ሲል የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ትላንት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኬንያ መግባታቸውና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንደተቀበሏቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር #ታንዛኒያ ለሳምንታት በዘለቀ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት 155 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 236 ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ጠ/ሚ ቃሲም ማጅዋሊ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት በጎረቤት #ኬንያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ በትንሹ 35 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። 40,000 ሰዎች  ደግሞ ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ሆነዋል።…
#Kenya

በጎረቤት ኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል።

ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደረሰው አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 188 መድረሱን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር አሳውቋል።

እስካሁን ያልተገኙ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተገልጿል።

በኬንያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን የከፍታ ቦታዎች መናድም ነዋሪዎችን ካለመጠጊያ አስቀርቷል፡፡

መንገዶችን ድልድዮችን እና ሌላም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ውድሟል። #VOA

@tikvahethiopia
#Kenya #USA

የጎረቤት ኬንያ ፕሬዜዳንት በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ ከ2008 ወዲህ ወይም ከ16 ዓመት በኃላ ነው ዋይት ሃውስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ መሪ በዚህ ደረጃ ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው።

አሜሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፍ ያለ አቀባበል እና ከፍተኛ የቀድሞና የአሁን ባለስልጣናት በተገኙበት ልዩ እራት ግብዣ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

ከፕሬዜዳንት ጆ ባይደንና ከሌሎች ባለልሰጣናት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉም ሲሆን ሁነኛ ስምምነቶችም ከአሜሪካ መንግሥት ጋር መፈራረማቸው ተሰምቷል።

ሩቶ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ጋርም ተገናኝነትው መክረዋል።

በሌላ በኩል ፥ ኬንያ የሀገሪቱን የጸጥታ ስራዎች እና የሰላም ማስከበር ተልእኮዎቿን ለማሳደግ 16 በአሜሪካ የተሰሩ እጅግ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ልትቀበል እንደሆነ " ሲትዝን ቲቪ " ዘግቧል።

ይህ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዋሽንግተን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ለኬንያ ካበረከቱት መልካም ነገሮች አንዱ ነው ተብሏል።

ሂሊኮፕተሮቹ እ.ኤ.አ ከ2024 እስከ 2025 መጨረሻ ናይሮቢ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋይት ሀውስ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኬንያ በመስከረም ወር 150 " M1117 " የታጠቁ እጅግ ዘመናዊ የደህንነት ተሽከርካሪዎችን ትቀበላለች።

More ➡️ @thiqahEth

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA #kenya

የጎረቤታችን ሀገር ኬንያን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶን ተቀብለው እያስተናገዱ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኬንያን ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ #የNATO_አባል_ያልሆነች (non-NATO) ዋና አጋር ሀገር እንደምታደርጋት ቃል መግባታቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Kenya

ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው።

መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል።

ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡

ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል።

ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል።

ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ተነግሯል።

ይህ በኬንያ ወጣቶች መሪነት የተነሳው እና ባለፈው ማክሰኞ በናይሮቢ ከተማ ተጀምሮ በመላው አገሪቱ የተሰራጨው ተቃውሞ በመጭው ማክሰኞ ብሔራዊ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ተቃዋሚዎቹ ለምን አደባባይ ወጡ ?

ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደስተኛ አይደሉም።

አካሄዳቸውም ለብዙ ኬንያውያን ኑሯቸውን አስቸጋሪ ማድረጉን ይገልጻሉ።

በተለይም መንግሥት አሁን ያዘጋጀው የታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ የህዝቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል እንደሆነ በመግለጽ እየተቃወሙ ነው።

የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቶ ነው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ የተቀየረው።

የኬንያ መንግሥት ምን ይላል ?

መንግሥት የታክስ ጭማሪ ሊያደርግ ያቀደው ብድር ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ ገልጿል።

ተቃውሞውን ተከትሎ ከረቂቅ አዋጁ ላይ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን ዛሬም ቀጥሏል።

የታክስ ጭማሪው ምን ላይ ነው ?

መንግሥት በያዘው እቅድ የታክስ ጭማሪው በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የሚደረግ ነው።

በነዳጅ ላይ ሊጨመር የታሰበው 9 ሺልንግ ሲሆን ጭማሪው ለፈረሱ መንገዶች መጠገኛ እንደሚሆን የአዋጁ አርቃቂዎች አስታውቀዋል።

መንግስት በተጨማሪ አካባቢን ለመጠበቅ በሚል ታክስ ለመጣል ያቀደ ሲሆን ይህም ደግሞ የፕላስቲ ውጤቶች የሚያስከትሉትን ብከላ ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል።

ብሔራዊ ሸንጎው ረቂቅ አዋጁን ሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ለተቃውሞ የወጡት ኬንያውያን ግን በተቃውሟቸው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።

#AFP
#VOA
#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው። መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል። ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡ ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል። ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ…
#Update

በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል።

ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው።

የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም ሆነ የግል ንብረትን እንዳያወድም ወይም እንዲያወድም እንደማይፈቀድለት አፅንዖት ሰጥቷል።

የተቃውሞ ሰልፈኛው የሚሄድበትን አቅጣጫ ቀደም ብሎ ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ እጅባና ጥበቃ እንዲደረግለት ማድረግ አለበት ተብሏል።

ሰልፈኞቹ ሰልፉን በፍጹም ሰላማዊ መንገድ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳሰበው የሀገሪቱ መንግስት ትጥቅ ታጥቆ ሰልፍ መውጣት እርምጃ ሊያስወስድ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፦
- የውሃ፣
- የኃይል አቅርቦት
- ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡት ወሳኝ ቦታዎች ላይ እንዳያገኙ ተከልክለዋል።

በተጨማሪ በህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ ተገልጿል።

በምንም መልኩ በየብስ ፣ በባቡር፣ በባህር ፣ በአየር ትራንስፖርት ላይ ጣልቃ መግባት እንደ ሌለባቸው ምንም ይሁን ምን ለሀገሪቱ ህግ የበላይነት ሁሉም ሰው ሊታዘዝ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ሁሉም ተቃዋሚዎች ሰልፉን ሁከት እና ብጥብጥን በማያበረታታ መንገድ እንዲያደርጉ እንዲሁም ደግሞ ፦
° ሰልፉን መሳተፍ የማይፈልጉ / ተቃውሞ ማድረግ የማይፈልጉ
° የፖሊስ አባላትን ፣
° የመንግስት አካላትን ማስፈራራት ፣ ማስጨነቅ እና መተንኮስ እንደሌለባቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኬንያ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ። የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት ያረቀቀውን አዲስ የታክስ ሕግ የተቃወሙ ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ቅጥር ጊቢ ጥሰው ገብተዋል። ፖሊስ በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ተቃዋሚ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት እና አስቀሽ ጭስ ተኩሷል። እስካሁን ድረስ ቢያንስ 5 ሰዎች በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ሕይወታቸው አልፏል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት የአገሪቱ ም/ ቤት አባላት…
ፎቶ ፦ በኬንያ ናይሮቢ የተቆጡ ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባታቸው በርካታ የምክር ቤቱ አባላት ምድር ቤት (ግራውንድ) ለመደበቅ ሲሯሯጡ ታይተዋል።

የተ/ምክር ቤት አባላቱ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረውንና በተለያዩ ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥለውን ረቂቅ ሕግ አጽድቀው ነበር።

ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ሕግ በ195 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ፣ በ106 የም/ ቤት አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ነው የጸደቀው።

በቀጣይ ወደ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ይመራል።

#Kenya
#KenyaParliament

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ፎቶ ፦ የሀገሪቱን ፓርላማ በኃይል ጥሰው የገቡት መንግሥት ያረቀቀውን የፋይናንስ ሕግ የሚቃወሙ የኬንያ ወጣቶች በፓርላማው ካፍቴሪያ ምግብ ሲበሉ ታይተዋል።

ወጣቶቹ ዛሬ ጨምሮ ላለፉት ተከታታይ ቀናት " ታክስ ለመጨምር ያሰበው ረቂቅ ሕግ ኖሮ ያከብድብናል ፤ ተውት ይቅር ! አንደግፈውም " በማለት እየተቃወሙ ይገኛሉ።

በዛሬው ተቃውሞ የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን ወጣቶቹ ግን የሀገሪቱን ፓርላማው ጥሰው ገብተዋል።

የተወሰነውን ክፍልም በእሳት አያይዘዋል።

#Kenya
#KenyaParliament

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የሀገሪቱን ፓርላማ በኃይል ጥሰው የገቡት መንግሥት ያረቀቀውን የፋይናንስ ሕግ የሚቃወሙ የኬንያ ወጣቶች በፓርላማው ካፍቴሪያ ምግብ ሲበሉ ታይተዋል። ወጣቶቹ ዛሬ ጨምሮ ላለፉት ተከታታይ ቀናት " ታክስ ለመጨምር ያሰበው ረቂቅ ሕግ ኖሮ ያከብድብናል ፤ ተውት ይቅር ! አንደግፈውም " በማለት እየተቃወሙ ይገኛሉ። በዛሬው ተቃውሞ የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን ወጣቶቹ ግን…
#Kenya

የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ሰላምና የህግ ስርዓትን እንዲያስከብር ትዕዛዝ ተሰጠው።

የሀገሪቱ መንግሥት ለቀናት ከዘለቀው የፋይናንስ ህግ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የኬንያ መከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ደህንነት፣ ሰላምና የህግ ስርዓት እንዲያስከብር አሰማርቷል።

በሌላ በኩል ፤ የኬንያው ፕሬዜዳንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው የዛሬውን ታቃውሞ ፤" እንደ ሀገር ክህደት / ከሃዲነት " የሚቆጠር እንደሆነ ገልጸው ፤ የጸጥታ ኃይሎች የኬንያውያንን ደህንነት እንዲያስጠብቁ መመሪያ እንደሰጡ ተናግረዋል።

ተቃዋሚዎች የኬንያ ፓርላማን ሰብረው ስለገቡበት ክስተት ጉዳይም ምርመራ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የወንጀል ድርጊትና ወንጀለኞችን ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ሰልፍ ከሚያደርጉት መለየት ይገባል ብለዋል።

ፕ/ት ሩቶ " አደገኛ ወንጀለኞች " ሲሉ የጠሯቸው አካላት ሊፈጸሙት የሚችልን ማንኛውም ሙከራ ከንቱ ሆኖ እንዲቀር የደህንነት አካላት እርምጃ እንዲወስዱ እንዳዘዙ ገልጸዋል።

ህዝቡንም " ዛሬ ማታ ተኙ ! የናተ፣ የቤተሰቦቻችሁ እና የንብረቶቻችሁ ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥተን እንጠብቃለን " ብለዋል።

" የተቃውሞው የፋይናስ ምንጮች ላይም ምርመራ ይደረጋል " ሲሉ አክለዋል።

በኬንያ ዛሬ ማክሰኞ በነበረው ተቃውሞ እስካሁን በታወቀው ብቻ 10 ሰዎች ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።

#Kenya
#FinanceBill2024

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Kenya

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል።

ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።

ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤ ይህንንም ተቀብዬ በሕጉ ላይ አልፈርምም፣ ስለዚህም ቀሪ ይሆናል። ሕዝቡ ፍላጎቱን አሳውቋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሕዝቡ ረቂቅ ሕጉን እንደማይፈልገው ገልጿል ያሉት ሩቶ " እኔም በዚህ ተስማምቻለሁ " በማለት ነው በሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ በይፋ ያሳወቁት።

ከሰሞኑን በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ ነበር። ትላንትም ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባት ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል። ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኬንያ

ምንም እንኳን ትላንትና የኬንያ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በፋይናንስ ረቂቅ ሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደተደረገ ቢያሳውቁም ዛሬም ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ነበር።

ናይኖቢ ውስጥ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጪስ ተኩሰዋል።

ወደ ፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት የሚወስደውን መንገድ ዘግተውታል።

ዛሬም በከተማይቱ በርካታ የንግድ ተቋማት ባደረባቸው ስጋት በራቸውን ሳይከፍቱ ነው የዋሉት።

ከናይሮቢ በተጨማሪ ሞምባሳና ኪሱሙ ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ነበር።

ትላንት ሩቶ ውሳኔያቸው ካሳወቁ በኃላ ተቃዋሚዎች ፦
- ቀጣይ ወዳሉበት ቤተመንግስት እንመጣለን። ይጠብቁን !
- ' ከሃዲ ፣ ወንጀለኞች ' እያሉ በቴሌቪዥን ለተናገሩት ዋጋ ይከፍላሉ
- ስልጣን የህዝብ ነው
- ለውሳኔው አርፍደዋል
- አሁን ደግሞ የስልጣን መልቀቂያ ለማስገባት ይዘጋጁ !
- ስልጣን ለመልቀቅ ይዘጋጁ የሚሉ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲያሰራጩ ነበር።

ኬንያውያን የፋይናንስ ረቂቁን " ኑሮ ያስወድድብልናል ፣ የስራ አጥነት እጅግ በከፋበት ሰዓት ግብር መጨመር አይገባም ፣ ተደራራቢ ግብር በቃን " በሚል ነበር ተቃውሞ የጀመሩት።

በወጣቶች በተመሩ የጎዳና ላይ ተቃውሞዎች ቢያንስ 20 ሰዎች ህይወታቸውን እጥተዋል። ተቃውሞው እየበረታ ሲመጣም ሩቶ " በቃ ረቂቅ ሕጉን ትቼዋለሁ " የሚል ውሳኔያቸውን አሳውቀዋል።

#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ ምንም እንኳን ትላንትና የኬንያ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በፋይናንስ ረቂቅ ሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደተደረገ ቢያሳውቁም ዛሬም ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ነበር። ናይኖቢ ውስጥ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጪስ ተኩሰዋል። ወደ ፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት የሚወስደውን መንገድ ዘግተውታል። ዛሬም በከተማይቱ በርካታ የንግድ ተቋማት…
#Kenya

በኬንያ ሰሞነኛውን ተቃውሞ እና ሰልፍ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በርካቶች ዝርፊያ ላይ መሰማራታቸው ተሰምቷል።

የሀገሪቱ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች " ዋጋቸውን ያገኛሉ " ብሏል።

በኬንያ ከፋይናንስ ሕጉ ጋር የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አልቆመም።

ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ሩቶ " ትቼዋለሁ ፤ አልፈርምም፣ ተሰርዟል " ቢሉም ተቃዋሚዎቻቸው " ረፍዷል ስልጣን ይልቀቁ " በሚል ተቃውመ ቀጥለዋል።

ተቃውሞውን ተከትሎ ግን በርካታ ዘረፋዎች እየተፈጸሙ ነው።

እነዚህ የዝርፊያ ተግባራት በዜጎች የእጅ ስልክ እና በደህንነት ካሜራዎች ተቀርጸው እየተሰራጩ ነው።

የኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ተቃውሞ እና ሰልፉን በመጠቀም የወሮበሎች ቡድን ንጹሃንን ሲዘርፉ መታየታቸውን እና እነዚህን ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

ዘራፊዎች የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ዋጋቸውን ያገኛሉም ብሏል።

ሌሎችም ከሰልፉ ጋር በተያዘ ህገወጥ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን ተፈላጊ ተጠርጣሪ ሰዎችንም በፎቶ አሰራጭቷል።

@tikvahethiopia
#Kenya

የኬንያው ፕሬዝዳንት ተቃውሞ በተደራጀባቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርበው ከወጣቶች ጋር ተወያዩ።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያዘጋጁትን የፋይናንስ ሕግ ውድቅ እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው የወጣቶች ተቃውሞ የተደራጀበት ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ለውይይት መቅረባቸው ታሪካዊ ነው ተብሏል።

ሩቶ ትላንትና ከሰዓት በ ' X ' ስፔስ ላይ ቀርበው ከህዝብ ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

' X ' ላይ ከተቃዋሚ ወጣቶቹ ጋር ለጥያቄ እና መልስ መቅረባቸው ፍጹም ያልተጠበቀ እንደነበር ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ በውይይቱ ቀጥተኛ እና መሸፋፈን ያልታየባቸው ጠንካራ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር።

መጀመሪያ ውይይቱ በጽህፈት ቤታቸው ይፋዊ ገጽ አስተናጋጅነት ሊካሄድ ነበር በኋላ ባገጠመ እክል ከፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎች አንዱ በሆነ ኦሳማ ኦቴሮ በተባለ ግለሰብ ገጽ ገብተው ነው ምላሽ የሰጡት።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ያለ ከልካይ የፈለጉትን ሲጠይቁ፣ ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ መሃል ላይ እየገቡ ሲመላለሱና ማብራሪያ ሲጠይቁ ነበር።

ተቃዋሚዎቹ ምን አሏቸው ?

መንግስታቸው እስካሁን ያስመዘገበውን ነገርና ባህሪያቸውን በተመለከተ አንስተው አብጠልጥለዋቸዋል።

በርካታ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በፖሊስ በጭካኔ መገደላቸውን አመልክተው " በሽብርተኛ አገር ውስጥ ነው እንዴ ያለነው? " በማለት ጠይቀዋቸዋል።

የመረጣችሁ ሰው በመሆኑ ቅድሚያ ለሰው ግድ ሊሰጣችሁ ይገባል ብለዋቸዋል።

ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ አጥ የሆነ አንድ የውይይቱ ተሳታፊ " በካቢኔዎት ውስጥ ብቃት የሌላቸው በርካታ ባለሥልጣናት አሉ " ብሏቸዋል።

➡️ ሙሰኛ እና የተቀመጡበት ቦታ የማይገባቸው በርካታ ሰዎች በመንግስት ውስጥ እንዳሉ ነግረዋቸዋል።

የተገደሉ ወይም የተጎዱትን ሰዎች ቤተሰቦች ለማነጋገር ሞክረዋል ወይ? ሲሉም ጠይቀዋል።

አንዳንዶች ውሸታም እና ሐዘኔታ የሌላቸው በሚል ከሰዋቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ምን መለሱ ?

● በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለሥልጣናትን በሙሉ ለማባረር ቃል ገብተዋል።

● " እውነት ነው ፤ አንዳንድ ባለሥልጣኖቻችን አስጸያፊ ድርጊቶችን እንደሚያሳዩ እስማማለሁ ፤ እራሳቸውን እንዴት እንደሚያስተካክሉ እኔም ጉዳዩን በግሌ አንስቼላቸዋለሁ። ከዚህ የበለጠም አደርጋለሁ " ብለዋል።

● በተቃውሞው የተገደሉ ሰዎችን አሃዝ በማጋነን አንዳንዶችን " ግድየለሽ " ሲሉ ከሰው ቁጥሩ 25 መሆኑን ተናግረዋል።

● በጥይት የተገደለ የ12 ዓመት ህፃን እናት ማነጋገራቸውን ገልጸዋል።

● በተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስ በካሜራ እይታ ውስጥ የገባ የፖሊስ አባል ክስ እንዲመሰረትበት እንዳዘዙ ተናግረዋል።

NB. የኬንያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ እንደሆነ አሳውቋል።

● ሩቶ አምባገነን እንዳልሆኑ ተናግረዋል። " እኔ ፕሬዝዳንት ነኝ ትክክል !! ግን ፕሬዜዳንቱ ፍጹም ስልጣን የለውም ለዛም ነው ዴሞክራሲያዊ ሀገር የሆነው ቼክ ኤንድ ባላንስ አለ። ፕሬዝዳንቱ አምባገነን አይደለም " ብለዋል።

● ረቂቅ ሕጉን ማንሳታቸውን በማረጋገጥ ፣ ሕጉን በተመለከተ ግን የተሳሳተ ግንዛቤ መፈጠሩን ጠቅሰዋል። የሕጉ ዓላማ የኬንያውያንን ንግድ ማጠናከረ ነበር በማለተ የተካተቱትን ዕቅዶች ጠቃሚነት አብራርተዋል።

ታሪካዊ ነው በተባለውና ምንም አይነት ቁጥጥር ባልነበረው የ ' X ' ህዝባዊ ግልጽ ውይይት መድረክ ላይ ከ150,000 በላይ ሰዎች ታድመው ነበር። 

ከዚህ በፊት አንድ ፕሬዝዳንት ይህን ያህል በይፋ ወጥቶ እራሱን በማጋለጥ ከሕዝቡ በቀጥታ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠበት ጊዜ ባለመኖሩ ምክንያት ነው ታሪካዊ የተባለው።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ሁልጊዜ በሚያስቆጡ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት ክርክር ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል።

በፖለቲካ ሕይወታቸው ፈታኝ ጥያቄዎችን እና ሁኔታዎችን ከመጋፈጥ ወደ ኋላ ሲሉም ታይተው አይታወቅም።

በመገናኛ ብዙኃን ዘንድ ከቀደምት ፕሬዝዳንቶች በበለጠ በራቸው ክፍት መሆኑ ይነገራል።


#BBCNEWS
#Kenyans
#CitizenTV

@tikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Africa #Kenya

" በሙስና የተዘፈቀውን ካቢኔዎትን ይበትኑ ! " - የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት

ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን ቢሰርዙም ተቃውሞው ቀጥሏል።

የኬንያ አብያተ ክርስትያናት ፕሬዜዳንቱ ካቢያናቸውን እንዲበትኑ ጠይቀዋል።

የቤተክርስቲያን መሪዎች እና በርከታ ኬንያውያን ሩቶ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና እንዲያጸዱ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት ፥ " የሩቶ አስተዳደር በመጥፎ አመራር እና የሙስና ክሶች ተጨማልቋል " በማለት የታቅውሞውን ድምጽ ተቀላቅሏል።

ምክር ቤቱ ፥ ሩቶ ሚኒስትሮቻቸውን እንዲያባርሯቸው ጠይቋል።

" ፕሬዚዳንቱ በራሳቸው አንደበት ካቢኔያቸው ብቃት እንደሌለው ተናግረዋል። ኬንያውያንም የፕሬዜዳንቱ ካቢኔ ምንም ብቃት የለውም እያሉ ነው። በተጨማሪ አብዛኛዎቹ የካቢኔ አባላቶች ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ ናቸው። ኬንያውያን ካቢኔውን የመበተኛ ጊዜ አሁን ነው እያሉ ነው " ሲል ገልጿል።

በኬንያ የፋይናንስ ረቂቁ ባስነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 40 ሰዎች መገደላቸው፤ 380 ሰዎች መጎዳታቸው ፣ ታቃዋሚዎችም ፓርላማውን በመውረር የምክር ቤት አባላት እንዲሸሹ ከሆኑ በኃሏ ሩቶ ረቂቁን ውድቅ አድርገው ነበር።

ሩቶ ከቀናት በፊት ፦
- ቁልፍ ሚኒስትሮችን እና የመንግስት ተቋማትን ማዋሃድ
- የመንግስት መኪናዎች ለ12 ወራት እንዳይገዙ መከልከል
- የመንግስት ባለስልጣናትን አላስፈላጊ የውጭ ጉዞ ማገድን ጨምሮ የተለያዩ የወጪ ቅነሳ እርምጃዎችን ይፋ አድርገው ነበር።

ነገር ግን ተቃውሞው ቀጥሎ ፕሬዜዳንቱ በመስና ተዘፍቋል የተባለውን ካቢኔ እንዲባትኑ ግፊት እየተደረገ ነው።

የኬንያ ፖለቲካ ተንታኝ ዲስማስ ሙአኮ " ፍርድ ቤት አንዳቸውንም በምንም ነገር ጥፋተኛ እስካላላቸው ድረስ ፕሬዜዳንት ሩቶ ሰዎች እንዲባረሩ ስለጠየቁ ብቻ የካቢኔ አባሎቻቸውን የማባረራቸው እድል ዜሮ ነው " ብለዋል።

" ነገር ግን፣ በጣም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የኑሮ ውድነቱ ነው። የኢኮኖሚውን ሁኔታ በማሻሻል እና ለኑሮ ውድነቱ መፍትሄ በማምጣት የመንግስት እዳ በአብዛኛው ኬንያውያን ዜጎች ላይ የማይወድቅ መሆኑን ማረጋገጥ ከቻሉ ህዝቡም ተረጋግቶ እስከ 2027 ድረስ (የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ) መጠበቅ ይችላል " ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቪኦኤ ነው ያገኘው።

#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Africa #Kenya " በሙስና የተዘፈቀውን ካቢኔዎትን ይበትኑ ! " - የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን ቢሰርዙም ተቃውሞው ቀጥሏል። የኬንያ አብያተ ክርስትያናት ፕሬዜዳንቱ ካቢያናቸውን እንዲበትኑ ጠይቀዋል። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና በርከታ ኬንያውያን ሩቶ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና እንዲያጸዱ ጥሪ እያቀረቡ…
#Kenya #Update

ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ።

ለሳምንታት በህዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ።

ሩቶ ዛሬ ነው ይህን እርምጃ የወሰዱት።

የፕሬዜዳንቱ እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው የፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው።

ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፥ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝደንት ራጋቲ ጋቻጉ ሲቀሩ ሌሎቹን ሚኒስትሮቻቸውን በሙሉ ማሰናበታቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ እርምጃውን የወሰዱት የሕዝባቸውን ድምፅ በመስማት መሆኑን ተናግረዋል።

#DW
#CitizenTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya #Update ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ። ለሳምንታት በህዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ። ሩቶ ዛሬ ነው ይህን እርምጃ የወሰዱት። የፕሬዜዳንቱ እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው የፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው። ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፥ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም…
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል።

ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል።

" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።

ከሥራቸው የማይባረሩት ምክትል ፕሬዝዳንቱና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የሚያገለግሉት የካቢኔው ዋና ፀሐፊ ሥልጣናቸው ላይ ይቆያሉ።

ሌሎቹ በጠቅላላ የካቢኔያቸው አባላት ሚኒስትሮች ተባረዋል።

የፋይናንስ ረቂቅ ሕጉን ተከትሎ ፥ " ግብር ሊጨመርብን አይገባም በቃን ! ፣ ተጨማሪ ግብር አንከፍልም፣ ሕጉ ኑሮው ያስወድድብናል " በማለት ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የጀመሩት ተቃውሞ ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የ39 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ሩቶ ሕጉን ሰርዘውታል።

ምንም እንኳን ሕጉ ሙሉ በሙሉ ቢሰረዝም ተቃውሞው አላበቃም።

ፕሬዜዳንቱ ባልተለመደ ሁኔታ ከተቃዋሚ ወጣቶች ጋር በኦንላይን (X) ምንም አይነት ገደብ የሌለው ግልጽ ሕዝባዊ ውይይት አድርገው ነበር ፤ ያም ቢሆን ሕዝባዊ ጥያቄውን አላስቆመውም።

ፕሬዜዳንቱ በሙስና የተዘፈቁ ሚኒስትሮችን ጠራርገው እንዲያባርሩና ካቢኔውን እንዲበትኑ ጥሪ ሲቀርብ ነበር።

ይህን ተከትሎ ዛሬ ፕሬዜዳንቱ ካቢኔያቸውን በትነዋል።  " የሕዝቤን ድምጽ በመስማት ነው እርምጃውን የወሰድኩት " ብለዋል።

#Kenya
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል። ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል። " አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።…
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።

በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤትም የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ ላይ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

ሕዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ካቢኒያቸውን መበተናቸው ይታወሳል።

#DW
#Kenya

@tikvahethiopia