#Israel #Palestine

እስራኤል ለፍልሥጤም በቅርቡ ጊዜው የሚያበቃ አንድ ሚሊዮን ዶዝ ፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት ልትሰጥ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው ስምምነት እስራኤል 1 ሚሊዮን የኮቪድ - 19 ክትባት ለፍልስጤም ትልካለች። ፍልስጤም በተመድ በሚደገፈው ፕሮግራም ክትባት ለሚያስፈልጋቸው ሀገራት ክትባት ሲላክላት አንድ ሚሊዮን ዶዝ ክትባቱን ለእስራኤል ትመልሳለች ተብሏል።

እስራኤል 85% ጎልማሳ ዜጎቿን የኮቪድ-19 ክትባት የከተበች ሲሆን በዌስት ባንክ እና ጋዛ ለሚገኙ 4.5 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ክትባት አላካፈለችም በሚል ስትተች ነበር።

ዛሬ ይፋ የሆነው ክትባት የመላክ ስምምነት በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤንት በሚመራው መንግስት የተደረሰ እንደሆነ ተገልጿል ፤ እስካሁን ግን ከፍልስጤም ባለስልጣናት ምንም የተባለ ነገር የለም።

በዓለማችን ካሉ ሀገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ስራ የሰራችው እስራኤል ዜጎቿን በመከተቡ ረገድም አመርቂ ስራን ሰርታለች ፤ በዚህ ሳምንት የሀገሪቱ ባለስልጣናት ቀሪ ነበር የተባለውን የመጨረሻ ገደብ በህዝብ መካከል ማስክ የማድረግ ገደብ እንዳነሱ ታውቋል።

@tikvahethiopia