#Kenya

የኬንያ ፖሊስ 41 ኢትዮጵያውያንን ናይሮቢ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።

ግለሰቦቹ ወደ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች አገራት ለመዘዋወር በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ቀናት ያህል ሲጠባበቁ ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም መያዛቸውን ገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑን በሕገ ወጥ መንገድ ሊያዘዋውሩ ነበሩ የተባሉ ሁለት አዘዋዋሪዎችም በዚሁ አጋጣሚ የተያዙ ሲሆን አንደኛው #ኢትዮጵያዊ መሆኑም ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው እነዚህ የሕገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች በርካታ ዝውውሮች ጀርባ እንዳሉበት ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ በዚህ ሳምንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ወደ ኬንያ እንዴት እንደገቡ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት በእስር እንዲቆዩ መታዘዙን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia