TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ - ሀዋሳ⬇️

11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የማጠቃለያ ስነ ስርዓት #በሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገሪቱን #ሰላም ለማስጠቅ ከመንግስት ጐን እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ በንግግራቸው፥ 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የማያሰሩ ከሆነ እንዲሻሻሉ አቅጣጫ እንደተቀመጠ አስታውቀዋል።

#የምርጫ_ኮሚሽንና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአመራር፣ በቴክኖሎጂና በተለያዩ መንገዶች እራሳቸውን #እንዲያሻሽሉ ጉባዔው መወሰኑንም ተናግረዋል።

በሀገሪቱ በቀጣይ የሚካሄደው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ገለልተኛ እንዲሆን በሀዋሳ ለሶስት ቀናት የተካሄደው ጉባዔ ውሳኔ ማሳለፉን ነው ሊቀመንበሩ ያስታወቁት።

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ በአዲስ ጉልበት አዲስ ሀይል #በወጣቱ እየተደራጀ መሆኑን የገለፁት ዶክተር አብይ፥ #ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከወዲሁ በመሰባሰብ ጠንካራ #አማራጭ ፓርቲ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ሊቀመንበሩ፥ ፓርቲያቸው ለተፎካካሪ ፓርቲዎች መሻሻል አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት መዘጋጀቱን የገለፁ ሲሆን፥ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን መሸነፍም እንዳለ በመገንዘብ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ኢትዮጵያን ለማገልገልና የተሻለ ለመሆን በአዲስ አመራር፣ በወጣቶች እና በምሁራን እራሳቸውን ማደረጃት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።

ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት እውነተኛ፣ ትክክለኛና ጠቃሚ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የሚያደርሱ መገናኛ ብዙሃን ናቸው ያሉት ሊቀመንበሩ፥ መገናኛ ብዙሃን #የኢትዮጵያዊ ማንነትን ባልጣሰ መልኩ ሊንቀሳቀሱ ይገባል ብለዋል።

ጉባዔው ለግብርና፣ መስኖ ልማት እና ኢንቨስትመንት ትኩረት በመስጠት የስራ አጥነትነትን ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ እንዲሰራ አቅጣጫ እንዳስቀመጠም ተናግረዋል።

የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ቱሪዝም መሆኑን የተናገሩት ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያውያን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን እራሳቸውን በተለያዩ መንገዶች ማዘጋጀት እንደሚገባቸውና አፍሪካውያን ወንድሞቻቸውን ለመቀበል እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

የሀገሪቱ ከተሞች ያደጉና ድህነትን የቀነሱ እንዲሆኑ በቀጣይ በትኩረት ለመስራት አቅጣጫ እንተጠቀመጠ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በተለይ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ ፅዱና ውብ ለማድረግ እንደሚሰራ የተናገሩ ሲሆን፥ ለዚህም የከተማዋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ከመንግስት ጎን እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢህአዴግ ውስጣዊ አንድነት በማጠናከር #የኢትዮጵያውያን አንድነት ለመጠበቅ ይሰራልም ብለዋል።

ብልሹ አሰራር ከባህላችን ጋር የሚቀራን ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚከፈለው ልክ ሳይሆን ከሚከፈለው በላይ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia