TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶችን ቦርዱ ከማዕከል ማንቀሳቀስ መጀመሩን አስታወቀ። ዛሬ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ዕለታዊ መግለጫ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋና ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ዛሬ ቦርዱ በገለጸው መሰረት ፦ - ለኦሮሚያ ክልል 118 (ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ) የምርጫ ክልሎች፤ የምርጫ ቁሳቁሶች ከማዕከል ተልከዋል። - ለአማራ…
#UPDATE #ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እየሰጠ በሚገኘው ዕለታዊ መግለጫ ላይ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋ እና ከማዕከል ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ መከናወኑን ገልጿል።

ቦርዱ ይህን የሎጀስቲክ ሥራ ለማከናወን ከየብስ ትራንስፖርት በተጨማሪ የአየር ትራንስፖርትን መጠቀሙን የገለጸ ሲሆን በዚህም አስቸጋሪ በሚባሉ ቦታዎች ጭምር የምርጫ ቁሳቁስ ማድረስ መቻሉን ነው የገለጸው።

ቀሪ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት የሚካሄድባቸው በደቡብ ክልል 4 የምርጫ ክልሎች እንዲሁም በአፋር ክልል አንድ የምርጫ ክልል የአየር ትራንስፖርት በመጠቀም የሚከናወን ይሆናል።

በአጠቃላይ የምርጫ ቁሳቁስ እሸጋና ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልል የማድረስ ሥራዎች ከተወሰኑ የቅንጅትና ጥቂት የመዘግየት ችግሮች በስተቀር ከፍተኛ የሆነ ችግር ሳያጋጥም መጠናቀቁን የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ቦርዱ በዋናነት የድምጽ መስጫ ወረቀቶችንና ውጤት ማሳወቂያ ፎርሞችን ወደ ምርጫ ክልል በማድረሱ ሥራ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው አንስቶ አመስግኗል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia