TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የብሄራዊ ባንክ ማሳሰቢያ ፦

ብሔራዊ ባንክ በትግራይ ክልል የአሮጌ ብር ቅያሪ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉ ቀናት እንዲጠናቀቅ ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል።

ኅብረተሰቡ የባንክ ቅርንጫፎች በተከፈተባቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በመሄድ ገንዘቡን እንዲቀይር ተብሏል።

ባንኮችም በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ዛሬ የብሄራዊ ባንክ እንዳለው በትግራይ ይቀየራል ተብሎ የሚታሰበው የአሮጌ የገንዘብ መጠን በአብዛኛው ተቀይሯል ፤ ያልተቀየረው ቀሪ ገንዘብም ጥቂት ነው ፤ ይህ እንዲጠናቀቅ ነው የጊዜ ገደብ ያስቀመጠው።

Source : ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዚህ ሳምንት የተከሰቱ እሳት አደጋዎች፦

በዚህ ሳምንት በይፋ የተገለፁ /ስለደረሱት አደጋዎች መረጃ በሚዲያ ላይ የተሰራጨ ሶስት የእሳት አደጋዎች መከሰታቸውን ተመልክተናል።

#MgandoCity

በጉጂ ዞን መጋዶ ከተማ የካቲት 23 በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር የሚገመት ንብረት አውድሟል። የእሳት አደጋው 29 መኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን አቃጥሏል።

19 አባወራዎች ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ ወድሞባቸዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው።

#DebrebrhanCity

በደብረብርሃን ከተማ የካቲት 24 በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል።

አደጋው ከቀኑ 9 ሰዓት ተኩል በከተማው ቀበሎ 03 ቀጠና 1 ነው የደረሰው።

የእሳት አደጋው ንብረት አውድሟል ፣እንሰሳትን ገድሏል።

በእሳት አደጋው አንድ ባህላዊ ፎቅ ቤት ፣ ሁለት ቆርቆሮ ቤቶች ፣ ሁለት የሳር ቤቶችና አንድ ኩሽና ተቃጥለዋል ፤ በውስጣቸው የነበረ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በተጨማሪ የከብቶች እና የዶሮች መኖ ተቃጥሏል ፣ግምታቸው ያልታወቀ በጎች ፣ ቁጥራቸው በትክክል ያልተገለጸ ዶሮች በአደጋው ተቃጥለዋል።

የአደጋው መንስዔ እየተጣራ ነው።

#SouthBenchWoreda

ትላንት የካቲት 26 ምሽት በደቡብ ቤንች ወረዳ ጌሊት ቀበሌ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የተከሰተው የእሳት አደጋ በቤት እና ንብረት ላይ ውድመት አድርሷል።

የእሳት አደጋው የ6 ግለሠቦች መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም የተለያየ አገልግሎት የሚሠጡ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

የእሳት አደጋው መንስኤና ያወደመው ንብረት እየተጣራ ነው።

* ዛሬ የካቲት 27 ደግሞ ሎግያ ፒያሳ አከባቢ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር ጥቆማ ደርሶናል፤ ስለአደጋው ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ ፕሬዜዳንት ሱዳን ገቡ። የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ ሱዳን የገቡት ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዑክ ጋር ነው። አልሲሲ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ተቀብለዋቸዋል። የአንድ ቀን ቆይታ በሱዳን ይኖራቸዋል የተባለው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ምክክር…
የግብፁ ፕሬዜዳንት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ በሱዳን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሱዳን ቆይታቸው ከሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ውይይት አድረገዋል ፤ በጋራም መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንት ሲ ሲ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ፦ ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የምታደርግ ከሆነ የሁለቱን ሀገራት ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዘዳንቱ ከዚህ ቀደም ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት (AU) በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የአውሮፓ ህብረት (EU) እና አሜሪካ በግዱቡ ጉዳይ አደራዳሪ እንዲሆኑ ያቀረበችውን ሀሳብ ግብፅም ትደግፋለች ብለዋል።

Source : SUNA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት 16 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞቱ።

ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የምታጣቸው ዜጎቿ ቁጥር እየጨመረ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 16 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 2,420 ደርሰዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 6,406 የላብራቶሪ ምርመራ 956 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ይህም በኢትዮጵያ አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር 165,029 አድርሶታል።

ትላንት 354 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ 427 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Tikvah #Purpose
@tikvahethiopia
በሁለተኛ ዙር የ40/60 ዕጣ የወጣላችሁ ባለዕድለኞች ፦

የአ/አ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ የወጣባቸውን ቤቶች ከፊታችን ሰኞ የካቲት 29/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአፈፃፃማቸው የተሻሉ የግንባታ ሳይቶችን ለባለ ዕድለኞች ቁልፍ ርክክብ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ዛሬ ምሽት አስታውቋል።

ባለእድለኞች ከፊታችን ሰኞ የካቲት 29/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአፈፃፃማቸው የተሻሉ የግንባታ ሳይቶችን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በየቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የቤቶቹን ቁልፍ ለባለ ዕድለኞች ርክክብ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።

በሚወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ቁልፍ የሚረከቡ ባለ ዕድለኞች የቤቶቹን ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ማሰራት የሚችሉ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

በመጀመሪያ ዙር ላይ የተካተቱ 220 ህንፃዎች የሚገኙበት የግንባታ ሳይቶች ዝርዝር የሚከተለው ነው ፦

1. መሪ ሎቄ (14 ህንፃዎች)
2. እህል ንግድ (5 ህንፃዎች)
3. ህንፃ አቅሪቢ (8 ህንፃዎች)
4. አስኮ (13 ህንፃዎች)
5. አያት 1 ሳይት 1 (14 ህንፃዎች)
6. አያት 1 ሳይት 2 (38 ህንፃዎች)
7. አያት 1 ሳይት 3 (41 ህንፃዎች)
8. አያት 1 ሳይት 4 (39 ህንፃዎች)
9. ሰሚት (8 ህንፃዎች)
10. ቦሌ ቡልቡላ ሎት 1 (27 ህንፃዎች)
11. ቦሌ ቡልቡላ ሎት 2 (13 ህንፃዎች)

Via Addis Ababa Press Secretary
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የመጀመሪያዎቹ የኮቪድ-19 ክትባቶች ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሱ !

ኢትዮጵያ በኮቫክስ የግዢ ስርዓት የተገኙ የመጀመሪያዎቹን 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ክትባቶች ተቀበለች።

ክትባቶቹ በህንዱ ሴረም ኢንስቲትዩት የተመረቱ የአስትራ ዜኔካ ክትባቶች ናቸው።

በኢትዮጽያ አየር መንገድ ተጭነው ዛሬ ጠዋት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በደረሱ ጊዜ የጤና ሚኒስትሯን ዶ/ር ሊያ ታደሰን ጨምሮ ከፍተኛ የአፍሪካ ህብረት የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም የመንግስታቱ ድርጅት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን ክትባቶች በማግኘቷ "እንኳን ደስ ያላችሁ" ያሉት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በክትባቶቹ የግዢ ሂደት ያደረጉ አጋር አካላትን አመስግነዋል።

ክትባቶቹ ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ ግንባር ቀደም ለሆኑት የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎችም የሚሰጡ ይሆናል።

ምንጭ ፦ አል ዓይን (ፎቶ - አብመድ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Video : በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት የተገኘው 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ክትባት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል።

WHO-Ethiopia ክትባቱ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ ፥ "ይህ የCOVID-19 ክትባቶችን በፍትሃዊነት ማሰራጨት ለማረጋገጥ ትልቅ እርምጃ ነው" ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማቸውን ለማቆም ተስማሙ።

በረሃብ አድማ ላይ ለበርካታ ቀናት መቆየታቸው የተነገረው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከነገ፣ ሰኞ የካቲት 29 2013 ዓ.ም ጀምሮ የረሃብ አድማቸውን ለማቆም መስማማታቸውን ጠበቆቻቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከነገ፣ ሰኞ የካቲት 29 2013 ዓ.ም ጀምሮ የረሃብ አድማውን የሚያቋርጡት በላንድማርክ ሆስፒታል የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ መሆናቸውን ጠበቆቻቸው አቶ ቱሊ ባይሳ እና አቶ ገመቹ ጉተማ አረጋግጠዋል።

ጠበቃው አቶ ገመቹ ጉተማ እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ዛሬ 39ኛ ቀናቸው መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ ነው።

"ትናንት ከ20 በላይ የአገር ሽማግሌዎች እና ፖለቲከኞች በሆስፒታሉ ተገኝተው ነበር። ይሁን እንጂ ወደ ሆስፒታሉ እንዲገቡ አልተፈቀደላቸውም ነበር። ዛሬ ዳግም ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት ከሽማግሌዎቹ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና ሱፐር ኢንቴንደንት ሁሴን ሸቦ ወደ ሆስፒታሉ ገብተው የረሃብ አድማውን አንዲያቆሙ ተማጽነዋቸዋል" ብለዋል ጠበቃው አቶ ገመቹ።

እነ አቶ ጃዋር ከነገ፣ ሰኞ ጀምሮ የረሃብ አድማውን ለማቋረጥ የተስማሙት የረሃብ አድማ ማድረግ የጀመሩበት ጥያቄያቸው ምላሸ አግኝቶ ሳይሆን፤ "ሃኪሞቻቸው፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ፖለቲከኞች ባደረጉት ልመና፣ ጫና በርትቶባቸው ነው። እሺታቸውን ለሽማግሌዎች ሰጥተዋል። ከነገ ጀምሮ የረሃብ አድማቸውን ያቆማሉ" ብለዋል አቶ ገመቹ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ፦

• የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ - 6,490
• በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 1,109
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 715
• ፅኑ ተማሚዎች - 436

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

በ2012 ዓ/ም መሰጠት የነበረበት እና በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት ሳይሰጥ የቀረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከነገ የካቲት 29 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው የሚሰጥባቸው በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የፈተና ማዕከላት / ጣቢያዎች ዝግጅታቸውን አጠናቀው የፈተናውን ሰዓት እየተጠባበቁ መሆኑን ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን አስመልክቶ ኦረንቴሽን ተሰጥቷቸዋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT