TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Kenya

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል።

ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።

ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤ ይህንንም ተቀብዬ በሕጉ ላይ አልፈርምም፣ ስለዚህም ቀሪ ይሆናል። ሕዝቡ ፍላጎቱን አሳውቋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሕዝቡ ረቂቅ ሕጉን እንደማይፈልገው ገልጿል ያሉት ሩቶ " እኔም በዚህ ተስማምቻለሁ " በማለት ነው በሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ በይፋ ያሳወቁት።

ከሰሞኑን በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ ነበር። ትላንትም ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባት ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። #BBC

@tikvahethiopia