TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጉዳይ !

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል። ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።

ፈተናው መሰጠት በጀመረበት ሰኞ ኅዳር 29/2024 ዓ.ም ፈተናው ተሰርቋል የሚሉ ወሬዎች ቢናፈሱም፤ ፈተናው አለመሰረቁን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

"ተማሪዎች ተረጋግተው ይፈተኑ" በሚል ይመስላል መንግስት የማህበራዊ ሚዲያዎችን ቢያግዳቸውም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከፈተና ክፍል ውስጥ የተነሱ ፎቶዎች ባለፉት 2 ቀናት በቴሌግራም ግሩፖች ላይ ሲዘዋወሩ ታይተዋል።

ትላንት ለሊት አንስቶ ግን ዛሬ የተሰጡት (የባዮሎጂ፣ ታሪክና ኬሚስትሪ) ፈተናዎች ቀድመው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከፈተናው ጋር በተያያዘ በርካታ የቤተሰቡ አባላት የሰጡትን ጥቆማ እና ትላንት የተለያዩ ግሩፖች ላይ የተለጠፉትን የፈተና ወረቀቶች (በPDF እንዲሁም በፎቶ) በመያዝ ዛሬ ከፈተናው በኃላ ባደረገው ማጣራት ፈተናዎቹ እራሳቸው ሆኖ አግኝቷቸዋል።

ከበቂ #ማስረጃ ጋር ለማረጋገጥ የቻልነው የዛሬው ፈተና ለተፈታኞች ከመሰጠቱ ከሰዓታት በፊት ቀደም ብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱን ነው።

ቴሌግራምን ጨምሮ ማኅበራዊ ትስስር ገፅ ፈተናው ከጀመረ ቀን ጀምሮ ቢቋረጥም በቀላሉ በ VPN ግንኙነቱን ማስቀጠል በመቻሉ ተማሪዎች ሲቀባበሉት አስተውለናል።

ለዓመታት የደከሙ ተማሪዎችን ልፋት ከንቱ በሚያስቀርና ትውልድን በሚገድል ድርጊት የተሳተፉ፣ የሚተባበሩ፣ የሚያጋሩ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

መንግስት ይህንን ፈትሾ ተጠያቂ መሆን ያለበትን አካል በአፋጣኝ ማሳወቅ ይኖረበታል ሲሉ የቲክቫህ ቤተሰብ የሆኑ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጉዳይ ! የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል። ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል። ፈተናው መሰጠት በጀመረበት ሰኞ ኅዳር 29/2024 ዓ.ም ፈተናው ተሰርቋል የሚሉ ወሬዎች ቢናፈሱም፤ ፈተናው አለመሰረቁን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም። "ተማሪዎች ተረጋግተው ይፈተኑ" በሚል ይመስላል መንግስት የማህበራዊ ሚዲያዎችን…
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ የሰጡት ቃል ፦

" ምንም የተሰረቀ ነገር የለም። ለተፈታኞች የደረሰ ምንም ነገር የለም።"

"ተማሪዎች ወደ ፈተና ከገቡ በኋላ ፈተናውን ፎቶ በማንሳትና ወደ PDF በመቀየር ያደረጉትን ሙከራ ተቆጣጥረንዋል። ምንም impact አያመጣም"

"ፈተናው ተሰርቋል ሊባል የሚችል አይደለም። የተሰረቀ ነገር የለም።"

@tikvahethiopia
" ውሃ አልተበከለም "

በደብረ ማርቆስ ከተማ እንዲሁም በደጀን ወረዳ " ውሃ ተበክሏል " እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ሀሰት ነው።

ተገቢውን የውሃ ምርመራና ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን ምንም ዓይነት የመበከል ችግር አላጋጠመም ፤ ያለምንም ስጋት ውሃን በተለመደው መንገድ መጠቀም ይቻላል።

ነዋሪዎች ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሸበር በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች እንዳትደናገጡ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰበር ዜና‼️ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ዛሬ ጠዋት #ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ #ናይሮቢ ሲበር #ተከስክሶ የሰው ህይወት አልፏል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቦይንግ

አውሮፕላን አምራች የሆነው ቦይንግ መጋቢት 01 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ አደጋ ከሞቱት 157 መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች ቤተሰቦች ጋር ስምምነት ላይ ደረሰ።

ቦይንግ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድና ተጠያቂነቱንም እንደሚቀበል በቺካጎ ከሚገኘው የፍርድ ቤት ሰነዶች መረጃ ማግኘት ተችሏል።

በምላሹም የተጎጂ ቤተሰቦች ከኩባንያው የቅጣት ካሳ አይጠይቁም።

የተጎጂ ቤተሰቦች ጠበቆች እንዳሉት ቦይንግ ለአደጋው "ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ይሆናል" ሲሉ ስምምነቱን እንደ ትልቅ ምዕራፍ ተቀብለውታል።

ከዚህም ዜና ጋር ተያይዞ የቦይንግ አክሲዮኖች ድርሻ 1 በመቶ፣ ወደ 218.50 ዶላር ወርዷል።

ስምምነቱ ከአሜሪካ ውጪ ያሉ እንደ #ኢትዮጵያ እና #ኬንያ ባሉ አገራት ያሉ የተጎጂ ቤተሰቦች በአገራቸው ሳይሆን በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች ካሳ እንዲከፈላቸው መንገድ ከፍቷል።

ካሳው የሚፈጸመው በየአገራቸው ቢሆን የበለጠ ሁኔታውን ፈታኝ እንደሚያደርገውና ክፍያውም ዝቅተኛ እንደሚሆን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#StateofEmergencyEthiopia

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ቁ.2 !

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሀገራዊ ሁኔታ እና የአዋጁን አፈጻጸም ትላንት ማምሻውን መገምገሙን አሳውቋል።

ዕዙ ለኅብረተሰቡ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ፣ የአዋጁን አፈጻጸም እና ወታደራዊ ርምጃዎች በመገምገም የተለያዩ ድሎች መመዝገባቸውን ማረጋገጡን ገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ " በአማራና በአፋር ክልሎች የክተት አዋጁን ተከትሎ በጠላት ላይ እየተወሰደ ያለው ርምጃ አመርቂ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል።

" ለዚህ መሠረቱ የሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ መነሣሣትና ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፈጠረው ንቅናቄ መሆኑ ተረጋግጧል " ሲል ገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ፥ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሆሮጉድሩ እና በምሥራቅ ወለጋ አንዳንድ ወረዳዎች በአሸባሪ ቡድኑ ሸኔ ላይ በክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ሀገር መከላከያ በጋራ ከፍተኛ ድል ተጎናፅፈዋልም ብሏል።

ዕዙ ድሉን ለማስቀጠል 3 ትእዛዞችን ማስተላለፉንም ገልጿል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#DireDawa

የድሬዳዋ ፖሊስ ማንኛውም ድሬዳዋ ከተማና ገጠር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ፍቃድ ቢኖረውም ባይኖረውም በአቅራቢያው በሚገኝ የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በግንባር በመሄድ ማስመዝገብ እንዳለበት በጥብቅ አሳስቧል።

ድሬዳዋ ፖሊስ ፥ ከህዳር 2 ቀንእስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት 2 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ሳያስመዘግብ የቀረ ከሆነ በህግ አግባብ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል፡፡

@tikvahethiopia
#AWI

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጫት ቤቶች እንዲዘጉ ተወሰነ።

ብሔረሰብ አስተዳደሩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል የመጀመሪያው ጫት ቤቶች እንዲዘጉ የሚል ነው።

በተጨማሪም ከየትኛውም ከተማ ከምሽቱ 2:00 በኋላ መንቀሳቀስ እንደማፈቀድ (በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት) ተገልጿል።

የመንግሥት እና የግል መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ተወስኗል።

መኝታ ቤት የሚያከራዩ ሰዎች ማንነትን እንዲያረጋግጡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተከራይ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ማንም ሰው ተኩስ ከተኮሰ መሳሪያውን እንደሚቀማ ውሳኔ ተላልፏል።

ማንኛውም ግለሰብ በየአካባቢው ተደራጅቶ በሮንድ አካባቢውን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት የማይተባበር ከሆነ በህግ እንደሚጠየቅ ተወስኗል።

ከመንግስት በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት ድጋፍ ያላደረጉ አካላት እንዲደግፍ ፣ እንዲከፍሉ ካልከፈሉ ድርጅታቸው ታሽጎ አገልግሎት እንዳያገኙ እንዲደረግ ተወስኗል።

(አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጧል)

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጉዳይ ! የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል። ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል። ፈተናው መሰጠት በጀመረበት ሰኞ ኅዳር 29/2024 ዓ.ም ፈተናው ተሰርቋል የሚሉ ወሬዎች ቢናፈሱም፤ ፈተናው አለመሰረቁን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም። "ተማሪዎች ተረጋግተው ይፈተኑ" በሚል ይመስላል መንግስት የማህበራዊ ሚዲያዎችን…
#ተጨማሪ

ትላንት የተሰጡት የታሪክ ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ከፈተናው በፊት ቀድሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መሰራጨቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቂ ማስረጃ ማረጋገጡ ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጠውም የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር (ሲቪክ) ትምህርት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ እንደነበርና ዛሬ የተሰጠው የፈተና ወረቀትም ትላንት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጨው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በበቂ ማስረጃ አረጋግጠናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቢዘጉም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አገልግሎቶቹ ቀጥለዋል።

ይህ ትውልድና እና ኢትዮጵያን የመግደል ተግባር በማን እና እንዴት እንደተፈፀመ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልግ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጠያቂው አካል መታወቅ ይኖርበታል።

ለዓመታት የለፉ ተማሪዎችን ድካም በሚያደናቅፍ ተግባር ላይ የተሳተፉ፣ ሲተባበሩ የነበሩ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ የነበሩ ሁሉ ሌላው ቢቀር ከሞራል ተጠያቂነት አይተርፉም።

በውጭ ያሉ የማህበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ አካላትም ሆነ የፖለቲካ ሰዎች ከምንም ጋር ግንኙነት የሌላቸው ተማሪዎችን የግል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ብቻ ሲሉ ኢ-ስነምግባራዊ በሆነ ትውልድን የመጉዳት ተግባር ላይ መሳተፋቸው እጅጉን የሚያሳዝን ነው።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ትምህርት ሚኒስቴር ስለጉዳዩ የሚለው ነገር ካለና ማብራሪያ ከሰጠ ተከታትሎ ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መከላከያ አርማውን ቀየረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ተቋማዊ አርማ መቀየሩን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ አስተወቁ።

ጄነራል መኮንኑ ፣ ተቋሙ ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ የቀየረው አዲስ ከፈጠረው አደረጃጀትና እየተገበረ ካለው ሪፎርም አኳያ ገላጭ ባለመሆኑ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

እንደ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ ገለፃ ፣ ተቋሙ አዲስ ይፋ ያደረገው አርማ ከተቋሙ ተልዕኮና ባህርይ አንፃር ልዩ ልዩ ትርጓሜዎችን የያዘ ነው።

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
#Somali

በሶማሊ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ 200 ሚሊዮን ብር ፀደቀ።

የሶማሊ ክልል መንግሥት ካቢኔ ዛሬ 7ተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል።

ስብሰባው በጎዴ ከተማ ነው የተካሄደው።

ካቢኔው በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ በተለይ ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች አስቸኳይ መልስ መስጠት የሚችልበት ሁኔታ ላይ በስፋት መክሯል።

በዚህም ድርቅ የተከሰተባቸውን አከባቢዎች ፈጣን መልስ ለመስጠት እና አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረስ 200 ሚልየን ብር ካቢኔው አፅድቋል።

#SRMMA

@tikvahethiopia
#GONDAR : ፖሊስ በጎንደር ከተማ ለእኩይ/ለሽብር ተግባር ሊውል ነበረ ያለውን ገጀራ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

ገጀራው በከተማው ቀበሌ 16 በተለምዶ ግሩፕ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግለሰብ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተገኘ ነው ተብሏል።

ማህበረሰቡ ባደረሰው ጥቆማ ከአንዲት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገወጥ ገጀራው መገኘቱን ያስረዳው የከተማው ፖሊስ ጥቆማ የተሰጠባት ግለሰብ ቤት ፖሊስ ሄዶ ህገወጥ ገጀራ መኖሩን ሲጠይቅ ምንም ነገር እንደሌለ መግለጿ ተመላክቷል።

ነገር ግን በተደረገው ፍተሻ በአልጋ ስር በከፍተኛ ሁኔታ የተደበቁ ገጀራዎች መገኘቱን እና ገጀራው ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ያልዋለና ለእኩይ አላማ ሊውል እንደታሰበ ያመለክታል ብሏል ፖሊስ።

የጎንደር ፖሊስ አሁን ላይ ነባራዊ ሁኔታውን መሰረት ባደረገ ሁኔታ በሮችን ከሁሉም የፀጥታ ኀይል ጋር በመሆን 24 ሰዓት እየጠበቀ መሆኑን ወንጀልንና ወንጀለኞችን መከላከልና መቆጣጠር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በቀጣይም ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን መሰል ህገወጦችን በቁጥጥር ስር እያዋልነ ወደ ህግ የማቅረብ ተግባሩ እንደሚቀጥል አሳቋል።

ምንጭ ፦ የጎንደር ከተማ 4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጫ ሰጥቷል።

ኤጀንሲው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል ብሏል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ ነው ያሳወቁት።

በ2 ሺ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው በዚህ ፈተና፣ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617 ሺ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565ሺ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ዘርፉ ሰራተኞችና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ፈተናዎች ተሰርቀው ወጥተዋል የሚባለው ጉዳይ እውነት ነወይ" ተበለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ምርምርራዎችና ትንተናዎች ተደርገው አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ምንም የሚያስጋ ነገር የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#SUDAN : የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት አቋቋሙ፡፡

ቡርሃን ምክር ቤቱን ያቋቋሙት በመፈንቅለ መንግስቱ የፈረሰውን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ለመተካት ነው፡፡

አዲስ የተመሰረተው ምክር ቤት 15 አባላት ያሉት ሲሆን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን ሲመሩት የነበሩት ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ም/ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል፡፡

ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን በምክትልነት ሲመሩ የነበሩት ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳገሎ (ሄሚቴ)ም በአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪነት እንደሚቀጥሉ ቡርሃን አስታውቀዋል፡፡

ከ15ቱ የምክር ቤቱ አባላት መካከልም 5ቱ የሃገሪቱ ጦር መሪ ጄነራሎች ናቸው፡፡

የሱዳን ጦር ከ20 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሚመራው የሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎም የሲቪል አስተዳድሩ ወደ ቀድሞ ስልጣኑ እንዲመለስ የሱዳን ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia