TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#IOM

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባደረገው ቅኝት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከ131 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ አመለከተ።

ድርጅቱ እንዳለው ተፈናቃዮቹ በትግራይና ተጎራባች በሆኑት የአፋር እንዲሁም የአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 39 በሚሆኑ ተደራሽ ስፍራዎች ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

ይህ የተፈናቃዮች መረጃ የተሰበሰበው አዲስ በሆነው "ዲስፕሌስመንት ትራኪን ማትሪከስ" በተባለ ዘዴ ሲሆን በዚህም የሕዝብ ቁጥርን በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብና የሰዎችን ተጋላጭነት እንዲሁም የተፈናቃዮችን ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ መረጃን በመሰብሰብ የሚተነትን ነው።

አይኦኤም እንዳለው በዚህ የቅኝት ተግባሩ 30,383 ተፈናቀሉ ቤተሰቦችን መለየት ችሏል።

ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ ፣ ምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶችን እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት "ይህ መረጃ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት የተፈናቀሉትን አጠቃላይ ሰዎች የሚያመለክት አይደለም። ከዚያ ይልቅ መረጃውን ለማሰባሰብ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች በአገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ብቻ የሚወክል ነው" ማለቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Afar #Tigray #UNHCR #IOM

UNHCR ከትግራይ ክልል ውስጥ #ለአደጋ_ተጋላጭ ናቸው ያላቸውን 55 ኤርትራዊያን ስደተኞችን በIOM Ethiopia እገዛ ወደ አፋር ክልል ማዛወሩን አስታውቋል።

ወደአፋር ክልል ከተዘዋወሩት ስደተኞች መካከል ከግማሽ በላዩ ህጻናት ናቸው።

UNHCR ስደተኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለወራት ከኖሩ በኃላ አሁን ላይ ምቹ ወደሆነ መጠለያ እንደሚገቡ እና አስፈላጊውን ሁሉ እርዳታ እንደሚያገኙ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#IOM

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) #የኢትዮጵያ ኃላፊ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ያልተፈቀደ ቃለ መጠይቆችን" አድርገዋል በሚል የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸውን AFP ዘገበ።

ኃላፊዋ ማውሪን አቺየንግ ያልተፈቀደ በተባለው ቃለ መጠይቅ ለህወሓት ወገንተኛ ባሏቸው የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ጎን ገሸሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

ማውሪን አቺየንግ ምንድነው ያሉት?

ባለፈው ሳምንት ማውሪን አቺየንግናና ሌላ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኛ የኢትዮጵያን መንግስት በመደገፍ በርካታ መጣጥፎችን ለሚፅፈው ጄፍ ፒርስ ረዘም ያለ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል።

በቃለ መጠይቁ ላይ እንደሚሰማው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ኃላፊ ማውሪን ጦርነቱ ከተነሳ በኋላ አዲስ አበባ የገቡ የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ባልደረቦቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በመተቸት መሬት ያሉ የድርጅቱ ተወካዮችን አግልለዋል ብለዋል።

ህወሓትን "ቆሻሻ" እና "ጨካኝ" በማለትም ሲናገሩ ይሰማል።

በአንድ ወቅትም ህወሓት ከሳዑዲ አረቢያ የተባረሩ የትግራይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ አሲረዋል በማለትም ሲከሱ ይሰማል።

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩና መውጪያ አጥተው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ ጥያቄ እንደቀረበላቸውና ሩዋንዳም እንዲላኩ የተፈለገው ለሌላ አላማ እንደሆነ ተናግረዋል።

"ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ የተፈለገው የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ ከሩዋንዳ እንዲጀመር" ለማድረግ መሆኑንም ያነሳሉ፤ “እንዲህ ዐይነት ነገር ቆሻሻ ነው” ሲሉ ይደመጣሉ።

ኃላፊዋ በጭራሽ ወደ ትግራይ እንደማይመለሱ ቃል ሲገቡም ይሰማል።

ያንብቡ: https://telegra.ph/AFP-10-12

የመረጃ ባለቤት AFP ነው።

@tikvahethiopia
#IOM

እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ  ስደተኞች ተመዝግበዋል።

ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14 በመቶ ናቸው።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ 200 የነበረው የስደተኞቹ ቁጥር  ያለፈው ማክሰኞ ወደ 1,300 ደርሷል።

ድርጅቱ በሱዳን ድንበር ላይ ለሚደርሱ 700 ያህል የሶስተኛ ሀገር ዜጎችን ለመቀበል የትራንስፖርት እርዳታ በርካታ ኤምባሲዎች ጥያቄዎች  እንዳቀረቡለት ታውቋል።

የአይኦኤም ባለስልጣናት ከድንበር ከተማ መተማ ወደ ጎንደር እና አዲስ አበባ ከተሞች የሚመጡ ስደተኞች መብዛትን ተከትሎ  ትራንስፖርት በማዘጋጀት ላይ ናቸው።

ድርጅቱ የሱዳኑ ግጭት  270,000 የሚደርሱ ሰዎችን ወደ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን ፣ ቻድ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ እንዲሰደዱ ሊያደርግ ይችላል ብሏል።

በሱዳን ወታደሮች እና ታጣቂዎች መካከል የተደረገው ጦርነት ሚያዝያ 15 ቀን 2023 ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎችም በከፍተኛ የውሃ፣ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የነዳጅ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።

በሌላ በኩል፤ ከቀናት በፊት በተፋላሚ ወገኖች ስምምነት የተደረሰበት የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም ለተጨማሪ ቀናት እንዲራዘም የተደረገ ቢሆን አሁንም በሀገሪቱ ግጭት ቀጥሏል።

ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም የተደረገው በሱዳን ጎረቤት አገራት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት፣ በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ / ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
#IOM

" በቅርብ ከደርሱት #አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው " - የተመድ የስደተኞች ድርጅት

ስደተኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

ቅዳሜ የደረሰው አደጋ፣ ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በሚሹ ስደተኞች ላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ በቅርቡ ከደርሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳለው፣ 86 ሰዎችን ይዛ ስትጓዝ የነበረው ጀልባ፣ ከፍተኛ ማዕበል ገጥሟት በሊቢያ ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው " ዙዋካ " ከተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ስትገለበጥ 61 ሰዎች #ሰምጠዋል

ድርርቱ ማዕከላዊው የሜዲትሬንያን ባሕር፣ ለፍልሰተኞች አደገኛ የጉዞ መሥመር መሆኑ ቀጥሏል ብሏል።

#ሊቢያ በጦርነት በመታመስ ላይ ያለች አገር ብትሆንም፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ #ሁከትን እና #ድህነት በመሸሽ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡

የስደተኞች ድርጅቱ እንደሚለው፣ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈርንጆች 2023 ብቻ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በባሕር ላይ #ሕይወታቸውን_አጥተዋል

መረጃው የቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia
#IOM

" እ.ኤ.አ ከ2014 እስከ 2023 ቢያንስ 63,285 ሰዎች ሞተዋል / የገቡበት አይታወቅም " - IOM

እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 63,285 ሰዎች በዓለም ላይ ባሉ ስደተኞች በሚጓዙበት መስመር ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም ጠፍተዋል።

አብዛኞቹ ህይወታቸውን ያጡት ደግሞ በውሃ መስጠም ምክንያት ነው።

እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ሪፖርት መሰረት 28,854 ሰዎች የሞቱት እና የት እንደገቡ ያልታወቀው በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ነው።

ከተመዘገቡት የሟቾች ቁጥር ወደ 60 በመቶ የሚጠጋው ከመስጠም ጋር የተያያዘ ሲሆን ከየት እንደሆነ ከተለዩት ውስጥ ደግሞ ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት በግጭት ውስጥ ካሉ ሀገራት ማለትም ፦
- አፍጋኒስታን፣
- ማይንማር፣
- ሶሪያ
- #ኢትዮጵያ የሄዱ ናቸው።

ከባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለስደተኞች በጣም ገዳይ እና የከፋ የነበረው 2023 ሲሆን 8,541 ሞት ተመዝግቧል።

ዓመቱ በሜዲትራኒያን ባህር በከፍተኛ ሁኔታ ሞት የጨመረበትም ነው።

እጅግ በርካታ አፍሪካውያን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በሚል በህገወጥ መንገድ እጅግ አስከፊ በሆነ መንገድ ወደ #ሊቢያ ሄደው በባህር ተጉዘው አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት የባህር ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል።

እንደ ዓለም አቀፍ ተቋማት መረጃ ፥ አስከፊው ጉዞ አድርገው እድለኛ ሆነው በህይወት ዛሬም ድረስ መረጋጋት ወደሌላት #ሊቢያ የሚገቡ ከሆነ እገታ ፣ ስቃይ ፣ ድብደባ  አለፍ ሲልም ግድያ ሊፈፀምባቸው ይችላል።

በኃላም በባህር ጉዞ ከሊቢያ አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ህይወታቸውን ያጣሉ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#IOM

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ የ38 ሰዎች አስክሬን ተገኘ።

በጀልባ መስጠም አደጋ የህፃናትን ጨምሮ አጠቃላይ 38 ሰዎች ሞተው አስክሬናቸው መገኘቱን የዓለም አቀፉ የስድተኞች ድርጅት አሳውቋል።

6 ሰዎች የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነግሯል።

ከሞት የተረፉ 22 ሰዎች በጅቡቲ እርዳታ እየተደረገለቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
" የ11 ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን ነው የተገኘው " - አይ ኦ ኤም

" ፍልሰተኞችን የጫነ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ መስጠሙን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መሞተዋል ፤ አልያም ጠፍተዋል " ሲል የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አሳውቋል።

አደጋው የበርካቶችን ህይወት ከቀጠፉና በተደጋጋሚ ከደረሱ የጀልባ መስጠም አደጋዎች የቅርብ ጊዜው ነው።

በታይዝ ግዛት ጀልባው ለአደጋ በተዳረገበት ወቅት 25 #ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን እና ሁለት የመናዊ መረከብ ዘዋሪዎችን ጭኖ እንደነበረ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም (አይ ኦ ኤም) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እስካሁን ድረስ የ11ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን የኤደን ባህረሰላጤ እና ቀይ ባህርን በሚያገናኘው በባበል ኤል መንደብ መተላለፊያ ባህር ዳርቻ መገኘቱን እና ሁለቱን የመናዊያን ጨምሮ 14 ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል።

ፍልሰተኞች ከጂቡቲ የተነሱ እንደነበሩ አይ ኦ ኤም አስታውቋል ።

እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየመን የሚደርሱት ስደተኞች በሦስት እጥፍ አድጓል።

በ2021 27,000 ገደማ የነበረው የፍልሰተኞች ቁጥር ባለፈው አመት ከ97,200 በላይ ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 380,000 የሚጠጉ ስደተኞች ግጭት ባየለባት ሀገር ውስጥ ይገኛሉ።

የመን ለመድረስ ፣ፍልሰተኞቹ ቀይ ባህርን ወይም በኤደን ባህረ ሰላጤ ለማቋረጥ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት አደገኛ በሆኑና በተጨናነቁ ጀልባዎች ይወሰዳሉ።

ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 2,082 ስደተኞች የገቡበት አልታወቀም ከእነዚህ መካከል 693 ያህሉ ሰጥመው ቀርተዋል።

በሰኔ ወር ቢያንስ 49 ስደተኞች በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ጀልባቸው በመስጠሙ ሞተዋል።

140 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንዳልታወቀ ድርጅቱ አስታውሷል።

ተጨማሪ 62 ስደተኞች ባለፈው ሚያዝያ ወር የመን ለመድረስ ሲሞክሩ በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ላይ በተከሰቱት ሁለት የጀልባ መገልበጥ አደጋዎች ህይወታቸው አልፏል። #IOM #VOA

@tikvahethiopia