#SUDAN : የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት አቋቋሙ፡፡

ቡርሃን ምክር ቤቱን ያቋቋሙት በመፈንቅለ መንግስቱ የፈረሰውን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ለመተካት ነው፡፡

አዲስ የተመሰረተው ምክር ቤት 15 አባላት ያሉት ሲሆን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን ሲመሩት የነበሩት ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ም/ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል፡፡

ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን በምክትልነት ሲመሩ የነበሩት ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳገሎ (ሄሚቴ)ም በአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪነት እንደሚቀጥሉ ቡርሃን አስታውቀዋል፡፡

ከ15ቱ የምክር ቤቱ አባላት መካከልም 5ቱ የሃገሪቱ ጦር መሪ ጄነራሎች ናቸው፡፡

የሱዳን ጦር ከ20 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሚመራው የሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎም የሲቪል አስተዳድሩ ወደ ቀድሞ ስልጣኑ እንዲመለስ የሱዳን ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia