TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአርባምንጭ ሲቀላ ክፍለ-ከተማ ድልፋና ቀበሌ በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በአንድ ብሎክ የንግድ ማዕከል ላይ ውድመት ማስከተሉ ተገለፀ፡፡

በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ለተጎዱ ነጋደዎችና ቤተሰቦች ማዘናቸውን የገለፁት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አርኮ ደምሴ የእሳት ቃጠሎው መንስኤ እና በንብረት ላይ ያደረሰው የጉዳት መጠን በቀጣይ ተረጋግጦ ይገለፃል ብለዋል፡፡

አሁን የማረጋጋት ስራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረው የዞኑ አስተዳዳርም በመልሶ ማቋቋሙ ሂደት ከተጎጂዎች ጎን በመቆምየድርሻውን ይወጣል ብለዋል፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኩማንደር ረታ ተክሉ በበኩላቸው ሰኔ1/2011 ዓ.ም 1200 ካ.ሜ ላይ በተገነባው ባለ 110 የአልበሳት ሱቆች ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ በአንደኛው ሱቅ ጢስ መታየቱን እና ይህ በፍጥነት ተቀጣጥሎ የንብረት ውድመት ማስከተሉን ተናግረዋል፡፡

በአርባንምጭ ዩንቨርሲቲ ፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ እሳት አደጋ መከላከያ ማሽኖች፣ የፖሊስ ሠራዊት፣የሀገር መከላከያ እና የደቡብ ልዩ ኃይል ክህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ የእሳት ቃጠሎው ወደሌሎች ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል፡፡

በቀጠሎው ምክንያት የደረሰው ጉዳት ለጊዜው አልታወቀም ያሉት ኮማንደሩ ከዞን እናከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ተቀናጅቶ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ተናግረው በአጠቃላይ የአደጋው መንስዔ እና በንብረትላይ የደረሰው ጉዳት ተጣርቶ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

Via Gamo Zone Administration public Relation office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከአዲስ አበባ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሃይማኖት መሪዎች፣ የማህበረ ቅዱሳን አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ከተለያዩ ማህበራት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በክረምቱ ወቅት በአስተዳደሩ በሚካሄዱ ዘርፈ ብዙ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የሃይማኖት ተቋማትና ተማሪዎች ህዝቡን በማስተባበር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጋሞ እና ኮሬ የህዝብ ለህዝብ ትስስር መደረክ በአርባምንጭ ከተማ ተካሄደ። የጋሞ ዞን ዋናአስ ተዳዳሪ አቶ አርኮ ደምሴ በጋሞእና ኮሬ ሕዝብ መካከል ለዘመናት የነበረውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር ታስቦ የሁለቱ ብሔረሰቦች የህዝብ ለሕዝብ ትሰስር መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

የጋሞ ከፍተኛ ዳጋማ አካባቢዎች የጥንታዊ ሰው መገኛ እንደሆኑ በርካታ የታሪክ መጻህፍት ይመሰክራሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከጋሞ አካባቢ ተንቀሳቅሰው በቦታ ርቀት ተለያይተው የቆዩት ሁለቱ ብሔረሰቦች አሁን የፈጠሩት ትስስር በኢትዮጵያ የመደመር መርህ ለሌሎች አካባቢዎችም እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ የሚችል ነው ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ እየታዩ ያሉ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል በአንድ ጊዜ ሳምንት ውስጥ በጥናት ላይ የተመሰረተ እርምጃ ሊወሰድ ነው። በኢንጅነር ታከለ ኡማ ሰብሳቢነት የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ተወካዮች ዛሬ ስብሰባ አካሂደዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ በዚሁ ጊዜ በጋራ ግብረ ሃይል በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በጥናት ላይ የተመሰረተ የወንጀል መከላከል እርምጃ ለመውስድ የሚያስችል ስልት ለመንደፍና በቅንጅት ወደ እርምጃ ለመግባት ተስማምተዋል። ግብረ ሃይሉ በተለይ በከተማዋ እየሰፋ የመጣውን የሞተር ሳይክል ቅሚያና ሌሎች በተናጠልና በቡድን የሚፈፀሙ የተደራጁ ወንጀሎችን በመቅጨት የከተማውን ነዋሪ ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት ተሰጥቶታል። ግብረ ሃይሉ በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚያደርጉ የተለያዩ የወንጀል መከላከል ስልቶችን በጋራ እንዲያወጣም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በአባይ ተፋሰስ ዙሪያ 20 ሚሊዮን ዘለቄታዊ የኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ መቀመጫውን ባህርዳር ያደረገው የአባይ ተፋሰስ ልማት ጽህፈት ቤት ገልጿል። 20 ሚሊዮን የአፕል፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ጌሾ እና ሌሎችም ችግኞች እንደተዘጋጁ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ አክሱም ከተማ ሲገቡ የትግራይ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአክሱም ሀውልትንም ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚስትሩ በአክሱም ቆይታቸው በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየተሰጠ ነው...

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ ነው። የፈተናውን ሂደት በጣምራ የሚመሩት የትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ ለፈተናው አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ስድስት የአቼቶ ምርቶች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡ ባለስልጣኑም ምርቶቹንም ሸማቹ ህብረተሰብ እንዳይጠቀም አስጠንቅቋል፡፡የአምራች ድርጅቶቻቸው አድራሻና ምንጫቸው የማይታወቁ የምግብ ምርቶች ገበያ ላይ እየዋለ መሆኑን በተደረገው የገበያ ቅኝት ማግኘቱንም አስታዉቋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ድርጅቶች ተመርተው ወደ ገበያ በተሰራጩ ምርቶች ላይ በተደረገ የገበያ ቅኝት በብሔራዊ ደረጃ የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ፤ ምንም ዓይነት ገላጭ ጽሁፍ የሌላቸው፤ የአምራች አድራሻ እና መለያ ቁጥር የሌላቸው የአቼቶ ምርቶች ገበያ ላይ መገኘታቸው በተደረገው የቁጥጥር ስራ የተገኘ ሲሆን ባለስልጣኑ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ አስታዉቋል፡፡

Real Aceto (ሪል አቼቶ)፤ Munit Aceto (ሙኒት አቼቶ)፤ Herme Aceto (ሐርሚ አቼቶ)፤(ሳሚ አቼቶ)፤ Sname Trading Aceto (ሰናሚ አቼቶ)እና Saron Aceto (ሳሮን አቼቶ) ናቸዉ እርምጃ የተወሰደባቸዉ፡፡በመሆኑም ህብረተሰቡ እነዚህን የአቼቶ ምርቶችን እንዳይጠቀማቸው እያሳሰበ ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፤ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ጠይቋል፡፡በተጨማሪም የክልል ተቆጣጣሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የቁጥጥር አካላት ምርቶቹን ከገበያ ላይ በአፋጣኝ የመሰብሰብ ስራውን እንዲሰሩ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም...

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአክሱም ቆይታቸው በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ከመወያየታቸው በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወሰኑ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል፡፡ ምክር ቤቱ በ8 ተቃውሞ እና በ4 ድምፀ ተዓቅቦ ነው በአብላጫ ድምፅ የወሰነው።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው የሕዝብና የቤት ቆጠራው ዳግም ይራዘም አይራዘም በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክርክር ካደረገበት በኋላ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በ24 ተቃውሞ እና በ2 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል። ምክር ቤቶቹ ባሳለፉት ውሳኔ ላይ በጋራ ይመክሩበታል ተብሎ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ትንባሆና ሺሻ በሚያስጨሱ የአልኮል መጠጥ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ተቆጣጣሪ አካላት እና ከፖሊስ ጋር ባደረገው ክትትል ትንባሆና ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ የአልኮል መጠጥ ቤቶች ላይ ነው እርምጃ ወስጃለሁ ያለው።

በዚህም 30 የአልኮል መጠጥ ምሽት ቤቶች ባለቤትና ሥራ አሥኪያጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ነው የገለፀው።

በዚህ ዓመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ 1112/2011 ሲጋራ እና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን አስመልክቶ ክልከላ አስቀምጧል።

በክልከላውም እንደ ሆቴል፣ ሬስቶራንት፣ ምግብ ቤት፣ መጠጥ ቤት እና የምሽት ቤት በመሳሰሉ ማንኛውም ድርጅቶች በአስር (10) ሜትር ዙሪያ እንዲጨስ መፍቀድ ያስቀጣል።

በአዋጁ አንቀፅ 5 ደግሞ የሺሻ ምርትን ማምረት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከማቸት፣ ማከፋፈል፣ ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል።

ማንኛውም ሰው ሺሻን ያመረተ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ያከፋፈለ፣ ያከማቸ ወይም የሸጠ እንደሆነ ከ3 ወር እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር 1 ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ተካትቷል፡፡

በመሆኑም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ባደረገው ቁጥጥርና ክትትል ትንባሆና ሺሻ በሚያስጨሱ 30 የአልኮል መጠጥ ምሽት ቤቶች ባለቤትና ስራ አስኪያጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

በቀጣይም አዋጁን በሚጥሱት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ነው ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡

ህብረተሰቡም ድርጊቶቹን ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 8482 ጥቆማ እንዲያደርስ ተጠይቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሁላችን ከተባበርን የማንፈታው ችግር የለም" ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
.
.
ሁሉም ሕብረተሰብ በሚችለው ከተባበረ የማንፈታው ችግር እንደማይኖር የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ የበሪ ሜዳ ሆስቴልና የሴት ተማሪዎች ትምህርት ማዕከል ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ባለሃብቶችና የአካባቢው ሕብረተሰብ ይህንን የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ችግር የሚፈታ ህንፃ ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱ የሚመሰገን ነው።

ዶክተር ደብረጽዮን አያይዘውም በተመሳሳይ መልክ የህዝብን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ሌሎች የልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

በተለይ ትምህርት ላይ የሚደረግ ልማት ለሁሉሞ ቁልፍ ሲሆን የሴት ተማሪዎችን በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ችግር መፍታትና ማስተማር ደግሞ ሁሉንም ሕብረተሰብ ማስተማር በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዋናው ነገር ከዚህ ሆስቴልና የትምህርት ማዕከል መገንባት በስተጀርባ ያለው የእንችላለን አስተሳብ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ደብረጽዮን ሌሎች በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ስራዎችን እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል።

ማዕከሉ የተሰራው በበጎ አድራጊዎች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ 160 ሴት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ሆነዋል።

Via Tigray Communication
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቆሼ...

"ፀግሽ ረጲ ቆሻሻ ማከማቻ በተለምዶው "ቆሼ" የሚባለው ከእንደገና ፈርሷል። የእሳትና ድንገተኛ አደጋም ቦታው ይገኛል። በአሁን ሰዓት የፈረሰውን የሚያነሳ እስካቫተር እየተጠበቀ ነው። የጉዳቱ መጠን ገና አልታወቀም።" ሳሚ ከአ/አ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና በቆሼ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፡፡ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዳግም በተከሰተ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ እስካሁን የአንድ ሰው አስክሬን መገኝቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለአሀዱ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

Via Ahadu Radio
ፎቶ ፦ ሳሚ/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም...

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። ነዋሪዎቹ ጠ/ሚሩ ጥያቄያቸውን ተቀብለው ሐውልቱን በማደስ ዙሪያ ለመነጋገር መምጣታቸውን አድንቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጠ/ሚሩ በበጀት ምደባ፣ በውኃ እጥረት፣ በመሠረተ ልማት ጥያቄዎችና በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከነዋሪዎቹ ጋር ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በዛሬው ዕለት በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።

አደጋውን ተከትሎ በአካባቢው በተደረገ ቁፋሮ አንድ የ70 ዓመት አዛውንት በህይወት ማውጣት ቢቻልም አለርት ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

አደጋው የደረሰው ቆሻሻ ከተጠራቀመበት አካባቢ ላይ ከተሰሩ የፕላስቲክ ቤቶች እና መንገድ ዳር በመሆኑ እስካሁን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።

አሁን ላይም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቆሻሻው በተደረመሰበት አካባቢ የሰው ህይወት ለማዳን በኤክስካቫተር የታገዘ ቁፋሮ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከሁለት ዓመት በፊት በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

Via #fbc
Photo: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከASTU...

"ፀግሽ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የተማሩ ወጣቶችን በመስኖ ልማት ለማሰማራት ከኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ የተማሩ ወጣቶች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።" #ፋንታሁን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ማሊ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በሃገሪቱ ዶጎን የሚባሉ የጎሳ አባላት መኖሪያ በሆነች መንደር በተፈጸመ ጥቃት ከ100 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በመካከለኛ ማሊ ሶብሌ ኮው በምትባል አንስተኛ መንደር ውስጥ መሆኑን 'አርኤፍአይ' የተሰኘው የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአከባቢው ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ የሟቾች አስክሬን እንዲቃጠል ተደርጓል። ተጨማሪ የሟቾች እስክሬን እየተፈለገ መሆኑን የአከባቢው ባለስልጣናት ጨምረው ተናግረዋል።

ከቅርብ ወራት ወዲህ በማሊ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ከዚህ ቀደም የነበሩት ጥቃቶች ብሄረ ተኮር አልያም በጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ናቸው።

በእዚሁ አከባቢ የዶንጎ ጎሳ አባላት በሆኑ አዳኞች እና የፉላኒ ጎሳ አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት የተለመደ ነው።

ከሶስት ወራት በፊት 130 የሚሆኑ የፉላኒ ጎሳ አባላት የዶንጎ አዳኞችን ልብስ በለበሱ ሰዎች በአንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ ተገድለው ነበር።

በእነዚህ ሁለት ጎሳዎች መካከል ግጭት እየተበራከተ የመጣው ከአራት ዓመታት በፊት ጸንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች በቀጠናው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ወዲህ ነው።

Via #bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia