TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር ቴድሮስ ምን አሉ ? የአፋር እና የአማራ ክልል ባለስጣናት ምን መለሱ ?

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ፦

" 7 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት ክልል ከአንድ አመት በላይ ሙሉ በሙሉ ከበባ ውስጥ ሆናል።

በዚህ ምክንያት ህዝቡ ምንም አይነት የምግብ አቅርቦት፣ የህክምና ፣ ኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን ፣ የመገናኛ አገልግሎት አያገኝም።

በመድሃኒት አቅርቦት እጥረት ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው። በምግብ እጥረት ምክንያት እንደዚሁ ብዙዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ከዚያ በላይ በየቀኑ የሚሰነዘረው የድሮን ጥቃት ሰዎችን እየገደለ ነው " ብለዋል።

የአፋር ክልል አዳአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ ፦

" የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ወደትግራይ በአፋር #አብዓላ በኩል የምግብ እርዳታ ሲጓጓዝ ቆይተዋል።

በቅርብ ጊዜ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ዓለም ያውቀዋል።

መጀመሪያ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባበት አማራጭ መንገድ የለም፤ ለምን ? በአፋር አብአላ በኩል ያለውን ጦርነት እራሳቸው ከፍተው በአብአላ በኩል ጦርነት እያካሄዱ ነው እነሱ። በቆቦም በኩል ጦርነት እየተካሄደ ነው።

እናስገባ ቢባል እንኳን ሁሉም መግቢያ በሮቹ በአፋር በኩል ነበር እስከዛሬ የሚገባላቸው እርዳታ የሚገባው በዛ በኩል እራሳቸው ጦርነት ከፍተው ወረራ አድርገው በአብዓላ ከተማ እስካሁን ድረስ በመድፍ እየደበደቡ ስለሆነ እርዳታ የሚገባበት አማራጭ የለም።

እሱ (ዶ/ር ቴድሮስ) ለህወሓት ፕሮፖጋንዳ ነው እንዲህ የሚያደርገው እንጂ የመግቢያ መንገዶቹ በሙሉ የጦርነት ቀጠና እንደሆኑ ያውቃል። " ብለዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጅዓለም ፦

" ህወሓት ቀበሌ ከምትገኝ የጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ትልልቅ ሆስፒታሎች ድረስ የሚችለውን ዘርፎ መውሰድ የማይችለውን አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎ አውድሟል።

ይሄ እንግዲህ መላው የዓለም አቀፍ ተቋማት በግላጭ የሚያውቁት ነው። ይህን እንኳን ሲያወግዙ አይሰማም።

በተመሳሳይ ጠላት ከወጣ በኃላ እነዚህ አካባቢዎች ከፍተኛ የመድሃኒት ችግር ፣ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችል ቁመና ላይ አይደሉም ያሉት ጤና ተቋማቱ መልሶ ለማቋቋም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት አንድም አስተዋጽዖ እያበረከተ አይደለም " ብለዋል።

ያብቡ : https://telegra.ph/WHO-01-14-2
TIKVAH-ETHIOPIA
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_19_Feb_2022.png
#SituationReport :

#Tigray #Amhara #Afar📍

የሰሜን ኢትዮጵያ #ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ወይም #UN_OCHA የዚህን ሳምንት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

#Afar

• በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች #አሁንም ግጭት ቀጥሏል። በዋናው ኮሪደር (A1) [አፋር ሰመራን ከመቐለ ትግራይ የሚያገናኘው] እና ትግራይ እና አፋር በሚዋሰኑባቸው ኤሬብቲ ፣ በርሀሌ እና መጋሌ ወረዳዎች ፣ በኡሩህ እና ዋህዲስ ቀበሌዎች፣ በሁሉም የኬልበቲ ዞን ግጭት መኖሩ ተመላክቷል።

• በአፋር ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። መጠነ ሰፊ መፈናቀል በመኖሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

• በአፋር ክልል በተከሰተው ግጭት እስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የተፈናቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ በመጋሌ፣ በርሀሌ፣ ኮነባ፣ ኢረብቲ እና ዳሎል ወረዳዎች መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ። አካባቢዎቹ በመንገድ ሁኔታ እና በፀጥታ ስጋት ምክንያት ለሰብአዊ አጋሮች ተደራሽ አይደሉም።

#Tigray

• በትግራይ ክልል እ.ኤ.አ. የካቲት 12 በምስራቅ ዞን አፅቢ ከተማ ላይ በደረሰ የአየር ድብደባ የንፁሀን ዜጎች ህይወት መጥፋቱ እና ሰዎች መቁሰላቸውን ተመድ አመልክቷል። የተመድ አጋሮች እስካሁን የተጎጂዎችን ቁጥር ማረጋገጥ እንዳልቻሉ ተገልጿል።

• በትግራይ ክልል በአብዛኛው ሰሜናዊ ክፍል [ከኤርትራ ድንበር በሚዋሰኑ ቦታዎች] የተወሰኑ ቀበሌዎች በማዕከላዊ ዞን ራማ ፣ በምስራቅ ዞን ኢሮብ፣ በምስራቅ ዞን ዛላ አምበሳ ከተማ ጨምሮ ተደራሽ አይደሉም። በእነዚያ አካባቢዎች ላለፉት ጥቂት ወራት ምንም አይነት እርዳታ ሳያገኙ የቆዩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች አሉ።

• እኤአ ከታህሳስ 15 አንስቶ የፀጥታ ችግሮችና ግጭቶች ወደ ትግራይ ክልል በየብስ በ #ሰመራ- #አብዓላ- #መቐለ መንገድ እርዳታ እንዳይገባ እንዳገዱ ይገኛሉ። ከታህሳስ አጋማሽ በፊት ተፈቅዶ የነበረው የአቅርቦት መጠን በዋናነት በቢሮክራሲያዊ እክል ከሚያስፈልገው በታች በመሆኑ አሁን በፀጥታ ችግር እና በግጭት መንገድ መዝጋቱ ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰውን የሰብአዊ አቅርቦት ችግር የበለጠ እንዳባባሰው ተገልጿል።

• እ.ኤ.አ. ከሀምሌ 12 አንስቶ አጠቃላይ 1,339 የጭነት መኪናዎች ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል የገቡ ሲሆን ይህ በትግራይ ክልል ያለውን ሰፊ ​​የሆነ የሰብአዊ ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስፈልጉት አቅርቦቶች ውስጥ 8 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ተጨማሪ 17 የጭነት መኪናዎች ባለፈው ህዳር ወር ከኮምቦልቻ ፣ አማራ ክልል ወደ ትግራይ ገብተው ነበር።

• የዓለም ጤና ድርጅት-WHO የላከው የህክምና ቁሳቁሶች መቐለ ቢደርሱም አጋር አካላት በነዳጅ እጥረት ምክንያት በክልሉ ወዳሉ ጤና ተቋማት መላክ እና ማከፋፈል እንዳልቻሉ ተመድ ገልጿል። በተለይም ከ800 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ወዳስጠለለው የሰሜን ምእራብ ዞን ማድረስ አልተቻለም። በዞኑ ከአጠቃላይ የውስጥ ተፈናቃይ 1.8 ሚሊዮን 44 % ይሸፍናል።

• በሰሜን ምዕራብ ዞን ተፈናቃዮችን ባስጠለሉ ቦታዎች የእከክ በሽታ እና ወባ ኬዞች መጨመራቸው ተመላክቷል። ከ1,100 በላይ የእከክ በሽታ ኬዝ በ22 ሳይቶች ፣ከ1800 በላይ የወባ ኬዞች በዞኑ ከዓመቱ መጀመሪያ (የፈረንጆች) ጀምሮ ተመዝግቧል። የአቅርቦት ችግር፣ የመድሃኒትና የነዳጅ እጥረት ተመድ የጤና አጋሮቹ የበሽታዎችን ስርጭት እንዲቀንስ ለማድረግ የሚሰሩትን ስራ እየገደበ መሆኑን ገልጿል።

• ተ.መ.ድ. በትግራይ ክልል ላሉት የሰብአዊ ድጋፍ አጋሮቹ ያለው ነዳጅ፣ ጥሬ ገንዘብ እና አቅርቦቶች በጣም አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ይህም ሁኔታ የሰብአዊ አገልግሎቶችን በተለይም የምግብ ፣ የውሃ ፣ የጤናና የስነ - ምግብ አገልግሎቶች ስርጭትን በእጅጉ እየቀነሰው መሆኑን አመልክቷል።

#Amhara

• በአብዛኛው የአማራ ክልል በአንጻራዊ የተረጋጋ ሁኔታ ያለ ሲሆን በሰሜን ወሎ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ግን ውጥረት እንደነገሰበት ነው።

• አማራ ክልልን ከትግራይ ክልል የሚያዋሱ አካባቢዎች አሁንም ባለው የፀጥታና የደህንነት ስጋት ተደራሽ አይደሉም። መድረስ አልተቻለም። ይህም በሰሜን ጎንደር፣ ዋግ ኽምራና ሰሜን ወሎ ያሉ አካባቢዎች ያካትታል። ባለው ሁኔታ ህዝቡ የአስፈላጊ የምግብ እደላ ጨምሮ አጠቃላይ ሰብአዊ ርዳታ እንዳያገኝ ሆኗል።

• በሰሜን ጎንደር ፣ ዋግ ኽምራ እንዲሁም ሰሜን ወሎ ዞኖች አካባቢዎች አዲስ መፈናቀል መኖሩ ተመላክቷል።

• በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። በርካታ ሰዎች በተደጋጋሚ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በአዋሳኝ አካባቢ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖች ውስን የሰብዓዊ ዕርዳታ ብቻ እንዳገኙ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ በዋናነት በዝቋላ ወረዳ እና ሰቆጣ ወረዳ በአሁኑ ወቅት ከ30,000 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

• ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ12,000 በላይ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ራያ ቆቦ አማራ ክልል ገብተዋል።

• በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ ከ21 ሺ የሚበልጡ ተመላሾች አስቸኳይ የመጠለያ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የመኖሪያ ቤታቸውን መልሶ የማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በዞኑ ሆስፒታሎችና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶችና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የመንግስት ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@tikvahethiopia