TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#TikTok #Kenya

በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ሀገሪቱ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

ስምምነቱ የተደረሰው " ቲክቶክ ያልተገቡ ቪዲዮዎችን ያሰራጫል " በሚል እንዲታገድ ከአንድ ግለሰብ ለሀገሪቱ ፓርላማ ከቀናት በፊት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡

የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያው ኩባንያ ቲክቶክ፣ በመድረኩ ላይ የሚወጡትን ቪዲዮዎች መቆጣጠርን በተመለከተ ከኬንያ ጋር በጋራ ይሠራል ሲል የፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት አመልክቷል።

ይህን በተመለከተም ከኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾ ዚ ችው ጋር መነጋገራቸውን ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት፣ " ያልተገቡ ናቸው " የሚባሉ ቪዲዮች ከመድረኩ እንደሚወገዱ ታውቋል።

በአፍሪካ በቲክቶክ ላይ የሚወጡትን የቪዲዮዎች ይዘት በተመለከተ ቁጥጥር ለማድረግ ኩባንያው በኬንያ ቢሮ እንደሚከፍት ዋና ሥራ አስፈጽሚው ሾ ዚ ችው ይፋ ማድረጋቸውም ታውቋል።

ቲክቶክ ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፤ ህዝቡንም እያሳሳተ ነው በሚል ቲክቶክ እንዲታገድ አዛለች። እግዱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በተመሳሳይ ቴሌግራምም እንዲታገድ ውሳኔ ከተሰጠባቸው መተግበሪያዎች አንዱ ነው።

ሶማሊያ አሸባሪ ድርጅቶችና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውሏል በሚል ነው እንዲታገዱ ያዘዘችው።

@tikvahethiopia