TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ ፕሬዜዳንት ሱዳን ገቡ። የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ ሱዳን የገቡት ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዑክ ጋር ነው። አልሲሲ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ተቀብለዋቸዋል። የአንድ ቀን ቆይታ በሱዳን ይኖራቸዋል የተባለው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ምክክር…
የግብፁ ፕሬዜዳንት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ በሱዳን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሱዳን ቆይታቸው ከሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ውይይት አድረገዋል ፤ በጋራም መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንት ሲ ሲ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ፦ ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የምታደርግ ከሆነ የሁለቱን ሀገራት ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዘዳንቱ ከዚህ ቀደም ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት (AU) በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የአውሮፓ ህብረት (EU) እና አሜሪካ በግዱቡ ጉዳይ አደራዳሪ እንዲሆኑ ያቀረበችውን ሀሳብ ግብፅም ትደግፋለች ብለዋል።

Source : SUNA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia