TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በድጋሚ ማሳሰቢያ ሰጠ! #ETHIOPIA #HERQA
#HERQA

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተለያዩ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ተምረው ያስመረቋቸውና በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎችን በተመለከተ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረቡን አስታወቀ።

በኤጀንሲ የዕውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ፤ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተለያዩ መስፈርቶችን ሳያሟሉ አስተምረው ያስመረቋቸውና በማስተማር ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ቁጥር በርካታ ነው። የተማሪዎችን መረጃ ለመደበቅ ሁለት ሬጅስትራር ያሏቸው፤ ግብር እንዳይከፍሉ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያቀርቡ ተቋማት እንዳሉ ተገንዝበናል።

ተቋማቱ አስተምረው ያስመረቋቸውና ተጠያቂነትን በመሸሽ ለኤጀንሲው ያላቀረ ቧቸው ሊኖሩ ስለሚችሉ ችግሩ የሰፋና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊና ማህበራዊ በመሆኑ ከፍተኛ አመራሩ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ቀርቧል::

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HERQA

በኢትዮጵያ ውስጥ በኦንላይን እንዲያስተምር ፈቃድ የተሰጠው ተቋም እንደሌለ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው UK MBA በሚል የሚንቀሳቀስ ተቋም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ የኦንላይን ትምህርት እሰጣለሁ በማለት በኢንተርኔት (በዩቲዩብ፣ በፌስ-ቡክና በኢስታግራም) ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የኦንላይን ትምህርት እውቅና ፈቃድ የተሰጠው አለመኖሩን ኤጀንሲው በተደጋጋሚ በገለጸው መሰረት ይህም ተቋም የሚያስተላልፈው ማስታወቂያ ህገ-ወጥ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።

[EPA]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

አስቸኳይ መልዕክት!

የግል ከፍተኛ ትምህርት የመደበኛ ፣ የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ትምህርትና ስልጠና ለሁለት ሳምንታት እንዲቋረጡ ትዕዛዝ ተላልፏል።

በመሆኑም የሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ፣ አካዳሚክ እና የአስተዳራዊ ሰራተኞች በሙሉ ለ2 ሳምንታት በየቤታቸው እንዲቆዩ ተብሏል።

በቆይታቸው ባሉበት ሆነው ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መመሪያዎችን ተከትለው ጥንቃቄ በማድረግ በመምህራኖቻቸው የሚሰጡ ንባቦችን እያካሄዱ ለ2 ሳምንታት የሚቆዩ #HERQA ማምሻውን ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HERQA

እስከ ሀምሌ 2013 ዓ.ም. ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ መረጃ መሰረት ካሉት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኮሌጅ እና ኢንስቲትዩት የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው የሚከተሉት ናቸው።

ዩኒቨርሲቲ የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው እስካሁን 5 ሲሆኑ እነርሱም፡-
1. ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ
2. ቅድስተ-ማርያም ዩኒቨርሲቲ
3. ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ
4. ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ እና
5. አድማስ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ስያሜ ያላቸው የግል ተቋማት እስካሁን 5 ሲሆኑ እነዚህም ፦

1. አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
2. ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
3. ሸባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
4. ሆፕ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
5. ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ናቸው፡፡

** የተቀሩት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮሌጅ ወይም ኢንስቲትዩት የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው ናቸው፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው ውጪ ከደረጃ ስያሜ ውጪ ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ በሚዲያ ማስታወቂያ ማሰራት፣ በተለያዩ ሰነዶች እና ባነሮች ላይ መጠቀም፤ ማዕተም ማሰራት ወዘተ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል።

ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ የተሰጠ የትምህርት ማስረጃ ካለም ተቀባይነት አይኖረውም ተብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የደረጃ ስያሜ መመሪያ ማክበርን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#HERQA

ከ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ይሁንታ ሳያገኙ አዲስ ዲፓርትመንት ከፍተው ማስተማር አይችሉም ተባለ።

ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት መርሃ ግብር የሚያስተምሯቸውን የትምህርት ክፍሎች ብቻ ይቆጣጠር ነበር።

ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ መመሪያ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መተላለፉን የኤጀንሲው የእውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቢይ ደባይ ተናግረዋል።

በዚህም ተቋማቱ የሚከፍቷቸው የትምህርት ክፍሎች መስፈርቶችን ያሟሉ ስለመሆናቸው ኤጀንሲው መመርመር እንደሚጀመር ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ኤጀንሲው በ2013 ዓ.ም በ1 ሺህ 112 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ማጣራት፤ 562ቱ ማሟላት የነበረባቸውን ዝቅተኛ መስፈርቶች ሳያሟሉ በመገኘታቸው ውድቅ ተደርገዋል።

ተጠሪነት ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ የቆየውን ኤጀንሲ፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ኮሚሽን በሚል ስያሜ እንደአዲስ በማቋቋም ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ምንጭ፦ #ሸገርኤፍኤም

@tikvahuniversity