TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ውድ የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ(ONE PACK FOR ONE CHILD) ቤተሰቦቻችን፣ ለቀጣዩ አመት 2012 የምናረገውን የፓክ ስብሰባ ጀምረናል። 13,000 ፓኮችን የማሰባሰብ ሂደታችንን ለመደገፍ በነዚህ አድራሻዎችና በአቅራቢያዎ ይደውሉልን።

DROPOFF LOCATIONS

1. ኡራኤል Urael- 0911245301 , 0929184747
2. ካዛንቺስ Kazanchis- 0913659542 , 0911870745
3. ቦሌ ሞናርክ Monarch (gulf Aziz building ) - 0923679220
4. ቦሌ ቦስተን Boston day spa - 0911453603 , 0923679220
5. አስኮ / Asko - 0911337333 , 0923679220
6. ሳሪስ Saris - 0912605469 , 0929184747
7. ገርጂ Gerji- 0911970979
8. ልደታ Lideta - 0911519122 , 0923679220
9. ሜክሲኮ Mexco -0911606881
10. መገናኛ Megenagna - 0912401320, 0913659542
11. መስቀል ፍላወር Meskel Flower - 0911606881, 0929184747
12. 5 ኪሎ 5 killo - 091306033 , 0929184747
13. ሰሚት/ ሳሊተምረት Salite Mihret - 0929184747 , 0923679220
14. ቃሊቲ /Kality - 0912605469 , 0911910228
15. ፒያሳ / Piassa -0912878684 ,0929184747

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክቡር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው ግብፅ ናቸው...

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በግብፅ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ካይሮ ይገኛሉ፡፡ በጉብኝታቸውም ከግብፁ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ፣ በአካባቢያዊና በአለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ #መወያየታቸውን በግብፅ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አመልክቷል። እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በካይሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽህፈት ቤት በመገኘት ከሰራተኞቹ ጋር ዉይይት አድርገዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሀምሌ 22 የሚካሄደውን #የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መሠረት በማድረግ በሚሲዮኑ ጽህፈት ቤት የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
The 33rd Oromo Studies Association Annual Confrence (OSA)

በOMN የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ👇
# https://www.facebook.com/OromiaMedia/videos/1382873938540806/?app=fbl
#update ኢትዮጵያ ውስጥ “እየተፈፀመ ነው” ያሉት ጅምላ እሥራት፣ ማሳደድና ማስፈራራት በአስቸኳይ እንዲቆም የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድና የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ - ኢሕአፓን ጨምሮ ሰባት ፓርቲዎች ጠይቀዋል።

ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚነሱ የክልል ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ “በንፁሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ ዝርፊያና ወከባ የፈፀሙ ወገኖች ሕግ ፊት ይቅረቡ” ሲሉም ፓርቲዎቹ ጥሪ አሰምተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው፦

ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሥራ ስምሪት መጀመሩንና ወደ እስያና አውሮፓም የሠለጠነ የሰው ኃይል ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ጀኔራል ብርሃኑ አበራ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በዚህ የውጭ ሃገር ሥራ ስምሪት በተለይ በኮንስትራክሽን ሙያ ላይ እውቀቱና ልምዱ ያላቸውን ባለሙያዎችን ለመላክ እንደታሰበም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ሥራ ቀጣሪው የሚፈልገው የሥራ ዘርፍ ስላልተገለጸ በየትኞቹ የኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ እንደሆነ ዝርዝሩን ገና አለመለየታቸውን አክለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/EE-07-26

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

ጌጅ ኮሌጅ በቴክኒክና ሙያ፣ በቅድመ ምረቃ (መጀመሪያ ዲግሪ) እና በድህረ ምረቃ (ሁለተኛ ዲግሪ) በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 6ሺ 454 ተማሪዎች በሚሊኒየም አዳራሽ አስመረቀ፡፡ ኮሌጁ በዘንድሮ ዓመት ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 98 በመቶ ያህሉ የመንግሥት ሠራተኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ኮሌጁ እውቅና ባገኘባቸው የትምህርት መስኮች በቴክኒክና ሙያ 4ሺ66 ፣ በቅድመ ምረቃ 2ሺ 299 እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 79 ተማሪዎችን ትናንት ማስመረቅ ችሏል፡፡ የምረቃት ሥነሥርዓቱ በኮሌጁ ታሪክ ለ16ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሞገስ ግርማ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ጥራቱን በማስጠበቅ ስያሜውን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ ጫፍ ላይ መድረሱን በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

ከምን ጊዜውም በበለጠ የትምህርት ሴክተሩን በማዘመንና በማሳደግ እንደ አንድ ባለድርሻ አካል ኮሌጁ ሚና እንደሚኖረው የተናገሩት ሥራ አስፈጻሚው፤ ጌጅ ኮሌጅ አሁን ባለበት ደረጃ ሳይወሰን ራሱን ከሌሎች የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ለመሰ ለፍ፤ ተወዳዳሪ በመሆን ብቁ ዜጎችን በማፍራትና ወደ ኢንዱስትሪው በመቀላቀል አገሪቷን ዕድገት ለመደገፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ኮሌጁ በ2012 ዓ.ም ደረጃውን ወደ ዩኒቨርሲቲ ተቋምነት ለማሳደግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሚቀጥለው ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል። የፌዴራል እና የክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ 2ኛ መደበኛ መድረኩን በባሕር ዳር እያደረገ ነው። በመድረኩ የተገኙት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤፍሬም ተክሌ (ዶክተር) በኢትዮጵያ በተያዘው የበጀት ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል ብለዋል። እስከ 2017 ዓ.ም ለ14 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደታቀደም አስታውቀዋል። እስከ 2022ዓ.ም ደግሞ ለ20 ሚሊዮን የሀገሪቱ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአራት ሚልዮን ዶላር ክስ እስር ቤት ይገኝ የነበረው የትድሀር ኮንስትራክሽን ባለቤት እስራኤላዊው ሜናሼ ሌቪ ከአራት አመት በሁዋላ ከእስር ቤት እንደወጣ ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። የኮንስትራክሽን ድርጅቱ ባለቤት አዲስ አበባ በነበረው ፕሮጀክት ዙርያ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ታክስ በማጭበርበር እና ጉቦ በመስጠት ተከሶ ማእከላዊ እስር ቤት በአስከፊ ሁኔታ በእስር ላይ ይገኝ ነበር ተብሏል። በመጨረሻም አሌፍ በተባለ የእስራኤል ድርጅት ድጋፍ ሰኔ 27 ነፃ ሆኗል ተብሏል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴአሻራ

የፊታችን ሀምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮች ችግኞችን በመላው ሀገሪቱ ለመትከል ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሃምሌ_22 #አረንጓዴ_አሻራ "200 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር" 3 ቀን ቀረው!
37 ሺህ ዩሮ ለባለቤቱ የመለሰው ወታደር!

ወድቆ ያገኘውን 37 ሺህ ዩሮ ለባለቤቱ የመለሰው ወታደር የሁለት ማዕረግ እድገት ተሰጠው። ታማኙ የናይጄሪያ አየር ኃይል አባል የሆነው በሺር ኡመር ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን በሰሜናዊቷ ካኖ ግዛት አውሮፕላን ማረፊያ ቅኝት በማድረግ ላይ ነበሩ። በቅኝቱ ወቅት በሺር ኡመር በካርቱን ተጠቅልሎ የወደቀ 37 ሺህ ዩሮ (41 ሺህ 500 ዶላር) ያገኛል።

በገንዘቡ መጠቅለያ ላይ የተጻፈው ስልክ ላይ በመደወል ለባለቤቱ መልሷል። የአየር ኃይል አባሉ በሺር ኡመር በዚህ የታማኝነት ተግባሩ ለማሳካት 10 ዓመት የሚወስድበትን የሁለት ማዕረግ እድገት ከተቋሙ ተችሮታል። የምስጋና ወረቀት በተቋሙ እንደተጠሰውም ነው የተነገረው።

ትናንት ምሽት በነበረው ስነ ስርዓት የአየር ኃይል አዛዡ ማርሻል ሳዲቅ አቡበከር “ኡመር ወድቆ ያገኘውን ገንዘብ ለባለቤቱ በመመለስ ሀቀኝነትን በተግባር አሳይቶናል” ብለዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ ክልል ዝግጅቴን አጠናቅቂያለሁ ብሏል!
#ሃምሌ22

በአንድ ጀምበር 200 ሚሊየን ችግኞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል በተያዘው እቅድ መሰረት የአማራ ክልል በአንድ ቀን 100 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ የመስኖ ግንባታና የተፈጥሮ ሃብት ምክትል ሃላፊ አቶ ማርቆስ ወንዴ፥ ሃምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ በክልል ደረጃ 100 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ለዚሁ ተግባር ችግኞች ወደ መትከያ ቦታዎች መጓጓዛቸውን በመግለጽ በእለቱ በየችግኝ መትከያ ቦታዎች ድጋፍ የሚያደርጉ የዘርፉ ሙያተኞች መመደባቸውን አንስተዋል፡፡

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ማህበረሰቡ ለዚሁ ተልዕኮ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም ምክትል ሃላፊው ገልጸዋል፡፡ በእለቱ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም በዚሁ ፕሮግራም ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው አቶ ማርቆስ የተናገሩት፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቁልቢ #ሀዋሳ #ሀምሌ19

በቁልቢ እና በሐዋሳ ከተሞች በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ ሐምሌ 19 ቀን የሚከበረው የገብርኤል አመታዊ ንግሥ በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ተከናወነ። የክብረ በዓሉ ታዳሚዎች ቁጥር በቁልቢ ሲጨምር በሐዋሳ በግማሽ ገደማ መቀነሱን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁልቢ ከተማ የተካሔደው የዛሬው የበዓል አከባበር ምንም እክል እንዳልገጠመው የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር ሱልጣን አወል ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

https://telegra.ph/HAMLE19-07-26
#update የአሜሪካ መንግስት ከ16 አመት በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ የሞት ቅጣት መወሰኑ ተነገረ፡፡ ከፈረንጆቹ 2003 በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ የሞት ቅጣት መወሰኑን የአሜሪካ ፌዴራል መንግስት ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው 5 ሰዎች በህፃናት ላይ በፈጸሙት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለሞት ቅጣት ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል ተብሏል ፣ የሞት ቅጣቱ የሚፈፀምበት ቀን ታህሳስ 2019 እና ጥር 2020 እንደሆነም በዘገባው ተካቷል፡፡ በአሜሪካ የሚገኙ የመብት ተሟጋች ቡድኖች የሞት ቅጣቱ የሚፈፀምበት ቀን በጣም ቅርብ ስለሆነ ሊታሰብበት ይገባል ፣ በቅጣቱ ፍትሃዊነት ላይም ትኩረት ይሰጥ ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው..."

ከሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ በሜድትራኒያን #ባሕር ላይ በትናንትናው ዕለት በመስጠም ላይ ከነበረ ጀልባ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከታደጓቸው ስደተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አንድ ከፍተኛ የሊቢያ ባለሥልጣን አስታወቁ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) በበኩሉ በጀልባ የሜድትራኒያን ባሕርን ለማቋረጥ ከሞከሩ 300 ስደተኞች ውስጥ #147ቱ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የአፍሪካ እና የሜድትራኒያን ቃል-አቀባይ ቻርሊ ያክስሊ ዛሬ እንደተናገሩት ኾምስ ከተባለችው የሊቢያ ከተማ ከተነሱት ስደተኞች ውስጥ 150 ያክል በባሕር ላይ ሞተዋል የሚል መረጃ በሊቢያ ከሚገኙ ባልደረቦቻቸው ደርሷቸዋል።

የሊቢያ የባሕር ኃይል ቃል-አቀባይ ጄኔራል አዩብ ቃሲም በበኩላቸው ከኾምስ 100 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ከሚገኘው የባሕሩ ክፍል በመስጠም ላይ ከነበረ ጀልባ አስከሬኖች እና 134 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን ተናግረዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችልም ትንብያዉ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመሰል አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና #እንዲጠነቀቅ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በአብዛኛዉ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጥሩ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ትንበያዉ የሚያመለክት ሲሆን ይህም ለግብርናዉ የስራ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ታምኖበታል፡፡ ቀድመዉ የተዘሩ እና በእድገት ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች የሚገኘዉ እርጥበት በጎ ሚና አለዉ ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ለቋሚ ተክሎች የዉሓ ፍላጎታቸዉን እንደሚያሟላለቸዉና ለአርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች የግጦሽ እና የመጠጥ ዉሃ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

በቀጣይ የሚኖረዉ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተፋሰሶች ላይ ለዉጥ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ በአብዛኛዉ የተከዜ፣ የኦሞ ጊቤ የአባይ፤ የላይኛዉና የመካከለኛዉ አዋሽ እና አፋር ደናክል ተፋሳሾች ከፍተኛ እርጥበት ያገኛሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
ፎቶ: ፋይል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል ዝግጅቱ ተጠናቋል!
#ሃምሌ22

በኦሮሚያ ክልል የተዘጋጁ ችግኞች #ወደሚተከሉበት ስፍራ እየተጓጓዙ መሆኑ ተገለጸ። በክልሉ ባሉ 3 ሺህ 92 የችግኝ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ችግኞች ወደሚተከሉበት ቦታ እየተጓጓዙ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየዓመቱ ሐምሌ 19 ቀን የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ዛሬ በቁልቢና በሐዋሳ ከተሞች ተከበረ።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች እንደገለጹት በከተሞቹ በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰላም ተከብሯል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለጹት በዓሉ በቁልቢ ከተማ የተከበረው ያለአላንዳች የጸጥታ ችግር ነበር።

ለዚህም የጸጥታ አካላት ባደረጉት የወንጀል መከላከል ሥራና ኅብረተሰቡ ያደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ በዓሉን በሰላም ለማክበር  እንዳስቻለ ገልጸዋል።

በዓሉ ላይ በስርቆት ተሰማርተው እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሰባት ተጠርጣሪዎችን በሥፍራው የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ከስምንት ወር በሚደርስ እስራት  መቀጣታቸውን  ኮማንደር ስዩም ኣስታውቀዋል።

በተመሳሳይ በሐዋሳ ከተማ ዓመታዊው የንግሥ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሃዋሳ #ሃምሌ19

በሐዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት የተከበረው ዓመታዊው የገብርኤል የንግሥ በዓል ሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #መስፍን_ዴቢሶ ገልፀዋል። 

@tsegabwolde @tikvahethiopia