TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቢሲኒያ_ባንክ

በአቢሲንያ የኢ-ኮሜርስ ክፍያ መንገድ ንግድዎን ያቀላጥፉ !

የድርጅትዎን ድህረ ገፅ ወይም መተግበሪያ ከባንካችን የኢ-ኮሜርስ ክፍያ መንገድ ጋር በማሳለጥ ከመላው ዓለም ክፍያ በቪዛ እና ማስተር ካርድ በቀላሉ መቀበል ይችላሉ።
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ! https://publielectoral.lat/BoAEth
#ኮሎኔል_ገመቹ_አያና

➡️ " ኮሎኔል ገመቹ አያናን ከኦሮሚያ ፖሊስ በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል የምርመራ መዝገብ በስማቸው የለንም ፤... ኮለኔል ገመቹን ይዘን ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ በመሔድ ተረከቡን ብለን ስንጠይቅ ኦሮሚያ ፖሊስ እኛ ጋር ጉዳይ የለውም የሚል ምላሽ ሰጥቶናል " - ኮማንደር ኤርትሮ ኦቦ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

➡️ " ኮ/ል ገመቹ መታሰራቸውን አንፈልግም ቢለቀቁ አልቃወምም " - አቃቤ ህግ

➡️ " ፍርድ ቤት ነጻ እንዳለኝ ሁሉ በነጻ እንድፈታ እፈልጋለሁ "  - ኮሎኔል ገመቹ አያና

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮ/ል ገመቹ አያናን ከኦሮሚያ ፖሊስ በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል የምርመራ መዝገብ በስማቸው እንደሌለው ገልጿል።

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኮሎኔል ገመቹ አያና ባለፈው ዓመት ግንቦት 9/ 2013 ዓ/ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ወንጀል ችሎት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል በነጻ መሰናበታቸው ይታወሳል።

ሆኖም በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ በነጋታው ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ/ም ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲወጡ በር ላይ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸውን እና 6 ወር በገላን ፖሊስ ጣቢያ እና ወታደራዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጄነራል ዶሮ እርባታ ውስጥ ታስረው እንደነበር እና ከህዳር 16 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፈው እንደተሰጡና እንደታሰሩ ተገልጾ ነበር።

ያንብቡ ; https://telegra.ph/Tarik-Adugna-05-19

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#Update

ኢንዶኔዥያ በሀገር ውስጥ #የምግብ_ዘይት አቅርቦት ላይ መሻሻሎች መታየቱን ተከትሎ እ.ኤ.አ. ከሰኞ ግንቦት 23 /2022 ጀምሮ የፓልም ዘይት ወደ ውጭ እንዳይላክ የተጣለው እገዳ እንደሚነሳ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Qatar2022

በዓለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉ ዳኞች ይፋ ሆኑ።

በኳታር አዘጋጅነት በ 2022 ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ፊፋ 36 ዋና ዳኞችን 69 ረዳት ዳኞችን እና 24 የቫር ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መሾሙን አስታውቋል ።

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ፊፋ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከሾማቸው ዳኞች ስም መካከል #አለመካትቱ ታውቋል ።

ፊፋ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር አዘጋጅነት በሚካሄደው የአለም ዋንጫን ላይ ሶስት ዋና ሴት ዳኞችን እና ሶስት ረዳት ሴት ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መምረጡ ተገልጿል ።

የአለም ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲመሩ ከተመረጡ ሶስት ሴት ዳኞች መካከል አንዷ ሩዋንዷዊቷ ሳሊማ ሙካንሳንጋ መሆኗ ተዘግቧል ።

አፍሪካን ወክለው የአለም ዋንጫን እንዲመሩ የተመረጡ ስድስት ዋና ዳኞች ሳሊማ ሙካንሳንጋ ፣ ጃኒ ሲካዝዌ ፣ ባካሪ ጋሳማ ፣ ቪክቶር ጎሜዝ ፣ ማጉዬቴ ኒዳዬ እና ሙስጣፋ ጎርባል መሆናቸው ተነግሯል ።

More : @tikvahethsport
#የተመድ_ማስጠንቀቂያ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት በቀጣይ ወራት ዓለም አቀፍ የምግብ እጥረት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትላንት በኒውዮርክ ንግግር ሲያደርጉ እንዳሉት ጦርነቱ በድሃ ሃገራት የዋጋ ንረትን በማስከተል የምግብ ዋስትና እጥረትን አባብሶታል።

የዩክሬን ወጪ ንግድ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ደረጃ ካልተመለሰ ዓለም ለዓመታት የሚዘልቅ ረሃብ ሊገጥማት ይችላል ብለዋል።

በአንድ ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው የሱፍ ዘይት፣ በቆሎ እና ስንዴ ወደ ውጭ ይልኩ የነበሩት የዩክሬን ወደቦች ከስራ ርቀዋል።

ይህም የዓለም አቀፍ አቅርቦትን ከመቀነስ ባለፈ የሌሎች አማራጮችን ዋጋ እንዲንር አድርጓል።

እንደ ተመድ መረጃ የዓለም የምግብ ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር በ30 በመቶ ብልጫ አለው።

ጉተሬዝ ፤ " ተባብረን ከሠራን በዓለማችን ላይ በቂ ምግብ አለ። ያለድን ችግር ዛሬ ካልፈታን በሚቀጥሉት ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እጥረት ችግር ውስጥ እንገባለን" ብለዋል።

የዩክሬን የምግብ ምርት እንዲሁም የሩሲያ እና የቤላሩስ #ማዳበሪያ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ከመቀላቀል ውጭ ለምግብ ቀውሱ ምንም አይነት ውጤታማ መፍትሄ የለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የምግብ ምርቶችን ወደ መደበኛ ደረጃ ለመመለስ ከሩሲያ፣ ከዩክሬን፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር "ጠንካራ ግንኙነት" እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በሌላ በኩል ፤ የዓለም ባንክ የምግብ ዋስትና እጦትን ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች የሚውል 12 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ ማድረጉን አሳውቋል። እርምጃው በሚቀጥሉት 15 ወራት ለተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ያለውን ጠቅላላ ገንዘብ ወደ ከ30 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ያደርሰዋል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" እርምጃ ተወስዶባቸዋል "

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመተማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የወረዳው ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ፥ " የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ሶስት ጸረ-ሰላም ኃይሎች በጥምር የጸጥታ ኃይል (ልዩ ኃይል ፣ ፀረሽምቅ እና ፖሊስ) ርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብሏል።

በጣምራ ስምሪቱ ርምጃ የተወሰደባቸው የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች መሆናቸውን ፅ/ቤቱ አሳውቋል።

ርምጃ የተወሰደባቸው ፦ 1. ፎላ አብተው - አድራሻ መተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ፤ 2. ደሴ አበራ - መተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ፤ 3. ሱራፌል ወርቁ - ከደጋ አካባቢ የመጣ መሆኑን ፅ/ቤቱ ይፋ አድርጓል።

በስምሪቱ 1 ቋም ክላሽ ፣ 2 ኤም 14 ፣ 1 ስናይፐር የተማረከ መሆኑን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን እንየተስተዋለ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህን አስመልክቶም የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለነዋሪዎችም የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

በተለይም ፦ አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው (ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም፣ የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣ እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።

ሊደረጉ የሚገባቸው የጥንቃቄ ተግባራት ፦

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፣

2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፣

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፣

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፣

5. አመጋገብዎን ማስተካከል (ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፣

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፣

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፣

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፣

9. የተለያየ ህመም ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ያድርጉ ፡ የታዘዘሎትን መድሃኒትም በትዕዛዙ መሰረት ይውሰዱ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ፤ ከሙቀቱ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ የጤና ችግሮችና ድንገተኛ ህልፈት ነዋሪዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#CBE

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ከደንበኞች የማይንቀሳቀስ ሂሳብ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ስለመውሰዱ የሚያስረዳ ማስረጃ የተገኘበት ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የባንኩ ሰራተኞችም በዚሁ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

➡️ 1ኛ ተከሳሽ አቶ እስጢፋኖስ ሙሉጌታ ገቢሳ (የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን)

➡️ 2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አስኩዋል ወልደአብዝጊ ߹

➡️ 3ኛ ተከሳሽ በቀለ ሽፌ

➡️ 4ኛ ተከሳሽ ይልቃል አዳነ ናቸው የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ የመሰረተባቸው።

አንደኛ ተከሳሽ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ " ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ " ተቀዳሚ ባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን የሥራ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በባንኩ ደንበኛ ከሆኑ ግለሰቦች ሳይንቀሳቀስ በመቆየታቸው ምክንያት የማይንቀሳቀሱ ሂሳብ (Inactive) የነበሩ የቁጠባ ሂሳቦች ሃላፊነቱን በመጠቀም ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (Active) በመቀየር ደንበኞች ከሂሳባቸው ጋር ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያስተሳሰሩትን ስልክ ቁጥር ሲስተም ላይ የተቀየረውን በማፅደቅ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ በተለያዩ ጊዚያት በራሱ ሥም በተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች በአጠቃላይ ብር 2,535,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺ) ብር በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ ወስዷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Ministry-Of-Justice-05-19

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
የብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ጠበቃ አቶ ሸጋው አለበል ምን አሉ ? (ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃል) ፦

" ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች የመኪና መንገድ ዘግተው ከከበቧቸው በኋላ በርከት ብለው አስገድደው ተሽከርካሪ ውስጥ እንዳስገቧቸው ነግረውኛል።

ተሽከርካሪ ውስጥ ግባ አልገባም በሚል ኃይል እንደተጠቀሙና መጠነኛ ቢሆንም የእጅ ነገር እንዳረፈባቸውም ነግረውኛል።

ከተያዙበት እለት ጀምሮም ለሁለት ቀናት ምድር ቤት በጨለማ ውስጥ ብቻቸውን እንዳደሩ እና ይህ ትክክል እንዳልሆነ ፤ ቀጥሎ በተሽከርካሪ ወደ ቢሾፍቱ ተወስደው ከዚያም በሄሊኮፕተር ወደ ባህርዳር መወሰዳቸውንና ለእሳቸው ተብሎ ሄሊኮፕተር ተመድቦ መወሰዳቸው የመንግሥትን ሀብት ማባከን መሆኑን እንደሚያምኑ ገልፀውልኛል።

ባህርዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ማንኛውም እስረኛ በሚጠየቅበት ሁኔታ መብታቸውን እንዲገለገሉ ተደርገዋል።

ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ወንጀል እንዳልፈፀሙ ነግረውኛል፤ የመናገር ነፃነታቸውን ተጠቅመው ሚዲያ ላይ በዋለ ጉዳይ እንዲሁም ቅሬታ ያላቸው አካላት አስረውኝ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው አስረድተውኛል።

ከተያዙ ጀምሮ ቃል አልሰጡም፤ የተጠረጠሩበት አልተነገራቸውም፤ ፍርድ ቤትም አልቀረቡ። እነዚህ ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸው በመጣሳቸው ቅሬታ እንዳላቸው ገልፀውልኛል።

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ በማረሚያ ቤት ውስጥ በተረጋጋ ሁኔታ ይገኛሉ። የዋስትና ጥያቄ አቅርበናል የዋስትና ጉዳያቸው ቀጠሮ ነገ ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ/ም ነው "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ለመጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶታል። በሕግ ጥላ ስር የሚገኘው ተከሳሹ ብሩክ በላይነህ፤ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል። ማክሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት የቀረበው ተከሳሹ፤ "የሚፈልጋቸው ምስክሮቹ በአካባቢው…
#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ ለውሳኔ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ተቀጥሯል።

ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮች በማቅረብ ራሱን ሲከላከል ቆይቷል።

ፍርድ ቤት የቀረቡ ምስክሮች "ሟች እና ተከሳሾች ጓደኛሞች እንደነበሩ እንደሚያውቁና ከዚያ ውጪ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ" ገልጸዋል።

በሕግ ጥላ ስር ሚገኘው ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ላይ የፍርድ ማቅለያ እና ማክበጃ መቅረቡን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መርኪያ መንገሻ ለ @tikvahuniversity ተናግረዋል።

ተከሳሹ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል።

ፍርድ ቤቱ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ተለወጫ ቀጠሮ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ሰጥቷል።

ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

More : @tikvahuniversity
#SEMU

የስሙ ኦዲዮ ቡክስ እና ፖድካስት መተግበሪያን ከጎግልና አፕል ማከማቻ በማውረድ በደንበኝነት ምዝገባ (Subscription) ወይም በአንድ ጊዜ ክፍያ (à la carte) ከመቶ በላይ ድምፀ-መጻሕፍት እና ፖድካስቶችንም ያግኙ።

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገጽቻችንን ይከታተሉ እና የቴሌግራም ቻነላችን @SemuAudiobook ቤተሰብ ይሁኑ።

መተረክ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎን ከ5 ደቂቃ ያነሰ ናሙናዎን በቴሌግራም +251 911 926725 ላይ ይላኩልን።

ጉግል ማከማቻ ፡ https://bit.ly/SemuGooglePlay
አፕል ማከማቻ፡https://apple.co/3gzblVH
ድረ-ገፅ፡ https://www.semuaudiobooks.com/
(ቁጥራዊ መረጃ)

ከIDMC የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሪፖርት ፦

➡️ በ2021 በመላው ዓለም 59.1 ሚሊዮን ተፈናቃዮች ተመዝግበዋል ፤ ይህ ቁጥር በታሪክ ከፍተኛው ነው። ከ59.1 ሚሊዮኑ መካከል 53.2 ሚሊዮን በግጭት እና ሁከት ፤ 5.9 ሚሊዮን በተፈጥሯ አደጋዎች የተፈናቀሉ ናቸው።

#ኢትዮጵያ

➡️ በ2021 በኢትዮጵያ ግጭት እና ሁከት ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ይህ ቁጥር ከቀደመው ዓመት በ3 እጥፍ ይበልጣል።

➡️ በኢትዮጵያ የተመዘገበው የተፈናቃዮች ቁጥር በአንድ አገር ውስጥ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ሁሉ የሚበልጥ ሲሆን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአመቱ የአገሪቱን ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል ከፍተኛውን ቦታ ይዟል። በሌሎች ክልሎች የተከሰቱ የርስ በርስ ግጭቶችም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።

በIDMC ሪፖርት መሠረት ፦

⮕ በትግራይ ክልል 1.8 ሚሊዮን፣
⮕ በአማራ ክልል 1.7 ሚሊዮን፣
⮕ በኦሮሚያ ክልል 643 ሺ ተፈናቃዮች ተመዝግበዋል።

➡️ በ2021 መጨረሻ በመላው ኢትዮጵያ 3.6 ሚሊዮን ዜጎች ሕይወታቸውን በተፈናቃይነት ለመግፋት ተገደዋል፤ ከእነዚህ መካከል 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት የትምህርት ዕድል የሌላለቸው ናቸው።

➡️ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በርሀ በታች በሚገኙ አገራት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ14 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።

➡️ በተፈናቃዮች ቁጥር ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ያሉት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ቡርኪና ፋሶ ናቸው (ከሰሀራ በታች)።

ሙሉ ሪፖርት : https://www.internal-displacement.org/global-report/grid2022/

@tikvahethiopia
የሚሊዮኖች የሳቅ ምንጭ የነበረው ኮሜዲየን ወንደሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሜዲ ዘርፍ ከታዩ እጅግ ተወዳጅ እና ምርጥ ኮሜዲያኖች እንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ ( #ዶክሌ ) በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየቱ ተሰምቷል።

ኮሜዲያኑ ላለፉት ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ ሀገር አድርጎ የነበረ ሲሆን ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የኮሜዲያን ወንደሰን (ዶክሌ) አጫጭር የኮሜዲ ስራዎች እጅግ በርካታ ሲሆኑ በተለያዩ ረጃጅም ፊልሞች ላይም በትወና ሰርቷል ፤ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በዚሁ ሞያ ውስጥ ቆይቷል።

ኮሜዲያኑ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

@tikvahethiopia