TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ።

• 10 ሰዎች ተገድለዋል።
• የሟቾች አስክሬን ዛሬ አርብ ለቤተሰቦቻቸው ይሰጣል።

ከቀናት በፊት በደቡብ 'አማሮ ልዩ ወረዳ' አካባቢ ታጣቂዎች የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ህይወት በግፍ ማጥፋታቸውን ከሰማን በኃላ ዛሬ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በመንገድ ግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ሰምተናል።

ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ነው።

ጥቃት ተፈፅም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ ያረጋገጡ ሲሆን ጥቃቱ በዞኑ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ "ሎያ ጎዳኔ" ቀበሌ ውስጥ ረቡዕ ሰኔ 09/2013 ዓ.ም አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ መፈፁም ገልፀዋል።

በታጣቂዎች የተገደሉት የፌደራል እና የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ባለሙያ የሆኑ 9 ሰዎች እና የቀበሌው ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ናቸው ብለዋል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት መኪና ውስጥ ከነበሩ 11 የመንገድ ሥራ ባለሙያዎች በሕይወት የተረፉ መኖራቸውንም አክለዋል።

በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች አስከሬን አዲስ አበባ ወደሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ጠቅሰው አስከሬናቸው ዛሬ አርብ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አቶ ዲሪርሳ ፥ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አስራ አንድ የመንገድ ግንባታ ባለሙያዎች መካከል ከግድያው ያመለጡት ሁለቱ "በአካላቸው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤ ደህና ናቸው" ብለዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ጥቃቱን የፈጸመው "ኦነግ-ሸኔ" የተባለው ቡድን እንደሆነ ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-06-18

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ እያጓጓዘ ነው ?

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የአፍሪካ ግዙፉ እና ግንባር ቀደሙ አየር መንገድ ወትግራይ እንዲሁም ወደሌሎች ቦታዎች መሳሪያ እያዘዋወረ ነው በሚል ስሙ ተነስቷል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) ይፋዊ የፌስቡክ ገፅም አየር መንገዱ ወደ መቐለ፣ ሃዋሳ፣ ኮምቦልቻ የጦር መሳሪያ እያዘዋወረ ነው ሲል በይፋ ፅፏል፤አየር መንገዱን ሎጅስቲክስ በማመላለስ የጦርነት ተሳታፊ እየሆነ ነው ሲል ከሷል።

ትላንት ምሽት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ ምላሽ ሰጥቷል።

ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ እያጓጓዘ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን አስረድቷል።

በየትኛውም የሀገር ውስጥ ሆነ የውጪ በረራዎቹ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዳላጓጓዘ ገልጿል።

አየር መንገድ፥ "ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወደ የትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል አላጓጓዝኩም፤ እንዳጓጉዝም አልተጠየኩም" ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አንጋፋና ፓን አፍሪካዊ አየር መንገድ መሆኑን ፣ ለአፍሪካውያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በግንባር ቀደምነት ላለፉት 75 ዓመታት አህጉሩን ሲያገለግል መቆየቱን በዚህም አየር መንገዱ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በተቀረው ዓለምም እጅግ የሚያኮራ ስም ማፍራቱን አንስቷል።

በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በሰራው ስራም ከተለያዩ ሀገራት እና መሪዎች እውቅና ለማግኘት መብቃቱን አስታውሷል።

ነገር ግን "አንዳንድ ሀላፊነት የማይሰማቸው ግለስቦች" ሀሰተኛ እና በፎቶ ሾፕ የተቀናበሩ ምስሎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በማሰራጨት የአየር መንገዱን ስም እና ዝና ለማጠልሸት የሚያደርጉት ጥረት መኖሩን ደምበኞቹ እንዲገነዘቡ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ ሰኞ ለሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ትላንት አዲስ አበባ መግባታቸውን የአፍሪካ ህብረት (AU) በይፋዊ የትዊተር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
"... በወገኖቻቸው ስቃይ የሚነግዱ አካላትን ታሪክ ይፋረዳቸዋል" - ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከዳንጉርና ማንዱራ ወረዳዎች ተፈናቅለው " ቻግኒ መጠለያ " ጣቢያ የነበሩ ዜጎችን ወደቄያቸው የመመለስ ስራ መጀመሩ ተገለፀ።

ተፈናቃዮቹ ሲመለሱ የሚጠቀሙባቸው መሰረታዊ ፍላጎቶችና መሰረተ ልማቶች ቀደም ሲል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

የም/ዕዝ ምክትል አዛዥና የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አባል ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ፥ "የእነዚህን ወገኖች ደህንነት ለመጠበቅ ሠራዊቱ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል" ብለዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ተፈናቅለው የነበሩት ወገኖች ወደቀዬአቸው ተመልሰው ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ የማይፈልጉ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን "በወገኖቻቸው ስቃይ የሚነግዱ አካላትን ታሪክ ያፈረዳቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት ለደህንነታቸው ሙሉ ጥበቃ እንደሚያደርጉላቸው አረጋግጠዋል።

መረጃው የኢዜአ ነው።

@tikvahethiopia
* 2 የችሎት ጉዳዮች !

#አዲስ_አበባ

የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠ/ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራን በመግደል በፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በሞት እንዲቀጣ ጠይቋል።

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዛሬ አርብ ጥያቄውን ያቀረበው የአስር አለቃ መሳፍንትን የክስ ሂደት ለሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። 

ዐቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ባለ 3 ገጽ የቅጣት አስተያየት፤ በተከሳሹ ላይ ሶስት የቅጣት ማክበጃዎችን ጠቅሷል።

የተከሳሽ ጠበቆች ፥ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የለበትም ብለዋል። ዐቃቤ ህግ “አንድም [የወንጀል] ሪከርድ ሳያቀርብ የሞት ፍርድ መጠየቁ ከህጉ ያፈነገጠ ነው” ሲሉ የአቃቤ ህግን የቅጣት አስተያየት ተቃውመዋል። 

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሰኔ 21 /2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/Ethiopia-Insider-06-18

#ባህርዳር

ዛሬ አርብ ማለዳ የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የዋለው ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉ 55 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በሻምበል መማር ጌትነት የክስ መዝገብ ስማቸው የተዘረዘሩ 55 ተከሳሾች ውስጥ 6ቱ በሌሉበት፣ 49 በተገኙበት ፍርዳቸው ሲታይ የነበረ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤቱ 20ዎቹን በነጸ አሰናብቷል።

በነጻ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው ተከሳሾች መካከል አቶ ዘመነ ካሴ ይገኙበታል።

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/BBC-06-18-2

መረጃዎቹ ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር እና ከቢቢሲ የተውጣቱ ናቸው።

@tikvahethiopi
#Israel #Palestine

እስራኤል ለፍልሥጤም በቅርቡ ጊዜው የሚያበቃ አንድ ሚሊዮን ዶዝ ፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት ልትሰጥ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው ስምምነት እስራኤል 1 ሚሊዮን የኮቪድ - 19 ክትባት ለፍልስጤም ትልካለች። ፍልስጤም በተመድ በሚደገፈው ፕሮግራም ክትባት ለሚያስፈልጋቸው ሀገራት ክትባት ሲላክላት አንድ ሚሊዮን ዶዝ ክትባቱን ለእስራኤል ትመልሳለች ተብሏል።

እስራኤል 85% ጎልማሳ ዜጎቿን የኮቪድ-19 ክትባት የከተበች ሲሆን በዌስት ባንክ እና ጋዛ ለሚገኙ 4.5 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ክትባት አላካፈለችም በሚል ስትተች ነበር።

ዛሬ ይፋ የሆነው ክትባት የመላክ ስምምነት በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤንት በሚመራው መንግስት የተደረሰ እንደሆነ ተገልጿል ፤ እስካሁን ግን ከፍልስጤም ባለስልጣናት ምንም የተባለ ነገር የለም።

በዓለማችን ካሉ ሀገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ስራ የሰራችው እስራኤል ዜጎቿን በመከተቡ ረገድም አመርቂ ስራን ሰርታለች ፤ በዚህ ሳምንት የሀገሪቱ ባለስልጣናት ቀሪ ነበር የተባለውን የመጨረሻ ገደብ በህዝብ መካከል ማስክ የማድረግ ገደብ እንዳነሱ ታውቋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያን ያስቆጣው የሀርቪስቶ አስተያየት :

ከ3 ቀን በፊት የፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ለአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ነበር።

በዚህ ሪፖርታቸው ላይ ስለ #ትግራይ ጉዳይ የተናገሩ ሲሆን በይበልጥ ግን የብዙሃን መነገሪያ የሆነው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በነበረኝ ቆይታ፥ "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት #የትግራይ_ተወላጆችን_ለማጥፋት እንደሚፈልጉ /ታጋሩዎችን ለ100 ዓመታት ማጥፋት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል" ብለው የተናገሩት ነው።

የትኛው የኢትዮጵያ ባለስልጣን ይህን እንዳለ / ሲናገር እንደሰሙት ግን በስም ገልፀው ሲናገሩ አልታዩም።

ሀርቪስቶ የአውሮፓ ህብረትን በመወከል ለጥቂት ቀን በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገው እንደነበር አይረሳም።

ፔካ ሀርቪስቶ ከቀናት በፊት ያቀረቡት አጠቃላይ ሪፖርት ኢትዮጵያን ክፉኛ አስቆጥቷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሀርቪስቶ ያቀረቡት ሪፖርት ኃላፊነት የጎደለው፣ መሰረት የሌለው፣ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ያልተከተለና ከቅኝ ገዢነት የመነጨ ነው ብሎታል።

ሚኒስቴሩ “ፔካ ሃቪስቶ መንግስት እያከናወነ ያለውን ስራ የሚያጣጥል እና በሐሰተኛ መረጃዎች የተመሰረቱ ሪፖርቶችን፣ ውሸቶችን በማቅረብ ተገቢ ያልሆኑ ጣልቃ ገብነቶች እንዲኖሩ አድርጓል” ብሏል።

በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ ፔካ ሃቪስቶ ከጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ፣ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ከም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አውስቶ፤ የቀረበው ሪፖርት ግን ሃሰተኛና የተካሄዱ ሰፋፊ ውይይቶችን ያላካተተ መሆኑን ተገልጿል።

* የፔካ ሀርቪስቶ ሪፖርት ፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

(ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ/ም)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ ዕለታዊ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላትም በቦታው ተገኝተዋል።

ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ላለፉት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን ፖሊሳዊ የደንብ ልብስ እና ዓርማ መቀየሩን ምክንያት በማድረግ የማብሰሪያ መርሀ-ግብር ማዘጋጀቱን ዛሬ አስታውቋል።

ይህ መርሀግብር ነገ ቅዳሜ ሰኔ 12/2013 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ነው ይካሄዳል የተባለው።

በዚህ ምክንያት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የተወሰኑ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።

በዚህም መሰረት ፦

• ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከ4ኛ ክፍለ ጦር/ጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሀራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከብሄራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ እና በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ መጋቢ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

መረጃውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#UnitedNations

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በይፋዊ የትዊተር ገፁ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለሁለተኛ ጊዜ የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ በመሆን ዳግም እንደተመረጡ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶችን ቦርዱ ከማዕከል ማንቀሳቀስ መጀመሩን አስታወቀ። ዛሬ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ዕለታዊ መግለጫ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋና ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ዛሬ ቦርዱ በገለጸው መሰረት ፦ - ለኦሮሚያ ክልል 118 (ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ) የምርጫ ክልሎች፤ የምርጫ ቁሳቁሶች ከማዕከል ተልከዋል። - ለአማራ…
#UPDATE #ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እየሰጠ በሚገኘው ዕለታዊ መግለጫ ላይ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋ እና ከማዕከል ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ መከናወኑን ገልጿል።

ቦርዱ ይህን የሎጀስቲክ ሥራ ለማከናወን ከየብስ ትራንስፖርት በተጨማሪ የአየር ትራንስፖርትን መጠቀሙን የገለጸ ሲሆን በዚህም አስቸጋሪ በሚባሉ ቦታዎች ጭምር የምርጫ ቁሳቁስ ማድረስ መቻሉን ነው የገለጸው።

ቀሪ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት የሚካሄድባቸው በደቡብ ክልል 4 የምርጫ ክልሎች እንዲሁም በአፋር ክልል አንድ የምርጫ ክልል የአየር ትራንስፖርት በመጠቀም የሚከናወን ይሆናል።

በአጠቃላይ የምርጫ ቁሳቁስ እሸጋና ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልል የማድረስ ሥራዎች ከተወሰኑ የቅንጅትና ጥቂት የመዘግየት ችግሮች በስተቀር ከፍተኛ የሆነ ችግር ሳያጋጥም መጠናቀቁን የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ቦርዱ በዋናነት የድምጽ መስጫ ወረቀቶችንና ውጤት ማሳወቂያ ፎርሞችን ወደ ምርጫ ክልል በማድረሱ ሥራ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው አንስቶ አመስግኗል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የምርጫ ዝግጅት በወላይታ ዞን :

• 13 የምርጫ ክልሎች አሉ።
• ሰኞ በ7 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ይደረጋል።
• ሰኞ በ6 የምርጫ ክልሎች ምርጫ #አይደረግም

በወላይታ ዞን በ13 የምርጫ ክልሎች 1 ሺህ 20 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፥ 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ካሉት 13 የምርጫ ክልሎች በሰባት የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን በ5 ምርጫ ክልሎች ላይ ደግሞ ምርጫ እንደማይካሄድ የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አሳውቋል።

ምርጫውን ማካሄድ የሚያስችል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ምርጫ ወደሚካሄድባቸው 7 ወረዳዎች እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን ወረዳዎችም ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የመጡ ቁሳቁሶቹን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

በምርጫው ከ1 ሚሊየን በላይ ህዝብ መመዝገብ አለበት ተብሎ ታቅዶ ከ 800 ሺህ በላይ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቧል።

ሰኞ ምርጫ በሚካሄድባቸው በ7 ምርጫ ክልሎች ከ600 ሺህ በላይ ህዝብ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል ፤ ቀሪው መራጭ ህብረተሰብ በ2ኛው ዙር ድምፁን ይሰጣል ተብሏል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
የዓለም ጤና ድርጅት ለወ/ሪት ሄራን ገርባ ሽልማት አበረከተ።

በዓለም ጤና ድርጅት የ2013 ትምባሆ የማይጨስበት ቀን ጉልህ አስታዋጽፆ ላበረከቱት ለወ/ሪት ሄራን ገርባ ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡

የ2013 የዓለም ጤና ድርጅት ለዓመቱ ያዘጋጀውን የዓለም የማይጨስበት ቀን ሽልማት ከአፍሪካ አህጉር ተሸላሚ ከሆኑት ስድስት ግለሰቦች መካከል አንዷ ወ/ሪት ሄራን ገርባ ነበሩ።

ወ/ሪት ሄራን ፥ ላበረከቱት አስተዋጾ የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ተጠሪ ዶ/ር ቡሬማ ሳምቦ ዛሬ ሰኔ11/2013 ዓ.ም. ሽልማቱን አበርክተውላቸዋል።

#EFDA

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ከ21 ቀን በኃላ ከፍተኛ የኮቪድ-19 ሟቾችን ሪፖርት አደረገች።

ባለፉት 21 ቀናት ሪፖርት ከተደረጉት ሁሉ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ባለፉት 24 ሰዓታት ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት የ14 ዜጎች ህይወት በቫይረሱ አልፏል ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,276 ደርሷል።

@tikvahethiopia