#IOM

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) #የኢትዮጵያ ኃላፊ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ያልተፈቀደ ቃለ መጠይቆችን" አድርገዋል በሚል የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸውን AFP ዘገበ።

ኃላፊዋ ማውሪን አቺየንግ ያልተፈቀደ በተባለው ቃለ መጠይቅ ለህወሓት ወገንተኛ ባሏቸው የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ጎን ገሸሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

ማውሪን አቺየንግ ምንድነው ያሉት?

ባለፈው ሳምንት ማውሪን አቺየንግናና ሌላ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኛ የኢትዮጵያን መንግስት በመደገፍ በርካታ መጣጥፎችን ለሚፅፈው ጄፍ ፒርስ ረዘም ያለ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል።

በቃለ መጠይቁ ላይ እንደሚሰማው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ኃላፊ ማውሪን ጦርነቱ ከተነሳ በኋላ አዲስ አበባ የገቡ የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ባልደረቦቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በመተቸት መሬት ያሉ የድርጅቱ ተወካዮችን አግልለዋል ብለዋል።

ህወሓትን "ቆሻሻ" እና "ጨካኝ" በማለትም ሲናገሩ ይሰማል።

በአንድ ወቅትም ህወሓት ከሳዑዲ አረቢያ የተባረሩ የትግራይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ አሲረዋል በማለትም ሲከሱ ይሰማል።

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩና መውጪያ አጥተው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ ጥያቄ እንደቀረበላቸውና ሩዋንዳም እንዲላኩ የተፈለገው ለሌላ አላማ እንደሆነ ተናግረዋል።

"ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ የተፈለገው የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ ከሩዋንዳ እንዲጀመር" ለማድረግ መሆኑንም ያነሳሉ፤ “እንዲህ ዐይነት ነገር ቆሻሻ ነው” ሲሉ ይደመጣሉ።

ኃላፊዋ በጭራሽ ወደ ትግራይ እንደማይመለሱ ቃል ሲገቡም ይሰማል።

ያንብቡ: https://telegra.ph/AFP-10-12

የመረጃ ባለቤት AFP ነው።

@tikvahethiopia