TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላጆች ልጆቻችሁን አስመዝግቡ!

በ2012 የትምህርት ዘመን ከ 7 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን መዝግቤ ለማስተማር እየሰራሁ ነው አለ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ፡፡ በመላው የክልሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም ሁለት ብቻ መሆኑን ወላጆች አውቀው ልጆቻቸውን ከወዲሁ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ እንዳሉት በ2012 የትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን፤ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል 4 ነጥብ 7 ሚሊየን፤ ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ደግም 6 መቶ 81 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመን አላርም ትሁነን!

•ከ70 ሺህ በላይ ንፁሃን ህይወታቸውን አጥተዋል!
•ከ11 ሺህ በላይ ዜጎች አካላቸው ጎድሏል!
•24 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል!
•ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ብቻ 85 ሺህ እድሜያቸው ከ5 ዐመት በታች የሆኑ ህፃናት በምግብ እጥረት ሞተዋል!
•በርካታ ሚሊዮን ዜጎች ቤታቸውን ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል!

ብልቂሳ አብደላ ከ20 ዓመታት በላይ በየመን ነዋሪ ናት ይህንን ብላለች፦ "ወላሂ! የጦርነት ጥሩ ነገር የለም፤ የመንን ያየ... ሰላም የሆነውን ሀገር ባያደፈርሱ ጥሩ ነው። ...ኢትዮጵያ ችግር አለ ሲባል የመንን፣ ሶሪያን፣ ኢራቅን አላዩም ወይ...የመን እንኳን አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት ነው፤ ይሄ ደግሞ የተለያየ ስላለ ከጀመረ የሚያቆም አይመስለኝም"

የመን ለምን እንዲሆነች??
•አለመደማመጥ
•ምክንያታዊ ሆኖ አለማሰብ

#የመናውያን መነጋገርና መደራደር የሚለውን #አማራጭ ባለመተግበራቸው ለዚህ ችግር ተጋልጠዋል። ጦርነት ሩቅ አይደለም፤ በፖለቲካና በሃይማኖት መካረሩ መዳረሻው ግልፅ ነው👉ጦ ር ነ ት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

Via #SRTA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የአለታ ወንዶ የመረዳጅ #ዕድር አባላት በአለታ ወንዶ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ800 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

Via #SRTA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
ሚዛን አማን⬆️

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ከቤንች ሸኮ እና ከምእራብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ጋር ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ በዚህ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ላይ የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በዞኑ ያሉ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ📸ይሄ ደግሞ ሀዋሳ መግቢያ #ቶጋ አካባቢ የደረሰ የመኪና አደጋ ነው። በአደጋ ስለደረሰው ጉዳት ወደበኃላ መረጃዎችን ሰብስበን እናሳውቃለን። @tsegabwolde @tikvahethiopia
የሁለት ሰው ህይወት አልፏል!

ከቢሻንጉራቻ ከፍ ብሎ ልዩ ቦታ ውሻሎ ምርጥ ዘር አካባቢ በዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ8 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን በምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ጉሳ ዴኮ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-03954 አይሱዙ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ ሲመጣ ባልታወቀ ምክንያት የቀኙን መስመር ለቆ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣው ኮድ 3-0739 በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ በሚጠራው ሚኒ ባስ መኪና ጋር ተጋጭተው ዶልፊን ሚኒ ባስ መኪና ውስጥ ከነበሩት ሰዎች አስሩ ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በዚህም ለህክምና አቅራቢያ ወደሚገኘው ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደው እየተረዱ የሚገኙ ሲሆን በአደጋው የ2 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ ቀሪዎቹ 6 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ጊዜው ክረምት በመሆኑም አሽከርካሪዎች ሲያሽከረክሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የፍጥነታቸውን ወሰን እንዲጠብቁ ኢንስፔክተሩ አሳስበዋል፡፡

Via #SRTA
ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪን ለመቆጣጠር እንዲቻል መመሪያ ተዘጋጀ!

በግል ትምህርት ቤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተደረገ ያለውን የተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪን ለመቆጣጠር እንዲቻል መመሪያ መዘጋጀቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የመማር ማስተማር እና ምዘና ዘርፍ ኃለፊው አቶ ተሰማ ዲማ ለደ.ሬ.ቴ.ድ እንዳስታወቁት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በተለይም በከተሞች የግል ትምህርት ቤቶች በየጊዜው ምክንያታዊ ያልሆነ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ቢሮው ጥቆማ ይደርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶችን የመማር ማስተማር ሥራ የሚከታተልበት አሠራር ያለው ቢሆንም ክፍያን በተመለከተ መቁረጥ ስለማይችል ትምህርት ቤቶቹ ሊመሩበት የሚገባውን መመሪያ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ቢሮው ከግል ትምህርት ቤቶች ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የትምህርት ቤት ክፍያ ላይ ጭማሪ ከማድረጋቸው አስቀድሞ በዓመቱ ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ባሉት ወራት ከተማሪ ወላጆች ጋር በጥልቀት በመነጋገርና ምክንያቶችን ዘርዝረው የማስቀመጥ ኃላፊነት እንዳለባቸውም በመመሪያው ላይ በግልጽ መቀመጡን አብራርተዋል፡፡

የተማሪ ወላጆችና ማህበረሰቡ ያላመነባቸው የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ በአሠራሩ መሠረት ተቀባይነት እንደሌለው አውቆ በየአካባቢውና ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው ቦታዎች ህዝቡ መብቱን እንዲያስከብርም አቶ ተሰማ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግና ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያላትን ማንኛውንም ጥያቄ በውይይት በአጭር ጊዜ ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው ትላንት በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ በተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፦

•የመስቀል በዓል የፍቅርና የይቅርታ በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።

•በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስና እንዳይደናቀፍ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን የበኩላቸውን ድጋፍና አስተጽፆ እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

•ሀዋሳ ከተማ ቀድሞ የምትታወቅበት የፍቅር፣ የሰላምና የመቻቻል ከተማነቷን ዳግም እንዳገኘች አንስተዋል።

•ከተማዋ አሁን ላለችበት ሁኔት የህዝቡና ነዋሪዎች ጥረት እንደሆነ አንስተው በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ስራዎችም ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል።

•ከተማዋ አሁን ባለችበት እንድትቀጥልም ከነዋሪዎችና ከመላው ህዝብ ጋር የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

•ምክትል ከንቲባው አዲሱ ዓመትና የመስቀል በዓል የሰላም፣ የልማት የብልጽግና እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#SRTA
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvagethipia
#ጊፋታ2012

የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ ላለፉት ሳምንታት በደመቀ መልኩ በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ዛሬም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ አመራሮችና የብሄሩ ተወካዮች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳሳቢው የመንገድ ትራፊክ አደጋ!

በደቡብ ክልል የመንገድ ትራፊክ አደጋ እየጨመረ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ከባለፈው ሐሙስ እስከ እሁድ መስከረም 18/2012 ዓ.ም በአራት ቀናት ብቻ 22 አደጋ የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 6 የሞት አደጋ፣ 14 ከባድ የአካል ጉዳት እና 2 ቀላል የአካል ጉዳት ያስከተለ አደጋ ተመዝግቧል ሲሉ በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር የትንተና ባለሙያ ምክትል ሳጂን ተመስጌን አረጋ ገልፀዋል፡፡

አብዛኛው የአደጋዎቹ መንስኤዎች የአሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለትና ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ያሳለፍነው ሳምንት የበዓል ሳምንት መሆኑ ለአደጋው መጨመር እንደ ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል ሲሉ ምክትል ሳጂን ተመስጌን አረጋ አክለዋል፡፡ በመሆኑም በአራቱ ቀናት ብቻ 9 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ 19 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ከተማ የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና የሞት አደጋ አደረሰ!

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ከተማ የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና ከጥንቃቄ ጉድለት ቅዳሜ ዕለት በአንድ ሰው ላይ የሞት አደጋ ማድረሱን የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ማስቆም ዳይሬክቶሬት የመረጃ ትንተና ባለሙያ መክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ ገልጸዋል፡፡

አደጋው የደረሰው ሁለት የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪናዎች በተከታታይ ቆመው ከነበሩበት የአንደኛው መኪና ረዳት መኪናውን ሲያንቀሳቅስ በፈጠረው ስህተት የሌላኛውን ኤፍ ኤስ አር መኪና መስተዋት በመወልወል ላይ በነበረው ረዳት ላይ አሰቃቂ አደጋ በማድረሱ የረዳቱ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ መክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ አስረድተዋ፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን የሞት አደጋ ጨምሮ በደቡብ ክልል ከባለፈው መሰከረም 22/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአራቱ ቀናት ብቻ 13 ያህል የትራፊክ አደጋ መድረሳቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከ13 አደጋዎች 5ቱ የሞት 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳትና ሁለት ቀላል የአካል ጉዳት ያስከተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአብዛኘው የአደጋ መንስኤዎች ለእግረኛ ቅድሚያ ያለመስጠት፣ የአሽካርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለትና ፍጥነት ናቸው፡፡ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ በማድረግ ፍጥነታቸውን ገድበው ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ምክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት በቡታጀራ ከተማ!

ከ 1 መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዋንም ጨምሮ የአለም ሀገራት የእስልምና እምነት ተከታዮችን እንግዶች ተቀብላ እያስተናገደች ነዉ። "አበሻ እጅቲማዕ" በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ በሀገራችን ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደዉን ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት ነዉ። ከህንድ ፣ከሱዳን ፣ከኬንያና ከሌሎች የአለም ሀገራት የተዉጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊ ናቸዉ።

ከ1 መቶ ሺህ በላይ አትዮጵያዉያን ጨምሮ የአለም ሀገራት እያስተናገደች ትገኛለች። "አበሻ እሽቲማ" ዳዕዋ ከሕዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማለት እስከ እሁዱ የሚቀጥል ነዉ፡፡

የከማዉ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸዉን ለእንግዶች ክፍት አድርገዉ እንግዳ የመቀበል ባህላቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ እያንጸባረቁ ነዉ። ከተለያዩ የአለም ሃገራት ማለትም ከአፍሪካና ከአውሮፓ ሃገሮች ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ የእስልምና የእምነቱ ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊዎች ናቸዉ።

(Gurage Zone Administration Public Relation Office)

#SRTA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኩቤ ካባ ተብሎ በሚጠራው የድንጋይ ማምረቻ ካባ ተደርምሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ!

በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኩቤ ካባ ተብሎ በሚጠራው የድንጋይ ማምረቻ ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ የድንጋይ ካባ ተደርምሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የድንጋይ ከባው ለረዥም ዓመታት ለሀዋሳ ከተማ እና አካባቢው ለግንባት የሚውል ድንጋዮች የሚመረትበት ሲሆን በዛሬው ዕለት በደረሰው የካባ ድንጋይ መናድ በሁለት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ የደረሰ ሲሆን በሦስት ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

ሟቾቹሁ የድንጋይ ካባውን በማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩት የስካቫተር ሹፌርና የጉልበት ሰራተኛ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሌሎች ጉዳት ደረሰባቸው ተጎጂዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆን ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ ገልፀው የአደጋው ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

[ምንጭ፦ #SRTA, PHOTO : Tikvah Family]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ስታድየም ደርሰዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝም በጂንካ ስታዲየም ተገኝተዋል። የአገር ሽማግሌዎች ኘሮግራሙን በምርቃት ጀምረዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስታዲየሙ ለተገኘው ህዝብ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።

#SRTA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ #ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ከመጪው ሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፊትና የአፍ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ እንደሚኖርባቸው አሳውቋል።

ይህን መመሪያ በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ መምሪያው በጥብቅ አስታውቋል፡፡

መመሪያው በመላው ሀገሪቱ #እየጨመረ የሚገኘውን ፤ እንዲሁም ወደ ከተማው የመግባት አዝማሚያ እያሳየ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ይረዳል ተብሎ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ረዳቶችና ተሳፋሪዎችን ፤ እንዲሁም የግልና የመንግስት መኪና አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን፤ ባጃጅና የመሳሰሉትን አነስተኛ የትራንስፖት ዘርፎች የሚያካትት ነው።

አሽከርካሪዎች ይህንን አውቀው በቀጣይ ሁለት (2) ቀናት ውስጥ ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የፊት ማስኮችን አድርገው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡

#SRTA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬ መሰጠት ተጀመረ። #SRTA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በሐመር ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል !

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን ከማሳ ላይ ፈጥኖ መሰብሰብ እንደሚገባም ተገልጿል። #SRTA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል።

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ 30 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኝ DRS ድርጅት ግዢ እንደተፈጸመና ቢሮ መግባቱን አሳውቋል።

የቅጽ አሟላሉን በተመለከተ በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም የፈተና ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ቢሮው ገልጿል።

በክልሉ የሚገኙ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች ፎርሙን ወስደው በመንግስትና በግል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እያስሞሉ ነው ተብሏል።

የፈተና ዝግጅት ተጠናቆ የህትመት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ፈተናው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30/2013 ይሰጣል ተብሏል። #SRTA

@tikvahethiopia
#ማሻሻያ

በደቡብ ክልል ለአስቸኳይ አዋጁ ማስፈጸሚያ የተጣሉ ገደቦች ላይ ማሻሽያ መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ነዋሪዎች እጅ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ለመመዝገብ እስከ ህዳር 10/2014 ድረስ በገደብ የተያዘ ስራ የተሰራ ሲሆን በዚህም ወቅት 27 ሺሕ 477 የጦር መሳሪያዎች ተመዝግቧል።

ነገር ግን በክልሉ አለ ተብሎ ከሚገመተው አንጻር ቁጥሩ ዝቅተኛ ነው።

የምዝገባው ጊዜ አጭር በመሆኑና በተላያዩ ምክንያቶች የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እስከ ሕዳር17/2014 ዜጎች በእጃቸው ያለውን የጦር መሳሪያ በአፋጣኝ ወደ ሚመለከተው አካል ቀርበው እንዲያስመዘግቡ ተብሏል።

ይሄን መመሪያ ተላልፈው የጦር መሳሪያ ይዘው በተገኙ ግለሰቦች ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።

እስካሁን ባለው ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለ 2 ሞተር ሳይክሎች ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ሰርዓት የገቡ ሲሆን አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሞተር ሳይክሎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ምዝገባው አልመጡም።

በዚህም ተጫማሪ ሰባት ቀናት የምዝገባ እድል የተሰጠ በመሁኑ ባለንብረቶች እስከ ህዳር 17/2014 ድረስ እድሉ እንዲጠቀሙ ተብሏል።

ከዚህ በፊት በ2 እግር ሞተር ስይክልና ባለ3 እግር ባጃጆች እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ የተላለፈ ሲሆን አሁን ግን ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ ፍቃድ ተሰጥቷል።

ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ተነስቶ በጥብቅ ቁጥጥር ተተክቷል።

#SRTA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ዛሬ እና ነገ ይመሰረታል። 5 ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው የሚያቋቁሙት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዛሬና ነገ በሚካሄዱ መርሀ ግብሮች 11ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ይመሰረታል፡፡ ለክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ከትላንት ምሽት ጀምራ የክልል እና የፌደራል እንግዶች ለክልሉ…
#Update

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በሀገራችን 11ኛው የክልል መንግሥት በይፋ ይመሰረታል።

11ኛው የክልል መንግሥት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቦንጋ ከተማ ይመሰረታል።

በቦንጋ እየተካሄደ በሚገኘው የክልል ምስረታ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችና ከ6ቱም መዋቅሮች የተገኙ የህዝብ ተወካዮች፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

#SRTA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ ጠዋት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስ ግቢን የሚያገኛኘው ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ እና ሁለት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህን የገለፀው የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ነው።

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " እስከአሁን ባለው ሂደት በጉዳቱ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል " ብለዋል።

እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተው አካል ብቻ በማግኘት እንዲያረጋግጡና እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#SRTA

@tikvahethiopia