TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DireDawa

በድሬዳዋ በእርሻ ማሳ ውስጥ አደገኛ እፅ ተከለው የተገኙት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አደገኛው የካናቢስ እጽ በእርሻ ማሳቻው ላይ ተክለው የተገኙ 2 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።

እጹ ሊያዝ የቻለው በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 08 ገንደ- ገበሬ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ተጠርጣሪ ግለሰብ በእርሻ ማሳ ውስጥ የተተከሉትን አደገኛ እፅ በመኮትኮት ላይ እንዳለ መሆኑ ተገልጿል።

ፖሊስ ወደ ቦታው የደረሰው በአካባቢው ላይ ሌላ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞ ሲሆን የአካባቢው ሚሊሻዎች ግለሰቡ እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ተመልክተው ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሰረት ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ከተከሉት በርካታ እጽ ጋር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከተማው ውስጥ ይሄንኑ አደገኛ እጽ የመሸጥ ስራ ከምትሰራ ሌላ ተጠርጣሪ ግለሰብ ጋር ግንኙነት በማድረግ ግለሰቧ አደገኛ የካናቢስ እጽ ስትሸጥ ተገኝታ ምርመራ ተጣርቶ ውሳኔ ማግኘቷን ፖሊስ ገልጿል።

በድሬዳዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን አደገኛ የካናቢስ እጽ ዝውውርን ለመግታት ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ ያሳወቀው ፖሊስ ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል እየጎዳ የሚገኘውን አደገኛ እጽ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ

@tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

#Amhara, #Gashena

ጋሸና ከተማ ተቋርጦባት የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማግኛቷን ተገልጿል። በአካባቢው ያሉ ሌሎች ከተሞችን የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና እየተካሄደ ሲሆን በነገው እለት ፋላቂት፣ ገረገራ፣ ኮን እና በአካባቢው ያሉ ከተሞች የተቋረጠባቸውን ኃይል መልሰው ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#Afar

በአፋር በክልል በህወሓት ወረራ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀመር የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል በህልውና ዘመቻው ምክንያት ለአንድ ወር በላይ በከፊል ተዘግተው የቆዩት የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች (ከጥቂቶቹ በስተቀር) ዛሬ መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል።

#AddisAbaba

በአ/አ ህገ ወጥ መሬት ወረራ በተሳተፉ 88 አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ፓለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአ/አ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ከ26 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸውና በህገ ወጥ የመሬት ወረራ የተያዙ 671 ይዞታዎች ካርታቸው እንዲመክን ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ መመለሳቸው ሪፖርት ተደርጓል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ኤርፖርት የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑ የድሬዳዋ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አሳውቋል። ትላንት ከቀኑ 10:50 ላይ የአውሮፕላኑን አቅጣጫና የርቀት መለኪያ፣ የኃይል መቆጣጠሪያና የመገናኛ መሳሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መጨመር (high voltage) ምክንያት በተከሰተ ቃጠሎና ፍንዳታ የኃይል መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ላይ አደጋ ደርሷል። በኃላ ችግሩን በማስተካከል ዛሬ ጥዋት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ የአውሮፕላን በረራ እንዲካሄድ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው።

ለቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ አስተዳደሩ በአመራርነት ዘመናቸው ላበረከቱት መልካም ስራዎች የምስጋና ኘሮግራም ተካሄዶል።

በዚሁ ፕሮግራም ላይ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘመናዊ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ " ጥቂት ብንዘገይም፤ እጅግ ለምንወዳቸው የቀድሞ ከንቲባችን እና ወንድማችን አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ዛሬ ያደረግነው ሽኝትና የሰጠነው ስጦታ፤ በአመራርነት ዘመኑ ካደረጉት አሰተወፅኦ አንፃር ለሳቸው ያንስባቸዋል እንጂ አይበዛም " ሲሉ ተናግረዋል።

ስጦታው በባለሀብቶች ተሳትፎ የተበረከተ መሆኑ ተገልጿል።

የቀድሞው ከንቲባ ለሶስት ዓመት ሙሉ ከተማዋ የነበረባትን የፀጥታ ችግር የፀጥታ አካላትን በማሰባሰብ ፣ አመራሮችን በማቀናጀት የከተማዋ ሰላም በአስተማማኝነት እንዲረጋገጥ እና ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ እንደነበሩ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ከቀድሞ ከንቲባው በተጨማሪ የድሬዳዋ ፀጥታ አካላት ፣ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ከ25 ሺህ ብር እስከ 100 ሺህ ብር በየደረጃው ተሸልመዋል። አጠቃላይ ሽልማቱ ከ700 ሺህ ብር በላይ እንደሆነ ተመላክቷል።

ብሩ የተገኘው ከባለሀብቶች ሲሆን የመንግስት በጀት እንዳልተነካ ተገልጿል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጠይቀው ቀና ምላሽ ለሰጡ የከተማው ባለሀብቶች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

1443 ኛው የረመዳን ፆም ወር የአፍጢር መርሀ-ግብር በአሁን ሰአት በለገሀር አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ የአፍጢር መርሀ-ግብር ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ፎቶ ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#DireDawa

" በሲሚንቶ ላይ በሚታየው ከከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ቤት መገንባት እስከማቆም ደርሷል ፥ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም እየዘገዩ ነው " - አቶ ከድር ጁሃር

በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በየጊዜው በተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች ፣ የምግብ ፍጆታዎች እንዲሁም በኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ላይ ሲሚንቶን ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ድሬድዋ ከተማም አንዷ በዋጋ ንረት ጫና እየደረሰባት ያለች ከተማ ናት፤ በተለይ ሲሚንቶን ጨምሮ የኮንስትራክሽን እቃዎች የዋጋ ንረት ነዋሪዎችን ክፉኛ እየፈተነ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ፤ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን የገለፀ ሲሆን የስሚንቶ ፋብሪካ (ናሽናል ሲሚንቶ) እዛው ድሬዳዋ እያለ የዋጋ ንረቱ አልቀመስ ማለቱ ፥ ነዋሪው ቤት መስራት እስከማቆም መድረሱን ፣ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም እየዘገዩ መሆኑ አስረድቷል።

እዛው ድሬዳዋ ላይ የስሚንቶ ፋብሪካ ያለው ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ አ.ማ (ናሽናል ሲሚንቶ) በድሬዳዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ለመቆጠር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል።

የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የሚያመርተውን የሲሚንቶ ምርት በ440 ብር ለአከፋዮች ቢያቀርብም በአስተዳደሩ ታች ላለው ቸርቻሪዎችና ማህበረሰቡ ጋር ሲደርስ ግን አላግባብ በሆነ ጭማሪ ከ700 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ችግሩን ለመፍታትና ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የድሬዳዋ አስተዳደር ለይቶ ባደራጃቸውና ህጋዊ የሲሚንቶ ችርችሮ ሻጮችና ሲሚንቶ በቀጥታ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የማድረስ ስራል ብሏል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dire-Dawa-04-09

@tikvahethiopia
#DireDawa

#ማሻሻያ

በድሬዳዋ አስተዳደር እሁድ ጠዋት ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን የተወሰነው ውሳኔ ላይ ማሻሻዮች ተደርጎበታል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ላይ ከጠዋት 12 ሰአት እስከ 4 ሰአት ድረስ በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል ።

በዚሁም ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።

በተለይም እድሜያቸው የገፍ እናት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እሁድ ወደ ቤተ-እምነቶች ለመሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በእጅጉ እየተቸገሩ ከመሆናቸው ባለፈ የጤና እክል ያለባቸው አካላትም ረጅም እርቀት በእግር ለመሄድ መቸገራቸውንም የሀይማኖት አባቶቹ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

ስለሆነም ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እሁድ ጠዋት በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ህብረተሰብ እንዲሁም ከሀይማኖት አባቶች የተነሱትን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት እሁድ ጠዋት ሙሉ ከተማው ለትራንስፖርት ክፍት እንዲሆን መወሰኑን አሳውቀዋል።

ነገር ግን ከኮኔል ድልድይ አንስቶ ከዚራ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለትራንስፖርት ዝግ እንደሚሆንም ከንቲባው ተናግረዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለቀጣይ አምስት ወር በመኖሪያ ቤት ተከራዮች ላይ ጭማሪ ማድረግም ሆነ ተከራዮችን ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ አሳልፏል።

ከተማ አስተዳደሩ ፤ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ እና አለአግባብ ከፍተኛ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተለያየ መንገድ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ይህን ተከትሎ ነው ለ 5 ወራት ተከራዮች ላይ ጭማሪ ማድረግ ሆነ ከተከራዩት ቤት ማስወጣት እንደማይቻል ውሳኔ ያሳለፈው።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳፋሪኮም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው። በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች…
#DireDawa #SafaricomEthiopia

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች አገልግሎት በ " 700 " ላይ በመደወል ማግኝት ይቻላል።

ዛሬ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ ጀምሯል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቶች በጥሪ ማዕከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም ፦
- በአማርኛ
- በአፋን ኦሮሞ
- በሱማሊኛ
- በትግርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ የማግኘት አማራጭ የሚኖራቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን " 700 "  ላይ በመደወል ማናገር ይችላሉ።

* ማስታወሻ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት ናቸው። የሽያጭ ማዕከሎቹ የሚገኙት ፦
- #ከዚራ
- #መስቀለኛ
- #ኮርኔል ነው።

#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa

@tikvahethiopia
#DireDawa

3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ውጭ ተደርጎበት ተገንብቷል የተባለው የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እና ተርሚናል ዛሬ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።

የድሬደዋ ወደብ እና ተርሚናል በ34 ነጥብ 1ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ባለሶስት ወለል የቢሮ ህንፃ ፣ መጋዘን ፣ የኮንቴይነር ተርሚናልና 10 ሄክታር የውስጥ ለውስጥ የኮንክሪት መንገድ አለው ተብሏል።

በተጨማሪም በአንድ ጊዜ 140 መኪናዎች ማቆም የሚያስችል የተገነባ ቦታ፤ ሁለት የዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን እንዲሁም ወደቡን ከኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር የሚያገናኝ #የባቡር_ሃዲድ የተሰራለት እንደሆነ ተገልጿል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ " ሰልባጅ ተራ / አሸዋ " ከጥዋት አንስቶ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሷል።

አደጋው ጥዋት 1:45 የተነሳ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ድሬ ቲቪ የሶማልኛ ቋንቋ ክፍል ዘግቧል።

በቃጠሎ እስካሁን በሰዎች ሕይወት ላይ የደረሰ የሞት አደጋ ባይኖርም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱ ግን ተጠቁሟል።

አሁንም እሳቱን የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

#DireDawa
#DireTVSOMALI

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa በድሬዳዋ ከተማ " ሰልባጅ ተራ / አሸዋ " ከጥዋት አንስቶ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሷል። አደጋው ጥዋት 1:45 የተነሳ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ድሬ ቲቪ የሶማልኛ ቋንቋ ክፍል ዘግቧል። በቃጠሎ እስካሁን በሰዎች ሕይወት ላይ የደረሰ የሞት አደጋ ባይኖርም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱ ግን ተጠቁሟል። አሁንም እሳቱን…
#Update #DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ የገበያ ስፍራ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በተለምዶ ' አሸዋ ' በመባል በሚጠራው የገበያ ስፍራ ዛሬ ጠዋት ተነስቶ የነበረው የእሳት አደጋ፥ በርካታ የመሸጫ ሱቆችና ማሽላ ተራ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን ተመልክተዋል።

የአደጋውን መንስኤና የጉዳት መጠን በምርመራ በማጣራት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የእሳት አደጋው ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጉ ነዋሪዎች የጸጥታ ኃይል ምስጋና አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከድሬ ቴሌቪዥን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ዛሬ በድሬዳዋ በደረሰው ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ከንቲባ አቶ ከድር ፥ ከጥዋት 1 ሰዓት ጀምሮ በተለምዶ ' አሸዋ ' በሚባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ፦
ሩዝ ተራ
ማሽላ ተራ
ሰልባጅ ተራ ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ አሳውቀዋል።

ሌሎች በከፊል የተረፉ እንዳሉ ጠቁመዋል።

እሳቱ አሁን ላይ ካደረሰው ጉዳት ባለፈ እጅግ በጣም የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችል እንደነበር ጠቁመው እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብር ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

Credit : DireTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ዛሬ በድሬዳዋ በደረሰው ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ከንቲባ አቶ ከድር ፥ ከጥዋት 1 ሰዓት ጀምሮ በተለምዶ ' አሸዋ ' በሚባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ፦ ሩዝ ተራ ማሽላ ተራ ሰልባጅ ተራ ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ አሳውቀዋል። ሌሎች በከፊል የተረፉ እንዳሉ ጠቁመዋል።…
#ድሬ

ከቀናት በፊት ድሬዳዋ ' አሸዋ ገበያ ' ስፍራ እጅግ በጣም የከፋ የእሳት አደጋ ደርሶ እንደነበር ይታወቃል።

በአደጋው በርካታ ነጋዴዎች አንድም ሳይቀር ነገር ሳይቀር ንብረታቸው ወድሟል።

አሁን ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጎጂዎች እንዲረዱ ለማድረግ " ድሬዳዋ ትጣራለች !! " በሚል ዘመቻ ጀምሯል።

ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረጊያ የሒሳብ ቁጥርም ይፋ ተደርጎ ድጋፍ እየተሰባደበ ነው። የሒሳብ ቁጥሮቹ  ፦
• ንግድ ባንክ ፦ 1000637750201
• ዳሽን ባንክ ፦ 5009786342011
• አዋሽ ባንክ ፦ 013211367855100
• የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፦ 1001300318808 ሲሆኑ ' BESAT ADEGA LETEGODU WOG DIGAF MAS ' ይላል።

በሌላ በኩል ፤ የስልጤ ልማት ማኅበር እና የስልጤ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት ለተጎጂዎች እያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር (በድምሩ 2 ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ማድረጋቸው ተነግሯል።

#DireDawa

@tikvahethiopia
#DireDawa : ዶክተር ጌታቸው ጫካቤኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዶ/ር ጌታቸው ጫካቤኛ በድሬዳዋ የመጀመሪያው የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ነበሩ።

ከአርባ ዓመታት በላይ በድሬዳዋ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በህጻናት ህክምና ስፔሻሊስትነት ፣ በህክምና ዘርፍ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ወገናቸውን አገልግለዋል።

በስራ ልምዳቸውም በርካቶችን አብቅተዋል።

ድሬዳዋ " ባለውለታዬን አጣኋቸው " ብላለች።

ከንቲባ ከድር ጁሀር  " ለረጅም ዓመታት በከተማው የህፃናት አለኝታ በመሆን ጡረታ እስኪወጡ የድሬዳዋን ህዝብ በፍቅር ነው ያገለገሉት " ሲሉ በህልፈታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

በዶ/ር ጌታቸው የህክምና ጥበብ ከህመማቸው የተፈወሱ በርካታ ህፃናት እና ወላጆች እንደሆኑ ገልጸው ሀዘኑ የመላው ከተማ እንደሆነ በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።

#DireDawa #ድሬ

@tikvahethiopia
#DireDawa

" አንዳንዴ አላህን መፍራት ያስፈልጋል። ክርስቲያም ከሆን የምናመልከውን ፈጣሪን መፍራት ያስፈልጋል።

ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።

በአንድ ለሊት የውጭ ምንዛሬው ሲጨምር ባንክም ውድድር ውስጥ ገብቷል።

ግን እዚሁ ስቶር የነበረውና ከ3 ወር በፊትና ከዛ በፊት የገቡ እቃዎች በአንዴ 300 ፐርሰንት መጨመር ሃጢያት አይደል ? አላህ እራሱ ይወደዋል ወይ ?

የሃላል ነገር ነው አይደል ሰው መብላት ያለበት፤ ይሄ ድሃ ማህበረሰብ ነው ሁሌ እናተን በችግር ጊዜ የሚያግዛችሁ።

ቢያንስ ለ3 ወር ! በአዲሱ ምንዛሬ ሲገባ ያኔ እኮ ባላንስ ይደረጋል ፤ ምን ነበር የሚለውን ማየት ይቻላል።

ወደ እርምጃ ሲገባ ግን የከፋ ይሆናል።

እውነቱን ለመነጋገር ከእናተ የድሃውን ማህበረሰብ እምባውን ማበስ ይሽለናል። በግልጽ ለመነጋገር።

ለሰው ብላችሁ አይደለም፤ ለማንም ብላቹ አይደለም ለህሊናችሁ ብላችሁ ስሩ፤ ዛሬ የዘራችሁትን ነገ ልጆቻችሁ የተሻለ ነገር ያገኛሉ። "

የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር (በቅርቡ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው ውይይት የተናግሩት)

#DireDawaCity

@tikvahethiopia
#DireDawa

የድሬው ወጣት ሙዚቀኛ ፈይሰል ኡስማን ሙሜ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊው ባጋጠመው ህመም ህይወቱ አልፏል።

ወጣት ፈይሰል ኡስማን በድሬዳዋ ከተማ ለገሀሬ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው ተወልዶ ያደገው።

ለ25 ዓመታት በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎችን ሲጫወት ነበር።

ፈይሰል ከ5 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ሙዚቃ በመጫወት ተወዳጅነት አትርፏል፡፡

ባለትዳር እና የ2 ልጆች አባት የሆነድ የድሬው ወጣት ሙዚቀኛ፥ ባጋጠመው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በ38 ዓመቱ ዛሬ በሞት ተለይቷል፡፡

ነፍስ ይማር !

#DireDawa

@tikvahethiopia