TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሐምሌ 18 በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ከሞቱ ሰዎች መካከል 16ቱ የኢሮብ ወረዳ ተወላጆች መሆናቸውን ዛሬ የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል። አስሩ ሴቶች ናቸው፣ የተመድ እንዳለው ሊቢያ አቅራቢያ በደረሰው አደጋ 150 ገደማ ሰዎች እንዳለቁ ይገመታል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ከቅዳሜ ጀምሮ አገልግሎቴ ስለተቋረጠ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል፤ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ዛሬ ላይ ተቀርፎ ሙሉ በሙሉ የተሟላ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ብሏል።

#ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ደቡብ

በ2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል በነበረ አለመረጋጋት በጉራጌ፣ ሲዳማ፣ ከፋ፣ ጎፋና በጌድዖ #ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመዘጋታቸው ከ40 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። «አሁንም ሎካ ብላቴ ዙሪያ ወረዳና ምሥራቅ አርሲ ድንበር አካባቢ ላይ ግጭቶች አሉ፤ ወደ 7 የሚጠጉ የተቃጠሉ ትምህርት ቤቶች አሉ። እዛ አካባቢ አሁንም ተመልሰን ለማስተማር እና የማካካሻ ፕሮግራም ለመስጠት እንቸገራለን የሚሉ ወረዳዎች አሉ» ብለዋል።

Via #DW
@tsegawolde @tikvahethiopia
#ሰሜን_ኮሪያ

ሰሜን ኮሪያ አጭር ርቀት ተጓዥ ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በምስራቃዊ ወደቧ በኩል አስወንጭፋለች ስትል ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች። ይህ ሙከራ በሳምንት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ አገሪቱ ይሄንን ያደረገችው ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ መጀመሯን ተከትሎ ቁጣዋን ለመግለፅ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CAF

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ሜዳዎች ከደረጃ በታች ናቸው ብሏል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ኢትዮጵያ የ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታደርግ እድል ሰጥቶ ነበር፡፡ #ኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የምትችልበትን አቋም ለማወቅ ካፍ በሥራ አስፈጻሚዎቹ አማካኝነት በሀገሪቱ የሚገኙ ሜዳዎችን አሰሳ አስደርጓል፡፡ የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትም በኢትዮጵያ ባደረጉት የሁለት ጊዜ አሰሳ ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት ዝግጁ አይደለችም የሚል ድምዳሜ በመድረሱ የኢትዮጵያን እድል ለካሜሮን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CAF-08-06
#ወረታ_ደረቅ_ወደብ

ግንባታው 47 በመቶ #የተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የወረታ ደረቅ ወደብ መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሥራ ይጀምራል ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት 8ኛውን የደረቅ ወደብ መዳረሻ በወረታ ከተማ ለመገንባት 20 ሄክታር መሬት ወስዶ ወደ ሥራ ገብቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 500 ሺ በላይ የሚሆን ደብተር ድጋፍ አደረገ፡፡ በገንዘብ ሲተመን ድጋፉ ከ5.8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነው ተብሏል፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለተማሪዎች ላደረገው ድጋፍ ኢ/ር ታከለ ኡማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

#ስጦታለአዲስአበባዬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በናይሮቢ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ ሳይዙ በሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ድንበር አቋርጠው ወደ ኬንያ በመግባታቸው በተለያዩ ማረምያ ቤቶች ታስረው የነበሩ 64 ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና #ኤርትራ!

#ለኤርትራ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከተቀመጡ 16 ሺሕ ተማሪዎች 40.8% ማለፋቸውን የአገሪቱ የማስታወቂያ ምኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር አስታውቀዋል። ፈተናውን ያለፉ የዲግሪ፣ ዲፕሎማና የሰርተፍኬት ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

Via Yemane G.Mekel,እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከአውሎፕላን ነዳጅ በስተቀር የነሃሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል። የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሃምሌ ወር ሲሸጥበት ከነበረው ዋጋ በ1ብር ከ85 ሳንቲም የጨመረ መሆኑ ተሰምቷል። #fbc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ከነማ

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለአንድ ዓመት ባሕር ዳር ከነማን ለማሰልጠን ዛሬ ፈርሟል፡፡ ቡድኑን ለማሰልጠን በቃል ደረጃ ተስማምቶ የነበረው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ዛሬ ሐምሌ 30/2011 ዓ.ም ፊርማውን አስቀምጧል።

Via #AMMA
ፎቶ: #SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ የሆቴል ገበያው እየተቀዛቀዘ ነው፤ የሆቴል ቱሪዝም ባለሞያዎች ፍልሰትም ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ እየታየ ነው።

Via #ታዲያስ_አዲስ/የሬድዮ ዝግጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በሲንጋፖር ሆስፒታል የህክምና ክትትል እያደረጉ መሆናቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት #ኢመርሰን_ምናንጋግዋ ተናግረዋል፡፡ ሙጋቤ የዚምባብዌ መስራች አባትና ባለውለታ መሆናቸውን የገለፁት ምናንጋግዋ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጤንነት ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
FM_08062019_183840
<unknown>
ልዩ መረጃ ከአቶ አርዓያ ጋር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አርብ ወይም ከዛ በፊት ይፋ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገብረ እግዚአብሔር ለልዩ መረጃ የሬድዮ ዝግጅት ተናግረዋል።

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እርማት እና #ከእርማት ጋር ተያያዥ የሆኑ ስራዎች መጠናቀቃቸውን የገለፁት አቶ አርዓያ፤ የቀረው በSMS እና በኢንተርኔት የመልቀቅ ስራ ነው ብለዋል። ተማሪዎች "most probably ከአርብ በፊት ሊያገኙ ይችላሉ" ሲሉም ገልፀዋል። ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ሀሰተኛ ገፆችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ አርዓያ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ እና የኤጄንሲውን ድረገፅ እንዳለ ተናግረዋል፤ በሀሰት መረጃዎች እንዳይወናበዱም የኤጀንሲውን ህጋዊ ገፆች እንዲከተሉም መክረዋል። ነገ 4:00 ወይም 8:00 ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ ይፋ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።

Via #LiyuMereja
ፎቶ፡ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በተለያዩ የመንግስት እና የግል ፕሮጀክቶች ውስጥ የስራ እድል መፍጠሩ አስታወቀ። የ2011 በጀት የዕቅድ አፈጻጸም በጀት ግምገማ እና የ2012 በጀት ዕቅድ ውይይት ላይ ያተኮረ የስራ የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዘነበ ኩማ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ2 ሺህ 166 የሚሆን ሄክታር መሬት ለሼዶች እና ለአረንጓዴ ልማት ውሏል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመት ውስጥ ለ99 ሺህ ኢንተርፕራይዞች 7.3 ቢሊዮን ብድር መስጠቱንም ገልጸዋል። #EBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባንኩ ተዘርፏል!

"የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለቡ ሙዚቃ ሰፈር ቅርንጫፍ ተዘርፎል። ግምቱ 1.7 ሚሊዮን ብር ካዝናውን በመስበር ተዘርፏል። ዝርፊያው የተፈፀመው ለሰኞ አጥብያ እሁድ ሌሊት ነው" ይህን መልዕክት ትላንት ምሽት የላከልኝ ስሙን የማልገልፀው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ነው።

ስለጉዳዩ እውነትነት የባንኩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በለጠ ዋቅቤካ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አረጋግጠዋል፤ በዝርፊያው የተጠረጠሩ የባንኩ ጥበቃዎችና ሌሎች በጉዳዩ የተጠረጠሩ የአካባቢው ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ አቶ በለጠ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ንግግር!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወይዘሮ #መዓዛ_አሸናፊ አርብ ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም የሕግና የፍትህ ግንዛቤ ማስጨበጫ ጉባዔ ላይ የጠቀሱት ምሳሌ መነጋገሪያ ሆኗል። ፕሬዝዳንቷ ምሳሌውን የሰጡት አንድ ግዛት የፍርድ ቤት ውሳኔን አልቀበልም ካለ በኃይል ማስከበር እንደሚያስፈልግ ለመግለፅ ከወደ አሜሪካ አንድ ተሞክሮ በመምዘዝ ነበር።

ምሳሌው፤ በአሜሪካ በ1950ዎቹ የነጮችና የጥቁሮች የትምህርት እድልን አስመልክቶ ከጥቁሮች የቀረበውንና ፍርድ ቤት የወሰነውን ግዛቷ አልቀበልም በማለቷ በወቅቱ አገሪቷን ያስተዳድሩ የነበሩት ፕሬዚደንት ድዋይት አይዘንአወር ውሳኔውን ለማስፈፀም ኃይል መጠቀማቸውን የሚገልፅ ነበር። ታዲያ ይህ የፕሬዚደንቷ ንግግር የትግራይ ክልል ላይ ያነጣጠረ ነው ያሉ ወገኖች ነበሩ።

የቢቢሲ አማርኛ ዘገባን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/M-08-06
#የደቡብ_ክልል_ኮማንድ_ፖስት

"በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 30/11/11 ደቡብ ክልል ግዜያዊ ኮማን ፖስት ከጉራጌ ፥ ስልጤ፥ሀድያና ከምባታ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ የሚሊሻ ኃላፊና የሰላምና የጸጥታ ኃልፊዎች በቀጣይ የሚሰሩ እቅዶችና በአተገባበር መመሪያ የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሄዷል።"

Via #B/የመድረኩ ተሳታፊ/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia