#update 5ተኛው የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ በአንድ ዓመት ተራዘመ። ዛሬ የተካሄደው 5 ተኛው የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ልዩ የጋራ ስብሰባ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ወሰኗል። ሁለቱም ምክር ቤቶች ከዚህ ቀደም ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስነው ነበር። ሆኖም ዛሬ የጋራው ምክር ቤት ቆጠራው ከአንድ ዓመት በላይ ላልተወሰነ ጊዜ ይራዘም የሚልና ሰላሙ በመሻሻሉ ለ6 ወር ብቻ ይራዘም በሚሉ የመከራከሪያ ሃሳቦች ላይ ከተነጋገረ በኋላ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል።

በስብሰባው ላይ በተካሄደው ውይይት የሰላሙ ሁኔታ መሻሻል ቢያሳይም ቆጠራውን ማካሄድ የሚያስችል አለመሆኑ፣ በርካቶች በተፈናቀሉበት የቆጠራ ሠራተኞችም ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር በማይችሉበት ሁኔታ ቆጠራውን ማካሄድ አግባብ እንዳልሆነ መነሳቱ ተዘግቧል። ውሳኔው በ30 ተቃውሞ እና በ3 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያለፈው።5ተኛው የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ ሲገፋ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia