#update አፍሮ ፅዮን ኮንስትራከሽን በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ሰቆጣ ወረዳ ያስገነባውን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ አስመርቋል፡፡ ትምህርት ቤቱን ያስመረቁት የአፍሮ ፅዮን ኮንስትራከሽን ባለቤት በጎ ፈቃደኛው አቶ ሲሳይ ደስታ ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቱ እያንዳንዳቸው አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሏቸው ሁለት ህንጻዎች አሉት፡፡ የቤተ ሙከራ፣ መጸዳጃ ቤቶች እና ሌሎችም ክፍሎች እንዳሉትም ታውቋል፡፡ ለግንባታው 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) እና ሌሎችም የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡

ምንጭ፡- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia