TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MeskelSquare መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያየ። ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መንፈሳዊና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ የተነሱ የመብትና የይዞታ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም አንቲባ አዳነች አቤቤ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 3 ረፋድ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጉባኤ አካሒዷል። በጉባኤውም ላይ ከፍ ሲል የተገለጸውን…
#Update

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጤና ችግር አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል።

ቅዱስነታቸው ፥ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ዶ/ር ቴድሮስ ምን አሉ ? የአፋር እና የአማራ ክልል ባለስጣናት ምን መለሱ ?

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ፦

" 7 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት ክልል ከአንድ አመት በላይ ሙሉ በሙሉ ከበባ ውስጥ ሆናል።

በዚህ ምክንያት ህዝቡ ምንም አይነት የምግብ አቅርቦት፣ የህክምና ፣ ኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን ፣ የመገናኛ አገልግሎት አያገኝም።

በመድሃኒት አቅርቦት እጥረት ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው። በምግብ እጥረት ምክንያት እንደዚሁ ብዙዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ከዚያ በላይ በየቀኑ የሚሰነዘረው የድሮን ጥቃት ሰዎችን እየገደለ ነው " ብለዋል።

የአፋር ክልል አዳአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ ፦

" የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ወደትግራይ በአፋር #አብዓላ በኩል የምግብ እርዳታ ሲጓጓዝ ቆይተዋል።

በቅርብ ጊዜ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ዓለም ያውቀዋል።

መጀመሪያ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባበት አማራጭ መንገድ የለም፤ ለምን ? በአፋር አብአላ በኩል ያለውን ጦርነት እራሳቸው ከፍተው በአብአላ በኩል ጦርነት እያካሄዱ ነው እነሱ። በቆቦም በኩል ጦርነት እየተካሄደ ነው።

እናስገባ ቢባል እንኳን ሁሉም መግቢያ በሮቹ በአፋር በኩል ነበር እስከዛሬ የሚገባላቸው እርዳታ የሚገባው በዛ በኩል እራሳቸው ጦርነት ከፍተው ወረራ አድርገው በአብዓላ ከተማ እስካሁን ድረስ በመድፍ እየደበደቡ ስለሆነ እርዳታ የሚገባበት አማራጭ የለም።

እሱ (ዶ/ር ቴድሮስ) ለህወሓት ፕሮፖጋንዳ ነው እንዲህ የሚያደርገው እንጂ የመግቢያ መንገዶቹ በሙሉ የጦርነት ቀጠና እንደሆኑ ያውቃል። " ብለዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጅዓለም ፦

" ህወሓት ቀበሌ ከምትገኝ የጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ትልልቅ ሆስፒታሎች ድረስ የሚችለውን ዘርፎ መውሰድ የማይችለውን አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎ አውድሟል።

ይሄ እንግዲህ መላው የዓለም አቀፍ ተቋማት በግላጭ የሚያውቁት ነው። ይህን እንኳን ሲያወግዙ አይሰማም።

በተመሳሳይ ጠላት ከወጣ በኃላ እነዚህ አካባቢዎች ከፍተኛ የመድሃኒት ችግር ፣ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችል ቁመና ላይ አይደሉም ያሉት ጤና ተቋማቱ መልሶ ለማቋቋም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት አንድም አስተዋጽዖ እያበረከተ አይደለም " ብለዋል።

ያብቡ : https://telegra.ph/WHO-01-14-2
#ሹመት

ኢንጅነር የኋላሸት ጀመረ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኢንጅነር የኋላሸት ጀመረ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሹመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥር 3 ቀን 2014 ጀምሮ ነው ኢንጅነር የኋላሸት ጀመረን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው የሾሟቸው።

@tikvahetiopia
ፎቶ : 350 የሶማሊያ ወታደሮች ' መሰረታዊ የኮማንዶ ስልጠና ' ከኳታር የተውጣጡ የስልጠና ባለሞያዎችን በማካተት እየተሰጠ መሆኑን የቱርክ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለወታደሮቹ ስልጠናው እየተሰጠው የሚገኘው በቱርክ የፀረ-ሽብርተኝነት ስልጠና እና መለማመጃ ማዕከል (Isparta) ዕዝ ውስጥ ነው።

ቱርክ እና ኳታር በሶማሊያ በፖለቲካ ውስጥ እንዲሁም በወታደራዊ ዘርፍ ላይ ተፅእኖ እንዳላቸው ይነገራል።

@tikvahethiopia
#Update

የደሴ - ወልዲያ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተገባደደ ነው።

ፍተሻው በስኬት ከተጠናቀቀ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች በሰዓታት ውስጥ ኤሌክትሪክ ሊያገኙ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ተቋሙ እስከዛሬ ድረስ በተከናወነው ጥገና ጉዳት የደረሰበት መስመርና ምሰሶ ከ97 በመቶ በላይ ተጠናቋል ብሏል።

ቀሪ ሥራዎችን በርብርብ በማጠናቀቅ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች ማምሻውን አልያም እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ መብራት እንዲያገኙ ይደረጋል ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል የሚያደርጉትን ጉዞ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ጀመሩ።

በፓርቲው ፕሬዜዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአመራሮች ቡድን ዛሬ ወደ አፋር ክልል ገብተዋል።

ቡድኑ በአፋር የዛሬ ውሎው ከሰመራ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በማቅናት በግንባር የተጎዱ የጦር አባላትን ጠይቋል።

ባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የጦር አባላቱ በግንባር ለከፈሉት የህይዎት እና የአካል መስዕዋትነት የተሰማቸውን ታላቅ ክብር በራሳቸውና በድርጅቱ ስም ገልፀው ዕውቅናም እንደሚሰጡት ተናግረዋል።

በአፋር ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የአፋር ልዩ ኃይል፣ የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት እና ሚሊሻ እንዲሁም ቁስለኛ የህወሓት ሰራዊት አባላት እንደሚገኙ ተገልጿል።

አመራሮቹ ከሆስፓታል መልስ በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሠረት በአፋር ዱፍቲ በአዋሽ ወንዝ እየለማ ያለውን የስንዴ ምርት መጎብኘታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በአፋር ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ አማራ ክልል እንደሚያመሩ ይጠበቃል።

ፎቶ ፦ ባልደራስ ፓርቲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ጄነራል ባጫ ደበሌ በትግራይ ክልል ተፈፅመዋል ስለተባሉት የአየር ጥቃቶች ለጀርመን ሬድዮ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" የትግራይ ህዝብ ከማንም በላይ ለእኔ ወንድሜ ነው፤ ህዝባችን ነው። ከማንም በላይ የምንሳሳለት እኛ ነን። አየር ኃይል ይሁን፣ እግረኛ ይሁን ፣ መድፈኛ ይሁን ፣ የድሮን ቡድን ይሁን፣ ሁሉም Rules of engagement (ROE) አላቸው ንፁሃን ዜጎችን በአየር የሚደበድብ ማንም እብድ የለም አልተደረገም። " ብለዋል::

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ምን አለ ?

" በትግራይ ክልል በሚፈጸሙ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ሳቢያ ከ100 በላይ ሰላማዊ ዜጎች መገደልና የንብረት ውድመትን በተመለከተ የደረሱን ሪፓርቶች አሳስቦናል:: ባለፉት ሁለት ሳምንታት ቢያንስ 108 ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል 75 ሰዎች ቆስለዋል:: " ብሏል::

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-01-14
#AmharaRegion

የአማራ ክልል መንግስት ከፋኖ አደረጃጀት ትጥቅ እንደማያስፈታ አስታወቀ::

" መንግስት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው " የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ ነው ሲል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ገልጿል::

የክልሉ መንግሥት ይህን የገለፀው ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር በተወያየበት መድረክ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል::

በዚሁ መድረክ : " ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ሆነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም " ተብሏል::

በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችል ተገልጿል።

በውይይት መድረኩ ላይ " ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ:: ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ሆኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል ነው " ተብሏል::

@tikvahethiopia
#Abala

በአፋር ክልል ፣ አብአላ ከተማ በሚሰነዘር የከባድ መሳሪያ ድብደባ የከተማው ነዋሪ ከቄዬው እየተሰደደ መሆኑን የከተማው ከንቲባ ተናገሩ።

ከንቲባው ይህን የተገሩት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ከመቐለ ከተማ 40 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው የአፋር የንግድ ከተማ አብአላ ከንቲባ አቶ ጣሂር ሀሰን ህወሓት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት የአፋር እና አማራ ክልሎች እንዲወጣ ከተደረገ በኃላ አብአላ ላይ ተደጋጋሚ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

የከተማው ከንቲባ ፥ " አሁንም ድረስ አላቋረጠም ንፁሃን መደብደብ ፤ በከባድ መሳሪያ መደብደብ እንስካሁን አላቆመም። በእግረኛም ወረራ እየሞከረ ነው። መጀመሪያውንም እንደሚታወቀው በየአካባቢው የሚያደርገውን ወረራ እና የንፁሃን ጭፍጨፋ ሙከራ ነው ያደረገው ያኔም አልተሳካለትም እስካሁን አላቋረጠም። በከባድ መሳሪያ ንፁሃንን እየደበደበ ነው፤ በእግረኛም እየሞከረ ነው ዘረፋ ለማድረግም እየሞከረ ነው ቢሆንም ግን አልተሳካለትም። ወደላይ ተመልሷል እስካሁን ግን የቆመ ነገር የለም ፤ ከከተማው ራቅ ብሎ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው " ብለዋል።

እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ከንፁሃን በተጨማሪ የአምልኮ ቦታዎች ፣ የመንግስት እና የግል ባለሀብቶች ንብረት ላይ ጉዳት መደረሱ ተገልጿል።

የደረሰውን ጉዳት በቁጥር ደረጃ ለመግለፅ ጥናት እየተደረገ መሆኑን የአብአላ ከንቲባ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia