TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ኤዴሌ ኮድር ተፈራርመውታል። ስምምነቱ ዩኒሴፍ በ2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
(ከሲዳማ ዞን መ/ኮ/ፅ/ቤት የተሰጠ ማሳሰቢያ)

የ55ቱ ብሔር ብሔረሰብ መቀመጫ ከተማ አርባ ምንጭ እንዲሆን መደረጉን የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ ገለፁ ተብሎ በጋሞ ሚዲያ ኔት ወርክ የተገለፀው ስህተት መሆኑን የሲዳማ ዞን የሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ባለፈው የዴኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን ተከትሎ በተላለፉት ውሳኔዎች መነሻ የተዛቡና በትክክል ከምንጩ ያልሆኑ አሉባልታዎች በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ሲተላለፉ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም በተሳሳተ ሁኔታ የዴኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉትን በሙሉ በአርባ ምንጭ ከተማ ማዕከል አድርገው እንዲቀጥሉ ተወስኗል በማለት የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል ተብሎ በመለቀቁ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሼር እና ላይክ በማድረግ ኮሜንቶች በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ የሲዳማ ዞን የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ደርሶበታል፡፡

ይህ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ከሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ያልወጣ መረጃ መሆኑንና ምንም ዓይነት ገለፃ ያልሰጡበት ጉዳይ በመሆኑ መቆም አለበት፡፡

በተጨማሪም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ በጋሞ ሚዲያ ኔት ወርክ በኩል የተሳሳተ መረጃ በሶሻል ሚዲያ ላይ የተለቀቀው ስህተት በመሆኑ ለሁሉም ሶሻል ሚዲያ ተከታዮች የማስተካከያ መልዕክት ያስተላልፉ ዘንድ በመጠየቅ ለወደፊቱም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሳያጣሩ ሼር እና ላይክ እንዳያደርጉ ለሁሉም ሚዲያ ተከታዮች መልእክት ማስተላለፋቸውን የሲዳማ ዞን ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ያሳስባል፡፡

ሲዳማ ዞን መ/ኮ/ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በፅ/ቤታቸው እንዲሁም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ እና የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ በተከታታይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።

Via #SMN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

በመቐለ ዙርያ ሮማናት ተብሎ የሚታወቅ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 300 ገደማ ዜጎች መንግስት ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው ቤቶቻች እያፈረሰ ነው ሲሉ ቅሬታቸው አቀረቡ። የጀርመን ራድዮ ያነጋገርናቸው ቅሬታ አቅራቢዎች በትላንትናው ዕለት ብቻ ከ200 በላይ የሚገመቱ ቤቶች "ሕጋዊ አይደሉም" ተብለው ፈርሰዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ከፍተኛ የሀብት ውድመት እንደገጠማቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡

Via #DW
ፎቶ: ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ታስረው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ መሆኑን የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አመራሮቻቸውና አባሎቻቸው የታሰሩት በቀዝቃዛ ቦታ፣ የፀሐይ ብርሃን በማያገኙበትና ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በማይችል ሁኔታ በመሆኑ እንዲሻሻልላቸው ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተው ሲወጡ፣ መውጫ በር ላይ አቶ ክርስቲያንን እንደያዟቸው ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው መርማሪ ፖሊስ በነጋታው ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ፣ ምድብ ወንጀል ችሎት እንዳቀረባቸውም አስረድተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ለምን አቶ ክርስቲያንን በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸውና እንዳሰራቸው ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ ተጠርጣሪው ወጣቶችን መሣሪያ እንደሚያስታጥቁና እንደሚያደራጁ በማስረዳት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት መጠየቁም ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ክርስቲያንም ወጣቶችን መመልመልና ማደራጀት ሥራቸው መሆኑንና ከእስርም ሲለቀቁ የሚቀጥሉት ሥራቸው እንደሆነ ተናግረው፣ መሣሪያ ያስታጥቃሉ ስለተባለው ግን ፖሊስ ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ፣ ለሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ስብሰባውን ረግጦ የወጣ አንድም የማዕከላዊ ኮሜቴ አባል የለም።" #ደኢህዴን #SEPDM

"...በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ስብሰባውን ረግጠው የወጡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሉ ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆን የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽ/ቤት ኃላፊ ጓድ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል።" #ደኢህዴን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአድዋ ማዕከል ግንባታ ተጀምሯል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር እና የታሪካዊ ድሉን ሁለንተናዊ ይዘት ለትውልድ ለማሻገር ሊገነባ የታሰበው የአድዋ ማዕከል በዛሬው ዕለት ግንባታው ተጀምሯል፡፡

የአድዋ ማዕከል ግንባታ ለረዥም ጊዜያት ሳይለማ በቆየው እና ከሚድሮክ ተመላሽ በተደረገው ቦታ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የግንባታው ወጪ ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የዓድዋ ማዕከል ግንባታው ሲጠናቀቅ ከሚሰጠው ማህበራዊና ታሪካዊ ፋይዳ በተጨማሪ በውስጡ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ ፦

✿ የአድዋ ሙዚየም
✿ ከ2000 ሰው በላይ የሚይዝ የዓድዋ አዳራሽ
✿ እያንዳንዳቸው 400 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት አዳራሾች
✿ የሲኒማ አዳራሽ
✿ ቤተ-መፅሐፍ
✿ የስፖርት ማዘውተርያዎች እና ጂሞች
✿ የህፃናት መጫወቻ እና የማቆያ ስፍራ
✿ የጌጣጌጥ መደብሮች
✿ የቤተ-ስዕል ማዕከላት
✿ ዘመናዊ የባስ እና የታክሲ ማቆሚያ
✿ ከ600 መቶ መኪና በላይ የመያዝ አቅም ያለው ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል
✿ ካፌዎች እና የምግብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት
✿ ለንባብ አገልግሎት የሚሆኑ የአረንጓዴ ስፍራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

China Jiangsu International E.T.C.C በተባለ አለም አቀፍ ኩባኒያ ግንባታው የሚካሄደው የአድዋ ማዕከል በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ በውስጡ "ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!" የሚል የአዲስ አበባ ከተማ 'ዜሮ(0.00) ኪ.ሜ' ምልክት ያርፍበታል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ዜና

በእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰበት የስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሳር ምድር ሙሉ ለሙሉ አገግሟል ተባለ፡፡ የፓርኩን የደን ሽፋን ለማሳደግ 50 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉም ተነግሯል፡፡

Via #ShegerFM
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Joseph Joseph
አፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜውን ጨዋታ
በቴሌግራም ግሩፓችን
ገምተው ይሸለሙDon't forget subscribe our Telegram channel
Join @hopemusics @josehope
#NewsAlert

"ለሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የምርጫ ቦርድን ስራ በትእግስት መጠባበቅ ይገባል'" አቶ ቃሬ ጫዌቻ
.
.
#የክልልነት ጥያቄው በህገ-መንግስቱ መሰረት ምላሽ እንዲያገኝ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስራ በመጀመሩ መላው የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በትዕግስት እንዲጠባበቁ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አስታወቁ።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ቃሬ ጫዊቻ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ዙሪያ ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ እንዲቻል ቅድመ-ዝግጅቱን ጀምሯል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ህዝበ ውሳኔውን ለማድረግ እንዲያስችል በደቡብ ክልልና በሲዳማ ዞን መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በመለየት ማሳወቁንና እስከ ሐምሌ 19 ድረስ ዝርዝሩን በጽሁፍ ማቅረብ እንዲቻል የጊዜ ገደብ መስጠቱን አስታውቀዋል።

የሲዳማ ዞን አስተዳደር ከክልሉ መንግስትና ከደኢህዴን ጋር በመሆን በጥያቄው ዙሪያ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙና ምርጫ ቦርድ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንደሚደረግ በመግለጹ መላው የሲዳማ ተወላጆችና ወጣቶች ጉዳዩን በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ቦርዱ በህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ዙሪያ ከሲዳማ ዞንና ከክልሉ መንግስት ጋር በተለያዩ ጊዜያት መወያየቱን ያስታወሱት አቶ ቃሬ ህዝበ ውሳኔውን አምስት ወር ባልሞላ ጊዜ አደራጅቶ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert አንድ ታጣቂ፣ በኢራቋ የኩርዶች ከተማ አረቢል ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ በዛሬው ቀን በፈፀመው ጥቃት፣ እስካሁን በተረረጋገጠው መሠረት አንድ የቱርክ ዲፕሎማት መገደሉን፣ መንግሥዊው የቱርኩ ዜና አውታር ዘግቧል።

መንግሥታዊው ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የቱርክ ምክትል ዋና ቆንስላ የነበረው ዲፕሎማት አረቢል ውስጥ በሚገኘው የቆንስላ ጽ/ቤት በሥራ ገበታው ላይ ነበር። ሌሎች በርካታ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው የተዘገበ ቢሆንም፣ እስካሁን ግን የሞቱትንም ሆነ የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ማወቅ አልተቻለም።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ ያስመርቃል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ፍሬው ተገኘ ለአብመድ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ሐምሌ 13/2011 ዓ.ም የሚያስመርቀው፡፡

በዕለቱም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሃመድ ዑመር ለተመራቂዎች መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ ከሀይማት አባቶች፣ ከጎሳ መሪዎች፣ ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ከልዩ ልዩ የኅብረሰተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 100 የልዑክ አባሎቻቸውን ይዘው ወደ ባሕር ዳር እንደሚመጡ ነው የሚጠበቀው፡፡

የልዑኩ አባላትም የባሕር ዳርና አካባቢዋን የመስህብ ሥፍራዎች እንደሚጎበኙና የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥርን የሚያጠናክሩ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቆቦ አካባቢ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ተከፍቷል!

ጉዳዩ እንዲህ ነው: ትናንት አንድ ነዳጅ የሚጭን ቦቴ መኪና ባጃጅ ገጭቶ ወደ ሀረር ያመልጣል። እሱ መኪና ተመልሶ እንዲመጣ ለማስገደድ ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር የሚወስደው መንገድ ላይ ቆቦ አካባቢ (ከጭሮ ትንሽ አለፍ ብሎ) መንገድ ተዘጋ። በዚህ ወቅት የአንዳንድ ቦቴ መኪኖች መስታወት ተሰብሯል። አሁን በምስሉ ላይ የሚታየው ገጭቶ አመለጠ የተባለው ቦቴ ወደ ስፍራው ስለተመለሰ መንገዱ ክፍት ሆኗል።

Via #Elias_Mesert

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጉባ ቆሪቻ ወረዳ የእርሻ መሬትን ለማስፋፋት ከ1 ሔክታር መሬት በላይ የነበረ ደን ጨፍጭፈዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን የወረዳው ፍርድ ቤት አስታወቀ።

የጉባ ቆሪቻ አቃቤ ህግ መላው ህብረተሰብ በችግኝ ተከላ ስራ በሚረባረብበት ወቅት ሐምሌ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ 1 ሔክታር መሬት ደንን ጨፍጭፈዋል ባላቸው ሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ ይመሰርታል።

ግለሰቦቹ በጎሮ ባቴ ቀበሌ በህዝብ የተተከለ ደንን የእርሻ መሬት ለማስፋፋት በሚል ምክንያት በመመንጠርና መሬቱን ለግል ጥቅም በማረስ ህገወጥ ተግባር ፈጥመዋል የሚለውን የአቃቤ ህግ ክስ የወረዳው ፍርድ ቤት ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተመልክቶት የቅጣት ውሳኔው አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ለኢዜአ እንደገለፀው አቶ ስለሺ ከበደና አቶ ንጉሱ ሰኢድ የተባሉት ተከሳሾች ጥተኞች ሆነው በመገኘታቸውና እራሳቸውን ከክሱ መከላከል ባለመቻላቸው የእስራት ቅጣት ውሳኔው ጸንቶባቸዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ

"በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በነርቭ እና ድንገተኛ ህክምና ላይ ያተኮረው አለምዓቀፍ ኮንፈረንስ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።" A.ነኝ ከ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"....ወደ ኋላ እየተመለከቱ ወደፊት መጓዝ አይቻልም እንደሚባለው ሁሉ፤ እኛም የሚመጣውን ብሩህ እና ያማረ ጊዜ በማሰብ ሀገራችንን ከክፋት፣ ከችጋር፣ ከድንቁርና እና ከልመና ለማሻገር ባለመታከት መስራት ብቻ ሳይሆን መትጋት ግዴታችን ነው፡፡

የእኛ ትውልድ #በንግግር የሚያምን፤ በውይይት የሚግባባ፣ ራሱንም ሆነ ወንድሙን የሚያዳምጥ፣ ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን በጋራ መፍትሄ የሚፈልግ ትንታግ ትውልድ እንጂ በጥላቻ እርስ በርሱ የሚገፋፋ የሚከፋፈል ከፍ ሲልም የሚገዳደል አይደለም፡፡

እኛ የዛሬ ተመራቂዎች ይህንን ታሪካዊ አደራ በሚገባ ተረድተን በመተባበር ፣ በመደጋገፍ ፣ ራሳችንን በእውቀት በማሳደግ ሀገራችንን በቅንነት ለማሻገር ከሚተጉት ጋር ሁሉ ወኔና ጉልበት በመሆን አደራችንን እንድንወጣ እየለመንኩ ፤ በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ መልካም ነገር የግጠማችሁ በማለት ንግግሬን በዚሁ እቋጫለሁ፡፡" አማኑኤል ኢቲቻ/የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንትና የዘንድሮ ተመራቂ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳንዋ በአብዬ ግዛት አንድ የተመድ ሰላም አስከባሪ እና አምስት ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተነገረ። የተመድ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የተገደለው ሰላም አስከባሪ፣ ኢትዮጵያዊ ወታደር ነው። ሌሎች 5 ሰላማዊ ሰዎችም በጥቃቱ ተገድለዋል። አንድ ደግሞ ቆስሏል። በተመድ መግለጫ መሠረት ግድያው የተፈጸመው ሰላም አስከባሪዎቹ መደበኛ ቅኝት በማድረግ ላይ ሳሉ ነው። የአብዬ አስተዳዳሪ እንዳሉት ትናንት ከአብዬ በስተሰሜን በሚገኝ የገበያ ቦታ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት ከሞቱት መካከል አንድ ህጻን ይገኝበታል። በአወዛጋቢዋ በአብዬ ግዛት ከደቡብ ሱዳን ጋር መቀላቀል በሚፈልጉ እና ከሰሜንዋ ሱዳን ጋር መሆን በሚሹ መካከል ግጭት ሲካሄድባት ቆይቷል። ከጎርጎሮሳዊው 2011 አንስቶ የተመድ «ለአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ኅይል» በምህጻሩ «UNISFA» የተባለ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ አሰማርቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመብራት መቆራረጥ ችግር ቀጥሏል፦

የመብራት ፈረቃ ቀረ ከተባለ ወዲህም መብራት ከአምስት ቀን በላይ እየጠፋ ለችግር እየተጋለጡ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ፈረንሳይ አካባቢ ነዋሪዎች ገለጹ።

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ችግሩን በማጣራት ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/M-07-17-381
"....ወደ ኋላ እየተመለከቱ ወደፊት መጓዝ አይቻልም እንደሚባለው ሁሉ፤ እኛም የሚመጣውን ብሩህ እና ያማረ ጊዜ በማሰብ ሀገራችንን ከክፋት፣ ከችጋር፣ ከድንቁርና እና ከልመና ለማሻገር ባለመታከት መስራት ብቻ ሳይሆን መትጋት ግዴታችን ነው፡፡ የእኛ ትውልድ #በንግግር የሚያምን፤ በውይይት የሚግባባ፣ ራሱንም ሆነ ወንድሙን የሚያዳምጥ፣ ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን በጋራ መፍትሄ የሚፈልግ ትንታግ ትውልድ እንጂ በጥላቻ እርስ በርሱ የሚገፋፋ የሚከፋፈል ከፍ ሲልም የሚገዳደል አይደለም፡፡" #አማኑኤል_ኢቲቻ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄውን #ለዘመናት ሲጠይቅ ቆይቷል፤ አሁን ግን ምላሽ አግኝቷል" አቶ ሚሊዮን ማትዮስ/የደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት/

@tsegabwolde @tikvahethiopia