#update ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ማሊ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በሃገሪቱ ዶጎን የሚባሉ የጎሳ አባላት መኖሪያ በሆነች መንደር በተፈጸመ ጥቃት ከ100 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በመካከለኛ ማሊ ሶብሌ ኮው በምትባል አንስተኛ መንደር ውስጥ መሆኑን 'አርኤፍአይ' የተሰኘው የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአከባቢው ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ የሟቾች አስክሬን እንዲቃጠል ተደርጓል። ተጨማሪ የሟቾች እስክሬን እየተፈለገ መሆኑን የአከባቢው ባለስልጣናት ጨምረው ተናግረዋል።

ከቅርብ ወራት ወዲህ በማሊ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ከዚህ ቀደም የነበሩት ጥቃቶች ብሄረ ተኮር አልያም በጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ናቸው።

በእዚሁ አከባቢ የዶንጎ ጎሳ አባላት በሆኑ አዳኞች እና የፉላኒ ጎሳ አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት የተለመደ ነው።

ከሶስት ወራት በፊት 130 የሚሆኑ የፉላኒ ጎሳ አባላት የዶንጎ አዳኞችን ልብስ በለበሱ ሰዎች በአንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ ተገድለው ነበር።

በእነዚህ ሁለት ጎሳዎች መካከል ግጭት እየተበራከተ የመጣው ከአራት ዓመታት በፊት ጸንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች በቀጠናው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ወዲህ ነው።

Via #bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia