#update በሚቀጥለው ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል። የፌዴራል እና የክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ 2ኛ መደበኛ መድረኩን በባሕር ዳር እያደረገ ነው። በመድረኩ የተገኙት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤፍሬም ተክሌ (ዶክተር) በኢትዮጵያ በተያዘው የበጀት ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል ብለዋል። እስከ 2017 ዓ.ም ለ14 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደታቀደም አስታውቀዋል። እስከ 2022ዓ.ም ደግሞ ለ20 ሚሊዮን የሀገሪቱ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia