አጫጭር መረጃዎች ፦

#Amhara, #Gashena

ጋሸና ከተማ ተቋርጦባት የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማግኛቷን ተገልጿል። በአካባቢው ያሉ ሌሎች ከተሞችን የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና እየተካሄደ ሲሆን በነገው እለት ፋላቂት፣ ገረገራ፣ ኮን እና በአካባቢው ያሉ ከተሞች የተቋረጠባቸውን ኃይል መልሰው ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#Afar

በአፋር በክልል በህወሓት ወረራ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀመር የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል በህልውና ዘመቻው ምክንያት ለአንድ ወር በላይ በከፊል ተዘግተው የቆዩት የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች (ከጥቂቶቹ በስተቀር) ዛሬ መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል።

#AddisAbaba

በአ/አ ህገ ወጥ መሬት ወረራ በተሳተፉ 88 አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ፓለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአ/አ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ከ26 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸውና በህገ ወጥ የመሬት ወረራ የተያዙ 671 ይዞታዎች ካርታቸው እንዲመክን ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ መመለሳቸው ሪፖርት ተደርጓል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ኤርፖርት የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑ የድሬዳዋ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አሳውቋል። ትላንት ከቀኑ 10:50 ላይ የአውሮፕላኑን አቅጣጫና የርቀት መለኪያ፣ የኃይል መቆጣጠሪያና የመገናኛ መሳሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መጨመር (high voltage) ምክንያት በተከሰተ ቃጠሎና ፍንዳታ የኃይል መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ላይ አደጋ ደርሷል። በኃላ ችግሩን በማስተካከል ዛሬ ጥዋት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ የአውሮፕላን በረራ እንዲካሄድ ተደርጓል።

@tikvahethiopia