TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስፖርት📌 በ2010 ሳይጠናቀቅ ወደ 2011 የተሻገረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በዛሬው እለት ቀጥሎ ተካሂዷል። በዛሬው እለትም #በሀዋሳ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና መካከል ቀጥሎ ተካሂዷል። በዛሬው እለት የተደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡና ጨዋታም በመደበኛ ሰዓት ያለምንም ግብ 0ለ0 መጠናቀቁን ተከትሎ በመለያ ምት አሸናፊው ተለይቷል። በዚሀም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን በመለያ ምት 7ለ6 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችሏል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 23 እስከ 25 #በሀዋሳ ከተማ ይደረጋል። ጉባኤው «በልማታዊ ዴሞክራሲ ማዕቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴያችንን በማስቀጠል የኢትዮጵያን ሕዳሴ እናረጋግጥ» በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለአራት ቀናት የሚቆየው የደኢህዴን 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት #በሀዋሳ ከተማ ጀምሯል፡፡ጉባዔው ከሌሎች ጊዜ በተለየ ሁኔታ በክብር የሚሰናበቱ አመራሮች እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የህገ ደንብ፣ #አርማና #ስያሜ ለውጥን የሚመለከቱ ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡ በ10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ አዳዲስ አመራሮች ወደ ድርጅቱ የመሪነት እርከን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል⬇️

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ከማሳደግ ውጪ ሌላ #አማራጭ እንደሌለ የደኢህዴን ሊቀ መንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል ገለፁ።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 10ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ #መጠናቀቅን ተከትሎ ለጉባኤተኛው የማጠቃለያ መልእክት አስተላልፈዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት በማጠቃለያ ንግግራቸው፥ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን ገልፀው፤ የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት አንዳለባቸው ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ለውጥ #ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ሊቀመንበሯ ገልፀዋል።

እነዚህ ሀይሎች 10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ እንዳይሳካም ሲንቀሳቀሱ ነበር ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት፤ ከሀዋሳ ውጪ በህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር ገንዘብ ተመድቦላቸው #ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ከክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በተሰራ ስራ ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል።

የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ይህንን በመገንዘብ እነዚህን የጥፋት ሀይሎች በንቃት መጠበቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ካማሳደግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ያሉት ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት፥ ከዚህ ውጨ ያለው አማራጭ #የጥፋት አማራጭ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ስለዚህ የለውጥ ጉዞውን በማሳከት ሂደት የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና የጉባኤተኛው ሚና አጅግ የላቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከነገ ጀምሮ #በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ እንዲሁም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ርብርብ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የደኢህዴን ጉባዔተኞች ልክ በደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን የነቃ ተሳትፎ፣ ዴሞክራሲያዊ ሂደትና ሰላማዊ ሁኔታን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት አክለውም፥ 10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በዚህ መልኩ የተሳካ ሆኖ በመጠናቀቁም እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን የሀዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ዞን እንዲሁም የልግ ባለሀብቶች ላደረጉልት አቀባበል እንዲሁም የኢህአዴግ ጉባዔን ለማስተናገድ እያደረጉ ላለው ዝግጅት ለአመራሩ እና ለህዝቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነገው እለት #በሀዋሳ ከተማ በሚጀመረው11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚጠበቁ ጉዳዮች፦

▪️በነሐሴ ወር 2007 በመቀሌ ከተማ ተደርጎ በነበረው 10ኛ የኢህአዴግ ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችን መሠረት በማድረግ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት ቀርበው ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያሳይ እና ለ12ተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚሆን ሰነድ እንደሚያዘጋጅ ይጠበቃል፡፡

▪️ሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲዎችና ድርጅቶች በቅርቡ ባካሄዷቸው ጉባኤዎች የመረጧቸውን አዳዲስ የማዕከላዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎቻቸውን በዚህ ጉባኤ በማሳተፍ አዲስ የኢህአዴግ ምክር ቤት ይመሠርታሉ፡፡

▪️ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ በጥልቀት ይገመገማል፤ ለውጡን ለማስቀጠል አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ፤ የቀጣይ አቅጣጫዎች ይመላከታሉ፡፡

▪️ባለፈው መጋቢት ወር ጥልቅ ተሐድሶውን ተከትሎ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና በተደረገውን የአመራር ለውጥ የተሠሩ ተግባራት ይገመገማሉ፡፡

▪️አዲስ የኢህአዴግ ምክር ቤት መመሥረቱን ተከትሎ የድርጅቱን ሊቀ-መንበርና ምክትል ሊቀ-መንበር #ይመረጣል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከአራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች የተወከሉ ከእያንዳንዳቸው 250 በአጠቃላይ 1000 በቀጥታ በምርጫውና በውሳኔዎች ዙርያ በድምጽ የሚሳተፉ ይሆናሉ፡፡

በልዩ ሁኔታ የ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ተሳታፊዎች በታዛቢነት የሚገኙ ግን ድምጽ (የማይሰጡ ተሳታፊዎች፡-

-ሴቶችና ወጣቶች
-አጋር ድርጅቶች
-የተለያዮ የኅብረተሰብ ክፍሎች
-ማኅበራት
-ፌዴሬሽኖች
-ዩኒቨርሲቲዎች
-የፌዴራል ተቋማት ኃላፊዎች
-ልማታዊ ባለሀብቶች

የ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ የሚሳተፉ፦

• የሠራዊት አመራሮች
• አርቲስቶች
• ስፖርተኞች
• ታዋቂ ግለሰቦች
• ተፎካከሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጥቅሉ አንድ ሺህ 900 ተሳታፊዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ - ሀዋሳ⬇️

11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የማጠቃለያ ስነ ስርዓት #በሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገሪቱን #ሰላም ለማስጠቅ ከመንግስት ጐን እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ በንግግራቸው፥ 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የማያሰሩ ከሆነ እንዲሻሻሉ አቅጣጫ እንደተቀመጠ አስታውቀዋል።

#የምርጫ_ኮሚሽንና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአመራር፣ በቴክኖሎጂና በተለያዩ መንገዶች እራሳቸውን #እንዲያሻሽሉ ጉባዔው መወሰኑንም ተናግረዋል።

በሀገሪቱ በቀጣይ የሚካሄደው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ገለልተኛ እንዲሆን በሀዋሳ ለሶስት ቀናት የተካሄደው ጉባዔ ውሳኔ ማሳለፉን ነው ሊቀመንበሩ ያስታወቁት።

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ በአዲስ ጉልበት አዲስ ሀይል #በወጣቱ እየተደራጀ መሆኑን የገለፁት ዶክተር አብይ፥ #ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከወዲሁ በመሰባሰብ ጠንካራ #አማራጭ ፓርቲ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ሊቀመንበሩ፥ ፓርቲያቸው ለተፎካካሪ ፓርቲዎች መሻሻል አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት መዘጋጀቱን የገለፁ ሲሆን፥ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን መሸነፍም እንዳለ በመገንዘብ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ኢትዮጵያን ለማገልገልና የተሻለ ለመሆን በአዲስ አመራር፣ በወጣቶች እና በምሁራን እራሳቸውን ማደረጃት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።

ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት እውነተኛ፣ ትክክለኛና ጠቃሚ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የሚያደርሱ መገናኛ ብዙሃን ናቸው ያሉት ሊቀመንበሩ፥ መገናኛ ብዙሃን #የኢትዮጵያዊ ማንነትን ባልጣሰ መልኩ ሊንቀሳቀሱ ይገባል ብለዋል።

ጉባዔው ለግብርና፣ መስኖ ልማት እና ኢንቨስትመንት ትኩረት በመስጠት የስራ አጥነትነትን ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ እንዲሰራ አቅጣጫ እንዳስቀመጠም ተናግረዋል።

የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ቱሪዝም መሆኑን የተናገሩት ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያውያን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን እራሳቸውን በተለያዩ መንገዶች ማዘጋጀት እንደሚገባቸውና አፍሪካውያን ወንድሞቻቸውን ለመቀበል እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

የሀገሪቱ ከተሞች ያደጉና ድህነትን የቀነሱ እንዲሆኑ በቀጣይ በትኩረት ለመስራት አቅጣጫ እንተጠቀመጠ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በተለይ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ ፅዱና ውብ ለማድረግ እንደሚሰራ የተናገሩ ሲሆን፥ ለዚህም የከተማዋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ከመንግስት ጎን እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢህአዴግ ውስጣዊ አንድነት በማጠናከር #የኢትዮጵያውያን አንድነት ለመጠበቅ ይሰራልም ብለዋል።

ብልሹ አሰራር ከባህላችን ጋር የሚቀራን ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚከፈለው ልክ ሳይሆን ከሚከፈለው በላይ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ እና አዲስ አበባ!!

ድምፃዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን በአዲስ አበባ ስታዲየም #በነፃ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰምቷል። ለአዲስ አበባው ኮንሰርት ምንም አይነት ክፍያ እንደማይቀበል የተነገረ ሲሆን ለሙዚቃው ዝግጅት ከአዘጋጆቹ በተጨማሪ የተወሰነውን ወጪ እራሱ ይሸፍናልም ተብሏል። ህዝቡም ኮንሰርቱን በነፃ እንደሚታደምበት ነው የተገለፀው። ከአዲስ አበባው በአይነቱ የተለየ የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ድምፃዊው #በሀዋሳ ከተማ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ እቅድ እንዳለው ለመስማት ተችሏል። የሙዚቃ ዝግጅቶቹ መቼ ይካሄዳሉ?? የሚለው ግን የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ ኢትዮፒካሊንክ የሬድዮ ዝግጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የድርጅትና የመንግስት የስራ አፈጻጸም እንዲሁም በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ላይ ሲሆን አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምም ይገመግማል። በስብሰባው በመስከረም ወር #በሀዋሳ በተካሄደው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአጋር ፓርቲዎች ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሶሪያ ስደተኞች~ሃዋሳ‼️

በአሁኑ ወቅት #በሀዋሳ_ከተማ በልመና ስራ ተሰማርተው የሚገኙ ጥቂት የሶሪያ ዜጎች መኖራቸውን የኢሚግሬሽን የዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቀቀ። በዚህም መሰረት ወጣት አስፋው ተክሌን በሠብሳቢነት እንዲሁም ወጣት አክሊሉ ታደሰን በምክትል ሰብሳቢነት መምረጡን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvagethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 21/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው።
.
.
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሂደዋል።
.
.
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል።
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታውቀዋል።
.
.
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው ተብሏል።
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡
.
.
#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
.
.
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።
.
.
ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
.
.
ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቋል።
.
.
ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታውቋል። በግጭቱ የ2 ሰው ህይወት አልፏል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
.
.
#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቅቋል።
.
.
አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መስርቷል።
.
.
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል።
.
.
በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታውቀዋል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
.
.
#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ፣ etv፣ fbc፣ VOA፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አብመድ
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

በዛሬው ዕለት #የታክስ_ንቅናቄው አንድ አካል የሆነ ግማሽ ማራቶን የታላቁ ሩጫ #በሀዋሳ ከተማ ተካሄዷል፡፡

ፎቶ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ ክልል

በደቡብ ክልል እየተነሱ ያሉ #የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በተመለከተ ሳይንሳዊ ጥናት ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ጥናቱን የሚያከናውነው ፎረም አስታወቀ።

ላለፉት ሶስት ወራት ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ፎረሙ፤ በቀጣዮቹ አስር ቀናት መረጃ ሰብሳቢዎች ወደ ስራ ይገባሉ ብሏል።

ፎረሙ ጥናቱን ከአራት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለክልሉ መንግስት እንደሚያቀርብም ነው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው።

ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እና የሙያ መስኮች የተውጣጣ 20 አባላት ያለው የጥናት ቡድን፤ የጥናቱን አካሄድ በተለመከተ ንድፈ ሀሳብ አዘጋጅቷል። አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለማየት መሞከሩንም አንስቷል።

በዛሬው እለትም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተመለመሉ 22 የጥናቱ ሱፐርቫይዘሮች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት አድርጓል።

በቀጣዩ ሳምንትም #በሀዋሳ ከ150 የመረጃ ሰብሳቢዎች ጋር እንደሚመክር ነው በመግለጫው የተነሳው።

የጥናቱ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅም ከሰው ሀይል ባሻገር #የሶፍትዌር ዝግጅት መደረጉን ፎረሙ የጥናትን መርህ እና አካሄድ ጠንቅቀው በሚያውቁ እስከ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ባላቸው የክልሉ ተወላጆች የሚደረገውን ጥናት ለክልሉ መንግስት እንደ ግብአት አቀርባለሁ ብሏል።

የጥናቱ ውጤት ውሳኔ ሰጪ ሳይሆን እንደ ምክረ ሀሳብ የሚቀርብ መሆኑንም ፎረሙ በመግለጫው አንስቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቀል...

#በሀዋሳ_ከተማ ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር በሚል ሲደረግ የነበረው ሴቶች ብቻ የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቀዋል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ገብተዋል!

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ወደተቋማቸው በሰላም ገብተዋል። በተመሳሳይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ወደተቋማቸው በሰላም ገብተዋል። የወልቂጤው ልዕኩ በጉዞ ላይ ይገኛል።

ቅዳሜ እና እሁድ #በሀዋሳ_ዩኒቨርስቲ #የStopHateSpeech መድረክ መካሄዱ አይዘነጋም--ፎቶዎች እና ተያያዥ መረጃዎችን ቆየት ብዬ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወንደሰን አስክሬን ወደሀዋሳ እያመራ ነው...

ነቀምት ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በነቀምቴ ከተማ በተነሳ ድንገተኛ #ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል። ወንድወሰን ዮሐንስ ትውልድ እና እድገቱ #በሀዋሳ ኮረም ሰፈር አካባቢ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የእድሜ እርከኖች ከተጫወተ በኋላ በስልጤ ወራቤ እና ኢትዮጵያ ውሀ ስራ (ኢኮስኮ) ሲጫወት ቆይቶ አሁን ወደሚገኝበት ነቀምት ከተማ አምርቶ እየተጫወተ የሚገኝ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ነበር። የተጫዋቹ አስከሬን ወደ ሀዋሳ እያመራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በነገው ዕለትም በትውልድ ከተማው ሥርዓተ ቀብሩ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

Via SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮማንድ_ፖስት

ሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓም #በሲዳማ_ዞን እና #በሀዋሳ ከተማ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መደበኛውን የህግ ማስከበር ስርዓት ተከትሎ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን አስመልክቶ ዛሬ በሀዋሳ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CM-07-31
#Hawassa

ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ የሚከሰተዉን የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት መቋረጥ ተከትሎ በርካቶች ስራችን ላይ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እየተፈጠረ ላለው ችግር ኢትዮ ቴሌኮም አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሲያስተካክለዉ ቢታይም አገልግሎቱ 24 ሰአት እንኳን ሳይቆይ መልሶ ሲቋረጥ ይስተዋላል።

በዚህም ተገልጋዮች ላልተገባ ወጭ እና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የደረሱትን ቅሬታዎች ይዞ የሚመለከተውን አካል አነጋግሯል።

በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በኢትዮ ቴሎኮም ፤ የደቡብ ሪጅን ዳይሬክተሩ አቶ ጁነዲን አብዱልቃድር " ችግሩ መኖሩ ግልጽ ነው " በማለት አሁን ላይ እንዲህ ያለው የስርቆት ሁኔታ በሁሉም አካባቢ አሳሳቢ መሆኑን ያነሳሉ።

አቶ ጁነዲን አክለዉም ፤ ኬብሉ ከውጭ በውድ ገንዘብ ተገዝቶ  ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ማህበረሰቡ ከፖሊስ ጋር ተጣምሮ ሊጠብቀው ይገባል ብለዋል።

በዚህ በኩል በሀዋሳም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ትልቅ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለፁት ደግሞ በሪጅኑ የህግ ጉዳይ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተድላመድህን ቀለመወርቅ ፤ " እስካሁን በተደረጉ እንቅስቃሴዎችም በርካታ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ስርቆቱ #በሀዋሳ እና #ሻሸመኔ ከፍ ያለ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ተድላመድህን ካለፈዉ ሀምሌ 1 እስከ ታህሳስ 30 እንኳን በሀዋሳ ከተማ ብቻ 4 መዝገብ ላይ ውሳኔ ተሰጥቶ ከስድስት እስከ ሁለት አመት እስራት መፈረዱን አንስተዋል።

በሀገር ደረጃ  የመሰረተልማት እንቅስቃሴዎችን ለመጠበቅ ታስቦ የወጣዉን 464/67 የተባለ አዋጅ መሰረት አድርጎ ያለመክሰስ ያለመመርመርና ውሳኔ አለመስጠት ችግር ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል።

የሚሰጡ ውሳኔዎች እስከ 20 አመት የሚዘልቁ ቢሆኑም ያ እየሆነ አለመሆኑን የሚገልጹት ስራ አስኪያጁ " በዚህ ቻሌንጅ ውስጥ ሆነንም ቢሆን አስተማሪ የሆኑ ውሳኔዎች እንዲሰጡ እየሰራን ነው "  ብለዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia