TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CAIRO

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የሶስትዮሽ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በግብጽ ካይሮ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ነው።

ስብሰባው በዋናነት የሶስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓመት መስከረም እና የካቲት 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት እና የግድቡን የውሃ አሞላል እና አለቃቅ በተመለከተ ከተደረገው ውይይት የቀጠለ ነው።

https://telegra.ph/ETH-09-15-5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢዜማ አመራሮች በመቐለ ነዋሪዎች ምን ተጠየቁ?

የ2012 ምርጫ በተያዘለት ቀነገደብ እንዲካሄድ ለምርጫው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች መጠናቀቅ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ/ኢዜማ/ አስታወቀ። ፓርቲው ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል አውግዞታል።
____________________________________________

•ስለሚመጣው ምርጫ ምንድነው አቋማችሁ?
•ስለምርጫ መራዘም የናተ ግልፅ የሆነ አቋም ምንድነው?
•ኢሳት ከዚህ በፊት ስላወጀው የዘር ማጥፋት ዘመቻ የኢዜማ አቋም ምንድነው?

በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠውን ምላሽ ከላይ ባለው ቪድዮ መከታተል ትችላላችሁ!

Via DW አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚክ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሃገራት በቀጠናው ያለውን የደህንነት ስጋት ለመቅረፍ 1 ቢሊየን ዶላር ለመመደብ ተስማሙ። ሃገራቱ በቡርኪናፋሶ ሲያደርጉት ከነበረው ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ በሳህል ቀጠና አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖችን ለመከላከልና የአካባቢውን ደህንነት ለማስጠበቅ የ1 ቢሊየን ዶላር ለመመደብ መስማማታቸውን ገልጸዋል። #FBC

@tikvahethiopia @tsegabwolde
#update ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ምርጡ አለም አቀፍ ውድድር" በመባል ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጎዳና ላይ ሩጫ "ምርጡ አለም አቀፍ ውድድር" ተብሎ የተመረጠው አጠቃላይ ድምጽ 56 በመቶ በማግኘት ነው፡፡

ምንጭ፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚዛን አማን⬆️

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ከቤንች ሸኮ እና ከምእራብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ጋር ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ በዚህ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ላይ የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በዞኑ ያሉ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል!" ሐሰን ጃበር የተባሉ ሊባኖሳዊ የንግድ ሰው በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀናት ትራንዚት በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው እንደተወሰዱ እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል። በዕለቱ ከአፍሪካዊቷ አገር ጋቦን በመነሳት በአዲስ አበባ አድርገው ወደ ሊባኖስ ቤሩት በማምራት…
#update ታግቶ ሳይሆን አይቀርም የተባለው የሊባኖስ ዜግነት ያለው ነጋዴ እንዚሁ ሀገራችን ላይ ታስሮ እንደነበር ተሰምቷል። እንደ AP ዘገባ ከሆነ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሊባኖሱን ነጋዴ ከእስር ፈታዋለች። የሊባኖስ ባለስልጣናት ቤይሩት ያሉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችን ጠርተው "ለምን እንደታሰረ አስረዱ፣ ካልሆነ ተመሳሳይ እርምጃ እንወስዳለን" ማለታቸውን AP ጨምሮ ዘግቧል። ቤይሩት ያሉ ኢትዮጵያውያንም "ዜጋችን ሀገራችሁ ላይ ታስሯል" እየተባሉ እንግልት ሲደርስቸው እንደነበር የAP ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ዘግቧል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2011 የህዳሴግድብ የቦንድ ሽያጭ በአንድ ቢሊዮን ብር ማሽቆልቆሉ ተሰማ!

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ወጪን ለመሸፈን ታስቦ ለህዝብ ሲቀርብ የነበረው የቦንድ ሽያጭ በ2010 ከነበረበት 2.14 ቢሊዮን ብር ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በማሽቆልቆል በተገባደደው የ2011 በጀት ዓመት 970 ሚሊዮን ብር ብቻ ሆኖ ተመዘገበ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሔራዊ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት የሚዲያ ግንኙነት ኀላፊ ኃይሉ አብርሃም ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በግድቡ መዘግየት እና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት ህብረተሰቡ አመኔታ ማጣቱን እንደ ምክንያት ገልፀው ይህም የቦንዱን ሽያጭ አቀዛቅዞታል ብለዋል።

‹‹የህዳሴው ግድብ ግንባታ #ቆመ የሚል አመለካከት በመፈጠሩ ምክንያት ሀብት ከማሰባሰብ ይልቅ ማህበረሰቡ ጋር ያለውን የመረጃ ብዥታ ማጥራት ላይ ትኩረት አድርገን ስንሠራ ቆይተናል›› ሲሉም ተናግረዋል።

https://telegra.ph/ETH-09-16

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በክልሉ የመንግስት ተቋማት ላይ ድንገተኛ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ በጉብኝቱ እስካሁን የገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ፣ የትራንስፖርት ቢሮ እና የሌሎችንም ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡ የርዕሰ መስተዳድሩ ድንገተኛ ጉብኝት ተቋማቱ ያሉባቸውን ችግሮች በቅርበት ለመረዳት እና ተቋማቱም ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ሚናው የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ:- ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በድጋሚ ማሳሰቢያ ሰጠ! #ETHIOPIA #HERQA
የABH እና የHERQA ጉዳይ...

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አንዱአለም አድማሴን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ባለስልጣናት በABH ላይ እየፈፀሙ ያለውን የስም ማጥፋት ተግባር በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መስከረም 2 ቀን 2012 መታገዱን ABH አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ከ5 እስከ 7 ሚሊዮን ህዝብ እንደሚሳተፍ ተገለጸ። በበአሉ ላይም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል። በኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ፣ የባህል እሴቶች ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ቶላ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ብዙ ልምዶች ፣ በዓላት እና ቀናት ከምዕራቡ አለም እየተዋስን እያከብርን ነው፣ ሀገር በቀል ባህል የሆነውን ኢሬቻ የኢትዮጵያ የምስጋና ቀን ሆኖ ቢከበር መልካም ነው ብለዋል።

በ2012 የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ከ 5 እስከ 7 ሚሊየን ህዝብ ይሳትፍል ተብሎ እንደሚጠቅም አቶ ስንትአየሁ ተናግረዋል። በዘንድሮ የኢሬቻ በዓል መስከረም 11፣ 2012 ዓ.ም ከ 50 ሺ በላይ ሰዎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ሩጫ ይካሄዳል ፣ መስከረም 23 ፣2012 ዓ.ም ለጊዜው ምንነቱ ያልተገለጸ ካርኒቫል ይካሄዳል፣ መስከረም 24 በአዲስ አበባ ሆራ ፌንፌንኔ እና ማጠቃለያው መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ እንደሚከበር ተነግሯል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

‘የአልሸባብ አባል’ በ10 ቦታዎች የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ ነበር በሚል ተከሰሱ!

•የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አዲስ አበባ ስቴዲየም ከኢላማዎቹ መካከል ነበሩ ተብሏል

ከስድስት ወራት በፊት በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ክትትል #የአልቃይዳ የምስራቅ አፍሪቃ ክንፍ ብሎ ራሱን የሚጠራውን የአልሸባብን ዓላማ ለማሳካት በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 10 ቦታዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዝግጀት ሲያደርጉ ነበር የተባሉት አዲሃመን አብዶ ክስ ተመሰረተባቸው።

ግለሰቡ በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ ላይ በተመሳሳይ ወቅት በተነጣጠሩ ጥቃቶች ላይ የአዲስ አበባ ጥቃት ለማቀናጀት የቦታ መረጣ እንዲያከናውኑ ተመልምለው ነበር ሲል ዓቃቤ ህግ ክሱን መስርቷል። ግለሰቡ ከትላልቅ ህንጻዎች ላይ በመሆን የቦሌ አየር መንገድ ማረፊያን በምስል አስቀርተዋል ሲል ያተተው ክሱ ሀያት ሬጀንሲ፣ ስካይ ላይት ሆቴል፣ በመገንባት ላይ ያለውን የንግድ ባንክ ህንፃ አና ሌሎችም ሰዎች በብዛት የሚሰበሰቡባቸውን ቦታዎች በምስል አስቀርተዋልም ብሏል።

ሁለተኛ ተከሳሽም ለዋና ወንጀል አድራጊ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት በሽብር አዋጁ መሰረት የሽብር ወንጀልን በመርዳት ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ለዋና ወንጀል አድራጊ የትምህርት ማስረጃ ሰነዶችን በጅግጅጋ ከተማ ተምረው እንዳጠናቀቁ በማስመሰል አዘጋጅተዋል፤ በዚህም ሊፈፀም ለታቀደው ወንጀል እገዛ አድርገዋል ሲል ዐቃቤ ህግ በአባሪነት ከሷቸዋል።

የሶማሊያ ዜግነት ያላቸው አንደኛ ተከሳሽ የጅቡቲን ሕገወጥ የጉዞ ሰነድ ፓስፖርት ይዘው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ወደ ቱርክ ለመብረር ቪዛ በማግኘት በቀጣይ እቅድ እንደነበራቸው ለማወቅ ተችሏል።

https://telegra.ph/E-09-16

ምንጭ፦#አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ALGERIA

አልጄሪያውያን በመጪው የፈረንጆቹ ታህሳስ 12 ቀን 2019 የሀገራቸውን ፕሬዚዳንት እንደሚመርጡ ታውቋል። ምርጫ የሚካሄድበት ቀን በጊዜያዊ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደልቃድር ቤንሳላ ይፋ ተደርጓል። የአልጄሪያ ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አህመድ ጋይድ ሳላህ ሀገሪቱ ምርጫ የምታካሂድበት ጊዜ በይፋ እንዲነገር  ከሳምንታት በፊት ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ለሃምሌ 4 ታቅዶ የነበረ ቢሆንም እጩዎች ባለመቅረባቸው ምክንያት መራዘሙ ይታወሳል። ሀገሪቱን ለ20 ዓመታት የመሯት የ82 ዓመቱ አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ ህዝባዊ ጫናው ሲበረታባቸው ባለፈው ሚያዚያ ላይ ስልጣን ለቀዋል።

Via #BBC/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ_አዋርድ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “ጊፋታ አዋርድ” የተሰኘ የምስጋናና የዕዉቅና ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡ በወላይታ ሶዶ “አርአያዎቻችን በረከቶቻችን ናቸው” በሚል መርህ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋናና ዕውቅና ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡ በስነ-ስርዓቱ ወቅት አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ በተለዩ አምስት ዘርፎች በሃገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጎ ተጽዕኖ የፈጠሩ 45 ግለሰቦች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-3

@tsegabwolde @tikvagethiopia
#update አፍሮ ፅዮን ኮንስትራከሽን በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ሰቆጣ ወረዳ ያስገነባውን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ አስመርቋል፡፡ ትምህርት ቤቱን ያስመረቁት የአፍሮ ፅዮን ኮንስትራከሽን ባለቤት በጎ ፈቃደኛው አቶ ሲሳይ ደስታ ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቱ እያንዳንዳቸው አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሏቸው ሁለት ህንጻዎች አሉት፡፡ የቤተ ሙከራ፣ መጸዳጃ ቤቶች እና ሌሎችም ክፍሎች እንዳሉትም ታውቋል፡፡ ለግንባታው 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) እና ሌሎችም የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡

ምንጭ፡- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ!

የ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ከመስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግባት እንደምትችሉ እያሳወቅን ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ የሚካሄደው ትምህርት በሚጀመርበት መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ብቻ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግቢ ገብተው ምዝገባ መስከረም 11-12/2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡- 025 553 0355

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮችን ብቻ በTIKVAH-MAGAZINE መከታተል ትችላላችሁ👇
https://publielectoral.lat/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#UPDATE የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በተለያዩ ድርጅታዊ አጃንዳዎች ዙሪያ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ለ2 ቀናት በሚኖረው ቆይታ፤ የጋህአዴን የ2011 ዓ.ም የድርጅት ፖለቲካና የልማት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውን ይጠበቃል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ከዚህ ሌላ የድርጅት ጽ/ቤቱ የ2012 ዓ.ም የውስጠ ድርጅት ሥራዎችና የጋህአዴን የአደረጃጀትና የአሠራር ሥነ-ምግባር ሠነድ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግባቸውን ይጠበቃል።

ምንጭ፡- (ጋህአዴን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዋና መሥሪያ ቤቱ በእንግሊዝ የሆነው ግሎባል ብራንድስ መጽሔት፣ ካሊብራ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሆቴል ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ላበረከተው አስተዋጽኦ ዕውቅና ሰጠ። በቅርቡ በለንደን በተካሄደ ሥነ ሥርዓትም የካሊብራ አማካሪዎች ሽልማቱን ተቀብሏል።

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለ6 ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል። ከየካቲት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ግዛት አብዩ ጌታው የገጠር መሬት አስተዳድርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ሙሉቀን አዳነ ጥሩነህ ደግሞ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ነው የተመለከተው። እንዲሁም አቶ ብርሀኑ ጣዕም ያለው የክልሉ ንግድ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ማማሩ አያሌው ሞገስ የክልሉ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና ዶ/ር መለስ መኮንን ይመር የግብርና ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

ዶ/ር አያሌው ወንዴ መለሰ ደግሞ የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ ነክ አካላት ጥበቃና ልማት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት ማሳሰቢያ!

አንዳንድ የሞባይል ደንበኞቻችን ከተለያዩ ሀገራት የጥሪ ምልክት(Missed Call) እየተደረገላቸው መሆኑን ተገንዝበናል። የእነዚህ ጥሪዎች ዋና አላማ ደንበኞቻችን ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተደወለላቸው መስሏቸው መልሰው ወደ ውጭ ሀገር እንዲደውሉ ለማድረግ እና ከሂሳባቸው የአየር ሰዓት እንዲቆረጥባቸው የሚጠቀሙበት የማጭበርበር ዘዴ ነው። በመሆኑም ውድ ደንበኞቻችን ቀድም ሲል በማታውቋቸው የውጭ ሃገራት የስልክ ቁጥሮች የጥሪ ምልክት ሲደርሳችሁ መልሳችሁ ባለመደወል ከአጭበርባሪዎች እንድትጠነቀቁ እናሳስባለን።

ኢትዮ ቴሌኮም

@tsegabwolde @tikvahethiopia