የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በተለያዩ የመንግስት እና የግል ፕሮጀክቶች ውስጥ የስራ እድል መፍጠሩ አስታወቀ። የ2011 በጀት የዕቅድ አፈጻጸም በጀት ግምገማ እና የ2012 በጀት ዕቅድ ውይይት ላይ ያተኮረ የስራ የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዘነበ ኩማ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ2 ሺህ 166 የሚሆን ሄክታር መሬት ለሼዶች እና ለአረንጓዴ ልማት ውሏል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመት ውስጥ ለ99 ሺህ ኢንተርፕራይዞች 7.3 ቢሊዮን ብድር መስጠቱንም ገልጸዋል። #EBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia