TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጉዳይ ! የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል። ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል። ፈተናው መሰጠት በጀመረበት ሰኞ ኅዳር 29/2024 ዓ.ም ፈተናው ተሰርቋል የሚሉ ወሬዎች ቢናፈሱም፤ ፈተናው አለመሰረቁን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም። "ተማሪዎች ተረጋግተው ይፈተኑ" በሚል ይመስላል መንግስት የማህበራዊ ሚዲያዎችን…
#ተጨማሪ

ትላንት የተሰጡት የታሪክ ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ከፈተናው በፊት ቀድሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መሰራጨቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቂ ማስረጃ ማረጋገጡ ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጠውም የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር (ሲቪክ) ትምህርት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ እንደነበርና ዛሬ የተሰጠው የፈተና ወረቀትም ትላንት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጨው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በበቂ ማስረጃ አረጋግጠናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቢዘጉም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አገልግሎቶቹ ቀጥለዋል።

ይህ ትውልድና እና ኢትዮጵያን የመግደል ተግባር በማን እና እንዴት እንደተፈፀመ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልግ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጠያቂው አካል መታወቅ ይኖርበታል።

ለዓመታት የለፉ ተማሪዎችን ድካም በሚያደናቅፍ ተግባር ላይ የተሳተፉ፣ ሲተባበሩ የነበሩ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ የነበሩ ሁሉ ሌላው ቢቀር ከሞራል ተጠያቂነት አይተርፉም።

በውጭ ያሉ የማህበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ አካላትም ሆነ የፖለቲካ ሰዎች ከምንም ጋር ግንኙነት የሌላቸው ተማሪዎችን የግል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ብቻ ሲሉ ኢ-ስነምግባራዊ በሆነ ትውልድን የመጉዳት ተግባር ላይ መሳተፋቸው እጅጉን የሚያሳዝን ነው።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ትምህርት ሚኒስቴር ስለጉዳዩ የሚለው ነገር ካለና ማብራሪያ ከሰጠ ተከታትሎ ያሳውቃል።

@tikvahethiopia