#HERQA

ከ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ይሁንታ ሳያገኙ አዲስ ዲፓርትመንት ከፍተው ማስተማር አይችሉም ተባለ።

ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት መርሃ ግብር የሚያስተምሯቸውን የትምህርት ክፍሎች ብቻ ይቆጣጠር ነበር።

ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ መመሪያ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መተላለፉን የኤጀንሲው የእውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቢይ ደባይ ተናግረዋል።

በዚህም ተቋማቱ የሚከፍቷቸው የትምህርት ክፍሎች መስፈርቶችን ያሟሉ ስለመሆናቸው ኤጀንሲው መመርመር እንደሚጀመር ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ኤጀንሲው በ2013 ዓ.ም በ1 ሺህ 112 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ማጣራት፤ 562ቱ ማሟላት የነበረባቸውን ዝቅተኛ መስፈርቶች ሳያሟሉ በመገኘታቸው ውድቅ ተደርገዋል።

ተጠሪነት ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ የቆየውን ኤጀንሲ፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ኮሚሽን በሚል ስያሜ እንደአዲስ በማቋቋም ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ምንጭ፦ #ሸገርኤፍኤም

@tikvahuniversity