TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል። ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል። " አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።…
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።

በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤትም የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ ላይ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

ሕዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ካቢኒያቸውን መበተናቸው ይታወሳል።

#DW
#Kenya

@tikvahethiopia