TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🎂ሁለተኛ አመታችንን ልናከብር ቀናቶች ቀርተውናል ዝግጁ ናችሁ?🎂

መልካምነትን ለትውልድ ያስተማሩ፣ በማንም ኢትዮጲያዊ ልቦና በበጎ ስማቸው የሚታወሱ፣ የህጻናቱ እናት፣ የደሀው ጧሪ፣ የታመሙትን አስታማሚ ፣ለተራበ አጉራሽ ለተቸገረ ደራሽ ብዙ ብዙ ባልን በወደድን ብቻ ሥራቸው ተዘርዝሮ አይዘለቅም፡፡

ከኢትዮጵያም አልፈው በአፍሪካም በዓለምም መልካምነትን የሰበኩ #ክብርት_ዶክተር_አበበች_ጎበና ክብር ይገባቸዋልና እናከብራቸዋለን፡፡

ዛሬ ላይ ስማቸው ላይጠፋ ከልባችን ተተክሏል ስራቸውስ?

ስንቱን ህጻን ያስተማረ ከጎዳና የታደገ እንደ እናት የተንከባከበ ድርጅታቸውስ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

እናታችንስ ዛሬ ላይ በምን አይነት የጤና ደረጃ ላይ ይገኛሉ?

ሐምሌ 21 ሁላችንም የቲክቫህ ቤተሰቦች በአበበች ጎበና የህጻናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት #እንገናኝ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ማደራጀትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሚናን አመልክቶ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፦

1.ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ 5 ወራት ይቀረዋል ያለው ለምንድነው?

ምንም እንኳን የሲዳማ ዞን ምክር ቤት የክልልነት ጥያቄውን ለደቡብ ክልል ያቀረበው ቀደም ብሎ ቢሆንም የማደራጀት ጥያቄውን ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው በህዳር 11/2011 ዓ.ም በመሆኑ ቦርዱ ስለጥያቄው እውቅና ኖሮት ዝግጅት የሚጀምረው ከዚሁ ቀን አንስቶ በመሆኑ በተጨማሪም ቦርዱ የህዝበ ውሳኔን የማደራጀት ሃላፊነት የወሰደው ከክልሉ ምክር ቤት በውክልና በመሆኑ ውክልናው በይፋ ከተሰጠበት ከህዳር 11/2011 አንስቶ የቦርዱ ህገመንግስታዊ ገደብ የሚጠናቀቀው ከ5 ወር በኋላ ይሆናል፡፡

2. የምርጫ ቦርድ የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ላይ መልስ ሳይሰጥ እስካሁን ለምን ቆየ ?

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፉት ስምንት ወራት በአዲስ አመራር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ የቆየ ሲሆን ዋና አላማውም ተቋሙ ተአማኒ እና ብቁ እንዲሆን የሚያደርጉትን ሪፎርሞች ማከናወን ነው፡፡

ከነዚህ ስራዎችም መካከል፦

- ከፍተኛ አቤቱታ ሲቀርብባቸው የነበሩ ህጎችን ለማሻሻል የተለያዩ ምክክሮችን ማድረግ ህጉን ማርቀቅና በተወካዮች ምክር ቤት ማጸደቅ

- በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ለወራት ያልተሟሉ የቦርድ አባላትን መሟላት ማስተባበር እና አዳዲስ የቦርድ አባላትን ማሟላት

- ድርጅታዊ መዋቅሮችን ማሻሻል

- የተለያዩ አካላት ጋር መስራት (ከፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራትና ምሁራን ጋር) ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ዝግጅትን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው የዞን እና የክልል አመራሮች፣ ከተወካዮች ምክር ቤት የሲዳማ ዞን ተወካዮችና ወጣቶች ጋር ውይይቶችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ቦርዱ በተሟላለት በአንድ ወር ውስጥ አስቸኳይ ውሳኔ ከሰጠባቸው ጉዳዮች አንዱም የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ጥያቄ ነው፡፡

3. ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ላይ የተለያዩ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች ተጠቅሰዋል ፣ ምርጫ ቦርድ ያንን ለምን አለ ?

ከምርጫ አይነቶች አንዱ የሆነው ሕዝበ ውሳኔ የሚካሄደው ህዝቦች በነጻ መልኩ ምርጫቸውን እንዲያሳውቁ በመሆኑ ሒደቱ እንደማንኛውም ምርጫ የተለያዩ አካላትን ተሳትፎና ዝግጅት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም በህዝበ ውሳኔው ሂደት ላይ የሚመለከታቸው አካላት ሌሎች ምርጫዎች ላይ ዝግጅት እንደሚደረገው ሁሉ ለህዝበውሳኔም ዝግጅት እና ትብብር ማድረግ እንደሚገባቸው ለማመላከት ዋና ዋና የዝግጅት ጉዳዮችን ቦርዱ የሚመለከታቸው አካላትን በማስታወቅ ይሰራል፡፡ እነዚህ ዝግጅቶች መደረጋቸው የሚከናወነውን ህዝበ ውሳኔውን ሰላማዊ ተአማኒ እና ውጤታማ ያደርገዋል፡፡

4. አንዳንዶች ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ ጉዳይ ላይ ፓለቲካዊ አቋም አለው ይላሉ፣ ለዚህ የቦርዱ ምላሽ ምንድነው ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋናው አላማው ስራውን በግልጽነት በመስራት ተአማኒ እና ብቁ የሆነ ተቋም መገንባት ሲሆን በምንም ምርጫንና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተቋሙ የፓለቲካ አቋም የለውም፣ አድሎም አያደርግም፡፡ በስራውም መሰረታዊ የምርጫ መርሆዎች የሆኑትን በነጻ ምርጫ ላይ መሳተፍ ፣ መረጃ የማግኘት፣ ሰላማዊ ውሳኔ መወሰን ላይ መሰረት በማድረግ ህገ መንግስቱን እና የምርጫ ህጎችን መሰረት አድርጎ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፦

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በመግለጫው እንደገለጹት በደኢህዴን 10ኛው ጉባኤ ላይ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሡ የአደረጃጀት ጥያቄዎች በህገ መንግሥቱና በህዝቦች ፍላጎት ምላሽ እንዲያገኝ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታውሰዋል።

ድርጅቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የህዝቦችን ጥያቄ በጥናት ለመመለስ አጥኚ ቡድን ተቋቁሞ ባመጣው ምክረ ሀሳብ ውጤት እና በተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 11 ቀናት ሲመክር መቆየቱን ተናግረዋል።

በጥናቱ ምክረ ሀሳብ መሠረት የሲዳማ ህዝብ ክልል ሆኖ ከተደራጀ በኋላ ቀሪዎቹ የክልሉ ህዝቦች በአንድ ላይ ክልል ይሁኑ ተብሎ የቀረበው ምክረ ሀሳብ የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉት እርከኖች ህዝቡ ተወያይቶበትና በየደረጃው ባሉት ምክር ቤቶች ፀድቆ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ታህሳስ 10/2011 ዓ.ም በፅሑፍ ቢቀርብም የክልሉ ምክር ቤት ባለመሰብሰቡ ለውሳኔ ሳይቀርብ መቆየቱን ተከትሎ ጥያቄው ለደቡብ ክልል ምክር ቤት በፍጥነት ቀርቦ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲተላለፍ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በግንቦት 9/2011 ዓ.ም በሠላማዊ ሰልፍ መጠየቁን ወደጎን የተወና የወላይታ ህዝብን ጥቅም የማያስከብር እና የክልል ጥያቄ የማይመልስ በመሆኑ የወላይታ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሙሉ በሙሉ ሳይቀበሉ መድረኩን ረግጠው በልዩነት መውጣታቸውን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ወንድም የሆነው የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የወላይታ ህዝብን የወከሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ድጋፍ መስጠታቸውን ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

ሌሎቹ የክልሉ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአንድ ላይ መደራጀት አለባቸው የሚለውን ምክረ ሀሳብ የወላይታ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ባለመቀበላቸው የውሳኔ አካል አለመሆናቸውንም ጭምር አቶ ዳጋቶ ተናግረዋል።

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ባረቀበው ምክረ ሀሳብ ላይ የያዘው አቋም የመጨረሻ ውሳኔ ባለመሆኑ የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የምያደርጉትን ሰላማዊ ትግል አጠናክረው እንደምቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደር የአደረጃጀት ጥያቄ እንጂ ከህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጋር ቀጥተኛ መስተጋብር የሌለው መሆኑን በመግለጽ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ለረጅም ዘመናት የዘለቀውን የአብሮነትና የመቻቻል ባህላችንን የሚሸረሽር ባለመሆኑ አጎራባች ህዝቦችም ተገቢውን ድጋፍ እንዲሰጡም ጠይቀዋል።

የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንዲቀጥል ህዝቡ በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል በተረጋጋ እና በሰከነ መንገድ ሰላማዊ ትግል እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረቡት ዋና አስተዳዳሪው መላው የዞኑ ህዝብ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ያሳየው የአብሮነትና የመቻቻል ባህሉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

Via Wolaita Zone Administration Public Relation Office

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የወላይታ ህዝብን የወከሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት #በሙሉ ድጋፍ መስጠታቸውን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

"ከሀምሌ 11 ጋር ተያይዞ ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች የሉም" አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ/የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት/
.
.
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ስጋት ላይ የሚጥሉ ጉዳዮች እንደሌሉ፤ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ተናገሩ። ከሀምሌ 11 ጋር በተያያዘም ዜጎችን ስጋት ላይ የሚጥል ምንም ነገር የለም ብለዋል።

ክቡር ፕሬዘዳንቱ የተናገሩትን ቃል በቃል ከዚህ በታች እንድታነቡት ፅፌላችኃለሁ፦

"የሀዋሳ ከተማን ነዋሪ ወደስጋት ሊጥሉ የሚችሉ ጉዳዮችን በቅርበት እየተከታተልን ከህዝቡ ጋር በመሆን ምላሽ ለመስጠት ሰፊ ስራዎችን ስንሰራ ነው የቆየነው። አሁንም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይም ከሲዳማ አንፃር የተነሳውን ጥያቄ ተንተርሶ ስጋት ውስጥ የሚያስገቡት ነገሮች እንዳሉ ሚደመጡ ነገሮች አሉ ግን ደግሞ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሲያቀርብ ነው የቆየው ይሄ በተለያየ ሂደት አልፎ አሁን የደረሰበት ደረጃ የደረሰ በመሆኑ አሁን ባለንበት ሁኔታ የከተማችንን ፀጥታ የሚያውክ ነገር ይፈጠራል ብለን የምንጠብቀው ነገር የለም። ከሀምሌ 11 ጋር ተያይዞ ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች የሉም የሚል ነገር ነው እየገለፅኩ ያለሁት።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ናይጀሪያ በአፍሪካ ዋንጫ 3ኛ ሆና አጠናቀቀች። ሊጠናቀቅ የፍፃሜ ጨዋታውን እየተጠባበቀ ባለው የአፍሪካ የ2019 የእግር ኳስ ዋንጫ ናይጀሪያ ቱኒዚያን በማሸነፍ 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ትናንት ምሽት በተደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ናይጄሪያ 1 ለ 0 አሸንፋለች። የድል ግቧን ከመረብ ያዋሃዳት በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር 5 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብነቱን እየመራ የሚገኘው ኦዲዮን ኢግሃሎ ነው። ናይጀረያ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ሦስት ጊዜ ዋንጫ ስታነሳ የዘንድሮውን ጨምሮ ደግሞ ለስምንት ጊዜ ያህል ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ቱኒዚያ ደግሞ በፈረንጆቹ 2004 ሻምፒዮን መሆኗ ይታወቃል። በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ነገ በሚደረገው የሴኔጋልና የአልጄሪያ የፍፃሜ ፍልሚያ ይጠናቀቃል።

Via ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትግራይ ክልል በመጪው ሀምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም 12 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን ለመትከል እቅድ ተይዞ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert

በሲዳማ ዞን በሚገኙ ከተሞች አለመረጋጋት እየተስተዋለ እንደሚገኝ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገለፁ። ከሀዋሳ የደረሱን መልዕክቶች እንደሚያስረዱት ከጥዋት ጀምሮ መንገዶች ተዘግተዋል፤ እንቅስቃሴም ቆሟል። በተመሳሳይ የአለታ ወንዶ፣ ይርጋለም፣ እና ሌሎች ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ያለው ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው ገልፀዋል። የአለታ ወንዶ ቤተሰቦች እንሰነገሩን የዝርፊየ እንቅስቃሴ ተስተውሏል። ከሀዋሳ ውጭ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚሉት በአካባቢያቸው ምንም አይነት የመከላከያ እና የፌደራል ሃይል የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ርዕሠ ከተማ ሐዋሳ ዉስጥ የሲዳማ ዞን የክልል መስተዳድር ሥልጣን እንዲሰጠዉ በሚጠይቁ ወጣቶችና በፀጥታ አስከባሪዎች መካካል ዛሬ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰዉ ተገደለ፣ ሶስት ሰዉ ቆሰለ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የሲዳማ ህዝብ ከዓመታት በፊት ያቀረበዉ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዘግይቶም ቢሆን ምላሽ ማግኘት በመጀመሩ መላው የሲዳማ ብሔር እንዲረጋጋ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ጠየቀ። የንቅናቄው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደስላኝ ሜሳ፣ «ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ተቀብሎ ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ መዘጋጀቱን አረጋግጧል።» ብለዋል። በዚሕም ምክንያት የሲዳማ ሕዝብ የህዝበ ውሳኔውን ሂደት እንዲጠባበቅ ንቅናቄው ጥሪ ማስተላለፉን አቶ ደሳላኝ ለጀርመን ራድዬም በሰጡት ቃለ መጠይቅ አመልከተዋል። ይሁንና አቶ ደሳለኝ እንደሚሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ዉሳኔዉ ሊደረግ ከሚገባዉን ቀን አዘግይቷል ብሎ ንቅንቄያቸዉ እንደሚያምን ጠቅሰዉ ለዚሕም ቦርዱ፣ ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል ብለዋል። በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ( ሲአን ) ፣ የሲዳማ ሀድቾ ዴሞክራሲያዊ ደርጅት ( ሲሀዴድ ) እና የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ሲብዴፓ )፣ የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የሚያስችለው የህዝበ ውሳኔ የሚደረግበትን ቀን መንግሥት በአምስት ቀናት ዉስጥ ይፋ እንዲያድርግ ባለፈዉ ሳምንት መጀመሪያ ጠይቀዉ ነበር። የተቀሩት ሁለቱ ፓርቲዎች አስከአሁን ሥለ ጉዳዩ በይፋ ያሉት ነገር የለም።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert

አለታ ጩኮ አለመረጋጋት አለ ነዋሪው ከፍተኛ ስጋት ላይ ነው፤ የፀጥታ ሃይልም አይታይም የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልግልን ሲሉ ለTIKVAH-ETH አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ረፋድ 4፡00 ላይ ፋሲል ከነማ ከመቀሌ 70 እንደርታ በአዲስ አበባ እንዲጫወቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኖ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ መቀሌ 70 እንደርታ ለጨዋታ ባለመገኘቱ ምክንያት ፋሲል ከነማ በፎርፌ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ሀዋሳ ከተማም በግማሽ ፍጻሜው ከኢትዮጵያ ቡና እንዲያደርግ መርሀ ግብር ቢወጣለትም ኢትዮጵያ ቡና ‹‹አልጫወትም›› በማለቱ ውጤቱ በፎርፌ ለሀዋሳ ከተማ ተሰጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎም ፋሲል ከነማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ለዋንጫ ይጫወታሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የፍጻሜ ጨዋታው በቢሾፍቱ ከተማ እንዲካሄድ መወሰኑን ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስነብቧል።
በመርሀ ግብሩ መሠረት ሐምሌ 14/2011 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 በቢሾፍቱ ስታዲዮም የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ከሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ የሚሆነው ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ አመት ውስጥ ከ130 ሺህ በላይ መንገደኞችን ከአዲስ አበባ ወደ አስመራና ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዙን አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለሁለት አስርት አመታት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነታቸውን በመመለስ ሰላማዊ ግንኙነት በጀመሩበት ማግስት የተከፈተው የሁለቱ ሀገሮች የአየር ጉዞ ልክ የዛሬ አመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ባደረገው ጉዞ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በአንድ አመት ውስጥም በአየር መንገዶቹ ለአመታት ተራርቀው የነበሩ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶችን በቀን ሁለት ጊዜ በረራ በማድረግ ማገናኘት መቻሉን ከአየር መንገዱ የተኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አስመራ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ልኡካቸው አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው በዛሬው እለት አስመራ የገቡት። በአስመራ ቆይታቸውም ከኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ትብብር ዙሪ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ወደ አስመራ አቅንተዋል።

Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፦ https://telegra.ph/EHRC-07-18
#Alert

አለታ ወንዶ ከተማ ያለው አለመረጋጋት አሁንም እንደቀጠለ ነዋሪውም በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኝ፤ የዝርፊያ እንቅስቃሴም በስፋት እንደሚታይ፤ የፀጥታ ሃይል በቦታው እንደሌለ ለTIKVAH-ETH መልእክት የላኩ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በዕረፍት ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ህግ ላይ ተወያይቶ ለማጽደቅ ሊሰበሰብ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በረቂቅ ህጉ ላይ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሐምሌ 15/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ይፋዊ ህዝብ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም በውይይት መድረኩ ላይ በአካል መሳተፍ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች በእለቱ እንዲሳተፉ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥሪ ማቅረቡን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ዛሬ በሀዋሳ በወጣቶችና ጸጥታ አስከባሪዎች ግጭት 1 ሰው ሞቶ፣ ሌሎች 3 ሰዎች እንደቆሰሉ DW የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በከተማዋ ከቀትር በፊት የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር፡፡ ጸጥታ ሃይሎች ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶችን ዘግተዋል፤ ነዋሪዎችም ቢዝነሶቻቸውን አልከፈቱም፡፡ የሞባይል ኢንተርኔትም ዝግ ነው፡፡ በተያያዘ ደኢሕዴን ሊቀመንበር ሙፈሪያት ከሚል ከዞኑ ሃላፊዎች ጋር ስብሰባ መቀመጣቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ የሲዳማ እጄቶዎች የሲዳማ ክልልን ለማወጅ ቀነ ገደብ ያስቀመጡት ዛሬ ነበር፡፡ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ቃሬ ጫዊቻ ትናንት ሕዝቡ ተረጋግቶ የምርጫ ቦርድን ሕዝበ ውሳኔ እንዲጠብቅ አሳስበው ነበር፡፡

Via #DW/ዋዜማ/አዲስ ስትልንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert

ይርጋለም ከተማ ያለው አለመረጋጋት እንደቀጠለ ነው ነዋሪውም በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኝ፤ የፀጥታ ሃይል በከተማው እንደሌለ ለTIKVAH-ETH መልእክት የላኩ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራና ሱማሌ ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ነገ በባህርዳር ከተማ ይጀመራል ተባለ። ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሰማሀኝ አስረስ መድረኩ የሁለቱን ክልል ህዝቦች የቆየ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ሐሚመራ ልዑክ ነገ ባ/ዳር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የሀይማኖት መሪዎችን የሀገር ሽማግሌዎችንና ኡስታዞችን ያካተተ ነው።

ም/ፕሬዚዳንቱ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የፊታችን ቅዳሜ በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ አሰማሀኝ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia