#NewsAlert

በአዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ስካይ ላይት ሆቴል አካባቢ የመብራት ፖል ወድቆ በአንድ ሰዉ ላይ የሞተ አደጋ ደርሰ። በቦሌ ክፍለ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል ፊት ለፊት ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መብራት ፖል ተሰብሮ በስራ ላይ በነበረ የመብራት ሀይል ሰራተኛ ላይ #የሞት አደጋ አጋጥሟል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ባለሙያዉ ሳጅን ምትኩ መንገሻ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፤ በአካባቢዉ የሚገኝ አንድ የመብራት ፖል ለመንቀል በክሬን መኪና እየተሰራ ባለበት ወቅት ፤ፖሉ ከክሬኑ አምልጦ በሰራተኛዉ ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

የመብራት ፖሉ በሰዉ ሃይል አልነቀል በማለቱ በመኪና ክሬን ፖሉን ለማንሳት በሚደረግበት ወቅት ፖሉ በሰረተኛዉ ላይ ማረፉንም ሳጅን ምትኩ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ ወዲያዉኑ ህይዎቱ ያለፈ ሲሆን የግለሰቡን ማንነት ለመለየት ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡ የመኪናዉ አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን ሳጅን ምትኩ አረጋግጠዋል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia