#IOM

" እ.ኤ.አ ከ2014 እስከ 2023 ቢያንስ 63,285 ሰዎች ሞተዋል / የገቡበት አይታወቅም " - IOM

እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 63,285 ሰዎች በዓለም ላይ ባሉ ስደተኞች በሚጓዙበት መስመር ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም ጠፍተዋል።

አብዛኞቹ ህይወታቸውን ያጡት ደግሞ በውሃ መስጠም ምክንያት ነው።

እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ሪፖርት መሰረት 28,854 ሰዎች የሞቱት እና የት እንደገቡ ያልታወቀው በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ነው።

ከተመዘገቡት የሟቾች ቁጥር ወደ 60 በመቶ የሚጠጋው ከመስጠም ጋር የተያያዘ ሲሆን ከየት እንደሆነ ከተለዩት ውስጥ ደግሞ ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት በግጭት ውስጥ ካሉ ሀገራት ማለትም ፦
- አፍጋኒስታን፣
- ማይንማር፣
- ሶሪያ
- #ኢትዮጵያ የሄዱ ናቸው።

ከባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለስደተኞች በጣም ገዳይ እና የከፋ የነበረው 2023 ሲሆን 8,541 ሞት ተመዝግቧል።

ዓመቱ በሜዲትራኒያን ባህር በከፍተኛ ሁኔታ ሞት የጨመረበትም ነው።

እጅግ በርካታ አፍሪካውያን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በሚል በህገወጥ መንገድ እጅግ አስከፊ በሆነ መንገድ ወደ #ሊቢያ ሄደው በባህር ተጉዘው አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት የባህር ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል።

እንደ ዓለም አቀፍ ተቋማት መረጃ ፥ አስከፊው ጉዞ አድርገው እድለኛ ሆነው በህይወት ዛሬም ድረስ መረጋጋት ወደሌላት #ሊቢያ የሚገቡ ከሆነ እገታ ፣ ስቃይ ፣ ድብደባ  አለፍ ሲልም ግድያ ሊፈፀምባቸው ይችላል።

በኃላም በባህር ጉዞ ከሊቢያ አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ህይወታቸውን ያጣሉ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia