TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ አክሱም ከተማ ሲገቡ የትግራይ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአክሱም ሀውልትንም ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚስትሩ በአክሱም ቆይታቸው በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየተሰጠ ነው...

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ ነው። የፈተናውን ሂደት በጣምራ የሚመሩት የትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ ለፈተናው አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ስድስት የአቼቶ ምርቶች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡ ባለስልጣኑም ምርቶቹንም ሸማቹ ህብረተሰብ እንዳይጠቀም አስጠንቅቋል፡፡የአምራች ድርጅቶቻቸው አድራሻና ምንጫቸው የማይታወቁ የምግብ ምርቶች ገበያ ላይ እየዋለ መሆኑን በተደረገው የገበያ ቅኝት ማግኘቱንም አስታዉቋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ድርጅቶች ተመርተው ወደ ገበያ በተሰራጩ ምርቶች ላይ በተደረገ የገበያ ቅኝት በብሔራዊ ደረጃ የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ፤ ምንም ዓይነት ገላጭ ጽሁፍ የሌላቸው፤ የአምራች አድራሻ እና መለያ ቁጥር የሌላቸው የአቼቶ ምርቶች ገበያ ላይ መገኘታቸው በተደረገው የቁጥጥር ስራ የተገኘ ሲሆን ባለስልጣኑ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ አስታዉቋል፡፡

Real Aceto (ሪል አቼቶ)፤ Munit Aceto (ሙኒት አቼቶ)፤ Herme Aceto (ሐርሚ አቼቶ)፤(ሳሚ አቼቶ)፤ Sname Trading Aceto (ሰናሚ አቼቶ)እና Saron Aceto (ሳሮን አቼቶ) ናቸዉ እርምጃ የተወሰደባቸዉ፡፡በመሆኑም ህብረተሰቡ እነዚህን የአቼቶ ምርቶችን እንዳይጠቀማቸው እያሳሰበ ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፤ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ጠይቋል፡፡በተጨማሪም የክልል ተቆጣጣሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የቁጥጥር አካላት ምርቶቹን ከገበያ ላይ በአፋጣኝ የመሰብሰብ ስራውን እንዲሰሩ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም...

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአክሱም ቆይታቸው በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ከመወያየታቸው በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወሰኑ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል፡፡ ምክር ቤቱ በ8 ተቃውሞ እና በ4 ድምፀ ተዓቅቦ ነው በአብላጫ ድምፅ የወሰነው።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው የሕዝብና የቤት ቆጠራው ዳግም ይራዘም አይራዘም በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክርክር ካደረገበት በኋላ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በ24 ተቃውሞ እና በ2 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል። ምክር ቤቶቹ ባሳለፉት ውሳኔ ላይ በጋራ ይመክሩበታል ተብሎ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ትንባሆና ሺሻ በሚያስጨሱ የአልኮል መጠጥ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ተቆጣጣሪ አካላት እና ከፖሊስ ጋር ባደረገው ክትትል ትንባሆና ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ የአልኮል መጠጥ ቤቶች ላይ ነው እርምጃ ወስጃለሁ ያለው።

በዚህም 30 የአልኮል መጠጥ ምሽት ቤቶች ባለቤትና ሥራ አሥኪያጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ነው የገለፀው።

በዚህ ዓመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ 1112/2011 ሲጋራ እና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን አስመልክቶ ክልከላ አስቀምጧል።

በክልከላውም እንደ ሆቴል፣ ሬስቶራንት፣ ምግብ ቤት፣ መጠጥ ቤት እና የምሽት ቤት በመሳሰሉ ማንኛውም ድርጅቶች በአስር (10) ሜትር ዙሪያ እንዲጨስ መፍቀድ ያስቀጣል።

በአዋጁ አንቀፅ 5 ደግሞ የሺሻ ምርትን ማምረት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከማቸት፣ ማከፋፈል፣ ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል።

ማንኛውም ሰው ሺሻን ያመረተ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ያከፋፈለ፣ ያከማቸ ወይም የሸጠ እንደሆነ ከ3 ወር እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር 1 ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ተካትቷል፡፡

በመሆኑም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ባደረገው ቁጥጥርና ክትትል ትንባሆና ሺሻ በሚያስጨሱ 30 የአልኮል መጠጥ ምሽት ቤቶች ባለቤትና ስራ አስኪያጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

በቀጣይም አዋጁን በሚጥሱት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ነው ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡

ህብረተሰቡም ድርጊቶቹን ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 8482 ጥቆማ እንዲያደርስ ተጠይቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሁላችን ከተባበርን የማንፈታው ችግር የለም" ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
.
.
ሁሉም ሕብረተሰብ በሚችለው ከተባበረ የማንፈታው ችግር እንደማይኖር የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ የበሪ ሜዳ ሆስቴልና የሴት ተማሪዎች ትምህርት ማዕከል ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ባለሃብቶችና የአካባቢው ሕብረተሰብ ይህንን የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ችግር የሚፈታ ህንፃ ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱ የሚመሰገን ነው።

ዶክተር ደብረጽዮን አያይዘውም በተመሳሳይ መልክ የህዝብን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ሌሎች የልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

በተለይ ትምህርት ላይ የሚደረግ ልማት ለሁሉሞ ቁልፍ ሲሆን የሴት ተማሪዎችን በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ችግር መፍታትና ማስተማር ደግሞ ሁሉንም ሕብረተሰብ ማስተማር በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዋናው ነገር ከዚህ ሆስቴልና የትምህርት ማዕከል መገንባት በስተጀርባ ያለው የእንችላለን አስተሳብ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ደብረጽዮን ሌሎች በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ስራዎችን እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል።

ማዕከሉ የተሰራው በበጎ አድራጊዎች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ 160 ሴት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ሆነዋል።

Via Tigray Communication
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቆሼ...

"ፀግሽ ረጲ ቆሻሻ ማከማቻ በተለምዶው "ቆሼ" የሚባለው ከእንደገና ፈርሷል። የእሳትና ድንገተኛ አደጋም ቦታው ይገኛል። በአሁን ሰዓት የፈረሰውን የሚያነሳ እስካቫተር እየተጠበቀ ነው። የጉዳቱ መጠን ገና አልታወቀም።" ሳሚ ከአ/አ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና በቆሼ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፡፡ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዳግም በተከሰተ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ እስካሁን የአንድ ሰው አስክሬን መገኝቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለአሀዱ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

Via Ahadu Radio
ፎቶ ፦ ሳሚ/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም...

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። ነዋሪዎቹ ጠ/ሚሩ ጥያቄያቸውን ተቀብለው ሐውልቱን በማደስ ዙሪያ ለመነጋገር መምጣታቸውን አድንቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጠ/ሚሩ በበጀት ምደባ፣ በውኃ እጥረት፣ በመሠረተ ልማት ጥያቄዎችና በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከነዋሪዎቹ ጋር ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በዛሬው ዕለት በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።

አደጋውን ተከትሎ በአካባቢው በተደረገ ቁፋሮ አንድ የ70 ዓመት አዛውንት በህይወት ማውጣት ቢቻልም አለርት ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

አደጋው የደረሰው ቆሻሻ ከተጠራቀመበት አካባቢ ላይ ከተሰሩ የፕላስቲክ ቤቶች እና መንገድ ዳር በመሆኑ እስካሁን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።

አሁን ላይም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቆሻሻው በተደረመሰበት አካባቢ የሰው ህይወት ለማዳን በኤክስካቫተር የታገዘ ቁፋሮ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከሁለት ዓመት በፊት በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

Via #fbc
Photo: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከASTU...

"ፀግሽ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የተማሩ ወጣቶችን በመስኖ ልማት ለማሰማራት ከኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ የተማሩ ወጣቶች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።" #ፋንታሁን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ማሊ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በሃገሪቱ ዶጎን የሚባሉ የጎሳ አባላት መኖሪያ በሆነች መንደር በተፈጸመ ጥቃት ከ100 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በመካከለኛ ማሊ ሶብሌ ኮው በምትባል አንስተኛ መንደር ውስጥ መሆኑን 'አርኤፍአይ' የተሰኘው የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአከባቢው ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ የሟቾች አስክሬን እንዲቃጠል ተደርጓል። ተጨማሪ የሟቾች እስክሬን እየተፈለገ መሆኑን የአከባቢው ባለስልጣናት ጨምረው ተናግረዋል።

ከቅርብ ወራት ወዲህ በማሊ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ከዚህ ቀደም የነበሩት ጥቃቶች ብሄረ ተኮር አልያም በጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ናቸው።

በእዚሁ አከባቢ የዶንጎ ጎሳ አባላት በሆኑ አዳኞች እና የፉላኒ ጎሳ አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት የተለመደ ነው።

ከሶስት ወራት በፊት 130 የሚሆኑ የፉላኒ ጎሳ አባላት የዶንጎ አዳኞችን ልብስ በለበሱ ሰዎች በአንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ ተገድለው ነበር።

በእነዚህ ሁለት ጎሳዎች መካከል ግጭት እየተበራከተ የመጣው ከአራት ዓመታት በፊት ጸንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች በቀጠናው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ወዲህ ነው።

Via #bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራል ፖሊስ ለነጌታቸው አሰፋ መጥሪያ ሊያደርሳቸው እንዳልቻለ ለፍርድ ቤት አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ትግራይ ክልል ለሚገኘው ቅርንጫፉ የፍርድ ቤት ትእዛዙን በፋክስ ቢልክም በመጥሪያው ላይ የተከሳሾቹ የመኖሪያ አድራሻ ባለመጠቀሱ ለማድረስ አለመቻሉን አስታውቋል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት ግንቦት 16/2011ዓ.ም በነጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ ላይ ሰጥቶ የነበረውን ትዕእዛዝ ውጤት ለመከታተል ነበር ለዛሬ ቀጠሮ የያዘው፡፡

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን ትክክለኛ አድራሻ የያዘ መጥሪያ በድጋሚ ተዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱም የትግራይ ክልል ፖሊስ እንዲተባበር የሚያስችል ትእዛዝ እንዲፃፍ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በፃፈው ማመልከቻ ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግን የተከሳሾቹ አድራሻ ለምን በክስ ማመልከቻው ላይ አልተጠቀሰም በማለት ጠይቋል፡፡

ፌዴራል አቃቤ ህግም ትግራይ ክልል ከማለት ውጪ የተከሳሾችን ትክክለኛ አድራሻ እንደማያውቅ ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎ አቃቤ ህግ ለተከሳሾቹ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ክሳቸው በሌሉበት እንዲታይ ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ በድጋሚ በትክክለኛ አድራሻ መጥሪያ ይላክልቸው ወይንስ በጋዜጣ ይጠሩ የሚለው ላይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 12/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

በተጨማሪም ችሎቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ማንነታቸው ሳይገለፅ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ይደረግልኝ በማለት ባቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 12/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 5ተኛው የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ በአንድ ዓመት ተራዘመ። ዛሬ የተካሄደው 5 ተኛው የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ልዩ የጋራ ስብሰባ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ወሰኗል። ሁለቱም ምክር ቤቶች ከዚህ ቀደም ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስነው ነበር። ሆኖም ዛሬ የጋራው ምክር ቤት ቆጠራው ከአንድ ዓመት በላይ ላልተወሰነ ጊዜ ይራዘም የሚልና ሰላሙ በመሻሻሉ ለ6 ወር ብቻ ይራዘም በሚሉ የመከራከሪያ ሃሳቦች ላይ ከተነጋገረ በኋላ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል።

በስብሰባው ላይ በተካሄደው ውይይት የሰላሙ ሁኔታ መሻሻል ቢያሳይም ቆጠራውን ማካሄድ የሚያስችል አለመሆኑ፣ በርካቶች በተፈናቀሉበት የቆጠራ ሠራተኞችም ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር በማይችሉበት ሁኔታ ቆጠራውን ማካሄድ አግባብ እንዳልሆነ መነሳቱ ተዘግቧል። ውሳኔው በ30 ተቃውሞ እና በ3 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያለፈው።5ተኛው የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ ሲገፋ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ በአብዲ ቦሩ የፈተና ማእከል የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆነችው ተማሪ አልማዝ ደረሰ ዛሬ ጠዋት 1፡30 ላይ ከወለደች በኋላ ፈተናዋን እዛው በወለደችበት ሆስፒታል ተፈትናለች፡፡

ተማሪዋ ለፈተናዋ ስትዘጋጅ መቆየቷን በመግለፅ በፈተናው እለት ብትወልድም ፈተናውን መፈተን አለብኝ በማለት ጥያቄ አቅርባለች፡፡

ተማሪዋ ያቀረበችው ጥያቄ በሚመለከተው አካል ተቀባይነት በማግኘቱ አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላት በማድረግ ልጇን በተገላገለችበት ካርል ሆስፒታል ፈተናዋን ተፈትናለች፡፡

“የወለድኩበትና የፈተናው እለት መገጣጠሙ አስቸጋሪ ቢሆንም ለፈተናው በቂ ዝግጅት በማድረጌ እንዲያልፈኝ አልፈለኩም”ብላለች።

የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት የሚመለከታቸው አካላትም ወጣቷ ወልዳ በተኛችበት መቱ ካርል ሪፈራል ሆስፒታል አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላት እንድፈተን ማድረጋቸው እንዳስደሰታት ተናግራለች።

ወጣቷ በሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎችና ለዚሁ ስራ በተመደቡ የፈተና ጣቢያ ሰራተኞች ድጋፍም በሆስፒታሉ ውስጥ ፈተናዎቹን እየወሰደች ትገኛለች።

ምንጭ፡- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ኢሕአዴግ-መራሹ መንግሥት የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ለመሸጥ ሕዝባዊ ይሁንታ የለውም ሲል ተቃውሟል፡፡ ንቅናቄው ዛሬ በአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ከሀገር የሸሸውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አስመልሳለሁ ያሉትን ቃል ሳያከብሩ መንግሥታቸው ሀገሪቱ ያፈራቻቸውን አንጡራ ሃብቶች ለመሸጥ መዘጋጀቱ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጧል፡፡ ይህ አካሄድ ሌዛ ዙር መንግሥታዊ ዝርፊያ መዘጋጀትነ ነው በማለትም አስጠንቅቋል፡፡ መንግሥት ስር ነቀል የኢኮኖሚ ለውጥ ማድረግ የሚችለው ከቀጣዩ ምርጫ በኋላ እንደሆነም ጠቁሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የተጀመረው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የመጀመሪያው ቀን መርሀ ግብር በሰላም መጠናቀቁን ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴሌግራም ተቋርጧል...

#በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ #ከተሞች የሚገኙ የTIKVAH-ETH አባላት የቴሌግራም አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው ገልፀዋል። በምን ምክንያት የቴሌግራም አገልግሎት ሊቋረጥ እንደቻለ ለማጣራት እንሞክራለን።

እንደ አማራጭ የቤተሰባችን አባላት #Psiphon ይህን መተግበሪያ በመጠቀም ቴሌግራምን በቀጥታ መጠቀም ትችላላችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia