TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የመቀሌ 70 እንደርታ እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ቀጣይ ሐሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ እንዲካሄድ ተወስኗል።

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ፋሲል ከነማን ከመቀሌ 70 አንደርታ ማገናኘቱ የሚታወስ ነው። ሁለቱን ቡድኖች ያገናኘው ጨዋታ የት ይካሄዳል የሚለው ጥያቄ ትኩረት ስቦ ቆይቶ ነበር።

ሁለቱ ቡድኖችም የሚጫወቱበት ሜዳ የት እንደሚሆን ከፌደሬሽኑ የሚወሰነውን ሀሳብ ይጠባበቁ ነበር። በመጨረሻም የውድድሩ አዘጋጅ ከሁለቱም ቡድኖች ጋር በመምከር ጨዋታው የፊታችን ሀሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲደረግ ወስኗል።

ጨዋታው ቀጣይ ሐሙስ በዝግ ከረፋዱ 4:00 ላይ ይጀመራል። ከሁለቱ ቡድኖች አሸናፊው የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የፍፃሜ ተወዳዳሪ ይሆናል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 ሚልየን ብር የወጣበት የአመልሰት ሙጬ ፊልም ትላንት ምሽት በብሔራዊ ቲያትር ቤት በድምቀት ተመረቀ።

ትላንት ጠዋት ላይ በኤልያና ሆቴል በተሰጠው መግለጫ ላይ የፊልሙ ፅሐፊ እና ዳሬክተር የሆነችው አምልሰት ሙጬ በመግለጫው ላይ እንደተናገረችው የፊልሙ ሐሳብ ወይም ጭብጥ መርካቶ አካባቢ ተወልዳ አድጋ ራሳን ለመለወጥ ጥረት የምታድርግ አንዲት ሴት ልጅ ሯጭ ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ የያዘ ፊልም እንደሆነ ገልፃለች።

አትሌት ሻለቃ ሐይሌ ገ/ስላሴን ጨምሮ በፊልሙ ላይ ከ 400 የሚደርሱ ተዋንያን በዚህ ፊልም ላይ ተሳትፈውበታል።

Via @AccessAddis
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ሀገራቸው ከሩሲያ የገዛቻቸው የኤስ-400 የሚሳኤል መቃወሚያዎችን በመጪው የፈረንጆቹ 2020 ሚያዚያ ሙሉ ለሙሉ እንደምትረከብ ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመጪው ሀምሌ 22/2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን ለመትከል እቅድ ተይዞ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው፡፡ በአማራ ክልል በዚህ ክረምት ወራት 2 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 100 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከልም ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በደቡብ ክልልም ሐምሌ 22 ቀን 50 ሚሊዮን ችግኝ ይተከላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ በደረሰ ጥቃት የተሰዉ አመራሮችን ቦታ ክፍተት ለመሙላት የተደረገው ምርጫ የአማራን ሕዝብ ካጋጠሙት ችግሮችና ክስተቶች በማውጣት ወደተሻለ ደረጃ እንደሚያሻግር ተገለጸ፡፡ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድርነት በዕጩነት፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ደግሞ ለአዴፓ ምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡

የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የአመራር ማሟላት ሥራው በማዕከላዊ ኮሚቴው በተካሄደ ምስጢራዊ ምርጫ መሠረት ዕጩ ርዕሰ መስተዳድርና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ተመርጠዋል። በጥቃቱ በተሰዉት እና የአዴፓ እና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚዎች በነበሩት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ ምትክ አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አገኘሁ ተሻገርን የመተካት ሥራ እንደተሰራም አቶ አብርሃም ገልጸዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባው በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል። ጨፌው በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ያቀረቡዋቸውን አዳዲስ የስራ ሀላፊዎችን ሹመት ተመልክቶ ነው ያፀደቀው።

በዚህም መሰረት፦

1. ዶክተር ሀብታሙ ኢተፋ፦ የኦሮሚያ ውሃ ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ዴንጌ ቦሩ፦ የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ሃላፊ
3. አቶ ግርማ ሀይሉ፦ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ
4. አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፦ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሃላፊ
5. ዶክተር ቀነኣ ያደታ፦ የኦሮሚያ የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
6. አቶ ሳዳት ነሻ፦ የኦሮሚያ የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ ሰይፈዲን ማሃዲ፦ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እና የጨፌ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ
8. ኢንጂነር ደጀኔ ፍቃዱ፦ ኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
9. ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ፦ የኦሮሚያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ
10.ዶክተር ቶላ በሪሶ፦ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ቦርድ ሰብሳቢ
11.አቶ ዝናቡ አስራት፦ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ(ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል። በዛሬው እለት የተሾሙት የስራ ሃላፊዎችም ጨፌው ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም ጨፌው በዛሬው ስብሰባው የክልሉ ዋና ኦዲተር አመራሮች እና ባለሙያዎች ጥቅማቅጥም ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ ላይ ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውል ሲል አጽድቋል። እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ አደረጃጀት፣ አሰራር፣ የአባላቶች ስነ ምግባር እና የስብሰባ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 201/2009ን አሁን ካለው ተጨባጭ እድገት እና ለውጥ ጋር ጨፌ ኦሮሚያን ለማጣጣም በቀረበው ረቂቅ የማሻሻያ ህግ ላይም ተወያይቶ አጽድቋል።

#fbc
#update ጨፌ ኦሮሚያ ለክልሉ የ2012 በጀት ዓመት ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፅድቋል። #ጨፌ_ኦሮሚያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባምላክ_ተሰማ

ማራቶን በአንድ ርምጃ ይጀመራል እንዲሉ የዛሬው የአፍሪካ ቁንጮ ኢንተርናሽናል አርቢትር የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ምርጥ ተጫዋቾች የሆኑትን እነ ሙሉጌታ ከበደን (ወለዬው) ለመዳኘት ወደ ሜዳ ሲያመራ ልዩ ስሜት ተሰምቶት ነበር። እነሆ ዛሬ ከአመታት በኋላ የአህጉራችን አፍሪካ ኮኮቦችን እየመራ የአህጉሪቱን ታላቅ ውድድር ፍፃሜ ለመዳኘት ፊት አውራሪ ዳኛ ሆኖ ተመርጧል።

ባምላክ የፊታችን አርብ በካይሮ ስታዲዬም ታላቁ ሊቨርፑልን ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ያበቃውን ሳዲዮ ማኔን እና የፔፕ ጋርዲዮላን ማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም የክላውዲዮ ራኒዬሪን ሌስተር ሲቲን ለእንግሊዝ ሻምፒዮንነት ያበቃው ሪያድ ማህሬዝን እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል።

በአላማና መንፈሰ ጠንካራነት የተገነባው የባምላክ ጉዞ በአለም ዋንጫ ትውልድ አህጉሩን አፍሪካን ወክሎ የወርቅ ኳስ አሸናፊዎቹን ከመዳኘት የሚያግደው እንደማይኖር መናገር ይቻላል። በአለም አቀፍ የእግር ኳስ መድረክ ጥሩ ተጫዋች አይውጣብሽ የተባለች የሚመስለው ሃገራችን አሁን ስሟን የሚያስጠራ ጥሩ አጫዋች አግኝታለች።

Via #PetrosAshenafi

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ጨፌው የ13 ዳኞችን ሹመት አፀደቀ። ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደሳ ቡልቻ የቀረበለትን 13 ዳኞች ሹመት ዛሬ አጽድቋል፡፡ አዲስ የተሾሙ ዳኞችም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

Via የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት_እና_የፕሮግራሞቻቸው.pdf
2.4 MB
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዕውቅናና የእውቅና እድሳት ፈቃድ (እስከ ሰኔ 26 ቀን በ2011)
#Breaking

ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ጋር ሀሙስ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍፃሜ ለማለፍ እንደሚጫወት ያሳወቀ ቢሆንም ዛሬ ግን ኢትዮጵያ ቡና ራሱን ከኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) በማግለሉ ሀዋሳ ከተማ #ለፍፃሜ አልፏል፡፡ ሀዋሳም ሀሙስ የመቐለ እና ፋሲልን አሸናፊ የሚገጥም ይሆናል፡፡ እስከ አሁን ሰባት ክለቦች ከዚህ ውድድር ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ-ቴዎድሮስ ታከለ (#teddy_soccer)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ስካይ ላይት ሆቴል አካባቢ የመብራት ፖል ወድቆ በአንድ ሰዉ ላይ የሞተ አደጋ ደርሰ። በቦሌ ክፍለ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል ፊት ለፊት ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መብራት ፖል ተሰብሮ በስራ ላይ በነበረ የመብራት ሀይል ሰራተኛ ላይ #የሞት አደጋ አጋጥሟል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ባለሙያዉ ሳጅን ምትኩ መንገሻ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፤ በአካባቢዉ የሚገኝ አንድ የመብራት ፖል ለመንቀል በክሬን መኪና እየተሰራ ባለበት ወቅት ፤ፖሉ ከክሬኑ አምልጦ በሰራተኛዉ ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

የመብራት ፖሉ በሰዉ ሃይል አልነቀል በማለቱ በመኪና ክሬን ፖሉን ለማንሳት በሚደረግበት ወቅት ፖሉ በሰረተኛዉ ላይ ማረፉንም ሳጅን ምትኩ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ ወዲያዉኑ ህይዎቱ ያለፈ ሲሆን የግለሰቡን ማንነት ለመለየት ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡ የመኪናዉ አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን ሳጅን ምትኩ አረጋግጠዋል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፦
https://telegra.ph/SEPDM-07-16
#update ሱዳናውያን የዜጎች በወታደር መገደልን ተከትሎ ምሽቱን በተቃውሞ ማሳለፋቸው ተገለጸ፡፡ የሃገሪቱ ፖሊስም ተቃውሞ የነበረበትን አካባቢ ዘግቷል ተብሏል፡፡ ሰባት ወራትን ያስቆጠረው የሱዳናውያን ተቃውሞ አሁንም ቀጥሎ የዜጎቹን ህይወት እያስገበረ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በናይጄሪያ የዘር ግጭት ያሰጋል...

ኦባሳንጆ በናይጄሪያ የዘር ግጭት እንደሚያሰጋቸው ገለፁ፡፡ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኦሊሴንጎል ኦባሳንጆ #በሩዋንዳ የተከሰተው አይነት የዘር ግጭት በናይጄሪያ እንዳይከሰት ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

ኦባሳንጆ አሁን በስልጣን ላይ ለሚገኙት ፕሬዚደንት ሞሃመድ ቡሃሪ በፃፉት ይፋዊ ደብዳቤ ‹‹ናይጄሪያ እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ወደ አደገኛ ቁልቁለት እየተጓዘች ትገኛለች ፣ይህንን አደጋ ሊከላከል የሚችለውም የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ብቻ ነው›› ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት ማስተላለፋቸው ነው የተገለፀው፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የፉላኒ እረኞችና አርሶ አደሮች መሀከል በተቀሰቀሰ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ከ 3 ቀናት በፊት ዮሩባ በመባል የሚጠራው ብሄረሰብ ከፍተኛ መሪ ሩቤን ፋሶራንቲ ልጅ የሆኑት የ58 አመቷ ኦሊኩንሪን ግድያ ተከትሎ ብዙዎችን ከስጋት ከቷል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚደንት ኦሊሴንጎል ኦባሳንጆም ከቀናት በፊት ባደረጉት ንግግር ‹‹ይህ በቀላሉ የሚታይ ጉዳይ አይደለም…ሀገሪቱን በሩዋንዳ ለተከሰተው አይነት የዘር ፍጅት የሚያጋልጥ ነው›› ሲሉ ገልፀው ነበር፡፡

በትላንትናው እለትም ጉዳዩ ያሳሰባቸው ኦባሳንጆ የተለያዩ ጎሳዎች በጥላቻና ቂም ለበቀል እየተነሳሱ ነው…ይህም እጅጉን አስጊ ነው ሲሉ ለፕሬዚደንት ቡሃሪ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ መፃፋቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

Via CTGN/zamiradio/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት 3 ነጥብ 4 በመቶ ደረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ የስርጭት መጠን 3 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፅ/ቤት ከአስሩም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ከተውጣጡ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ጋር የ2011 እቅድ አፈፃፀምን እየገመገመ ይገኛል።

በግምገማው ላይም በከተማዋ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እና አሁን ላይም 3 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተመልክቷል።

ለዚህም በከተማዋ ያሉ አጋላጭ ቦታዎች መስፋፋት እና የስነ ምግባር ክፍተት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

በአለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት የኤች አይ ቪ ስርጭት ከ1 በመቶ በላይ ከሆነ ያ ሀገር በበሽታው ወረርሽኝ ውስጥ ነው።

ይህም በከተማዋ ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት መጠን በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የሚያመላክተው።

Via #AHADU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የመጋዘን አስተዳደር ስልጠና፦

•የስልጠና ጊዜ : ከሃምሌ 29-ነሃሴ 10/2011
•የስልጠና ሰኣት : የጥዋት ፈረቃ ከ2:30-6:30
: የከሰዓት ፈረቃ ከ7:30-11:30

የስልጠና ቦታ፡ ካዛንችስ ንግስት ታወርስ ሆቴል እና አፓርትመንት 4ኛ ፎቅ

ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ :
0115589045
0903182525
CPJ የ2019 የዓለም ፕሬስ ነጻነት ተሸላሚዎችን ይፋ አደረገ። «በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ሁኔታ እያሳሰበኝ መጥቷል» ሲል በቅርቡ መግለጫ ያወጣዉና ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ድርጅት CPJ ፤የዘንድሮ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ተሸላሚ ጋዜጠኞችን ዝርዝር ይፋ አደረገ። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጁኤል ሲሞን እንደገለፁት አሸናፊዎቹ ህይወታቸዉንና ነፃነታቸዉን በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በመጣል ዘገባዎችን ወደ ህዝብ ያደረሱ ጋዜጠኞች ናቸዉ። በዚህም መሰረት የብራዚል ፣የህንድ ፣የፓኪስታንና የኒካራጓ ጋዜጠኞች ከአፍሪካ ደግሞ ማክስሴን ሜሎ ሙባያዚ የተባለች የታንዛኒያ ጋዜጠኛ ድርጅቱ የ2019 የመናገርና የመፃፍ አሸናፊ አድርጎ መርጧቸዋል። በጎርጎሮሳዉያኑ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ/ም በኒዮርክ ከተማ ተሸላሚ ጋዚጠኖቹ ሽልማታቸዉን ከድርጅቱ በይፋ ይወስዳሉ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በትላንትናው ዕለት በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ የኢቦላ ቫይረስ እንዳለበት የተረጋገጠው ግለሰብ በዛሬው ዕለት ህይወቱ አልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እውን በድሬዳዋ ከተማ መፈንቅለ ከንቲባ ተካሂዷል?

/ኢትዮ ኤፍ ኤም/

ከሰሞኑ በድሬደዋ ተካሄደ የተባለው ከንቲባው አቶ መሃዲ ጊሬ በፈረንሳይ ሃገር ለስራ ባቀኑበት ወቅት እንደነበርም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም በህገ-ወጥ መንገድ ስልጣንን ለመውሰድ ተደረገ የተባለውን ሙከራ በተመለከተ ከከተማ አስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ሚዲያው በፈለገው መንገድ እየተረጎመ የሚሄድበት አግባብ ቢኖርም በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ላይ የተሞከረ ምንም ነገር የለም ብለዋል፡፡

በወቅቱ ከንቲባው ለስራ ውጭ ሀገር ስለነበሩ ምክትላቸው እሳቸው በሌሉበት ሁኔታ ተክተው የመስራት ሀላፊነት ስላለባቸው በዛ መንገድ በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ላይ አጠቃላይ ግምገማ መደረግ እንዳለበት ተስማምተን ወደ ውይይት ገብተናል ብለዋል፡፡

የድሬደዋ ከንቲባ አቶ መሃዲ ጊሬ ሀገር ውስጥ በሌሉበት ሁኔታ ካቢኔው ግምገማ ማካሄዱ ከንቲባውን በሌሉበት ከስልጣን ለማውረድ የተደረገ ሙከራ ነው ሊባል ይቻላል...በወቅቱስ በካቢኔው መካከል አለመስማማት ተፈጥሮ ነበር ወይ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ሀላፊው የሰጡት መልስ ምንም አለመግባባት አልተፈጠረም፡፡ በሂደቱም ከንቲባውን በተመለከተ ምንም ውሳኔ ላይ አልደረስንም፡፡ ይሁን እንጂ ከንቲባው ነገሩን ውጭ ሀገር በነበሩበት ወቅት ነገሩን በተረጎሙበት ምክኒያት ወደ መረጃ መዛባት ውስጥ ገብተናል በማለት ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

አሁን ምክትል ከንቲባው የዋናውን ቦታ ተክተው እየሰሩ ነው ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄም ሀላፊው አቶ እስቅያስ ሁለቱም ከንቲባዎች እንደቀድሞው በስራቸው ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahetbiopia