የታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ።

• 10 ሰዎች ተገድለዋል።
• የሟቾች አስክሬን ዛሬ አርብ ለቤተሰቦቻቸው ይሰጣል።

ከቀናት በፊት በደቡብ 'አማሮ ልዩ ወረዳ' አካባቢ ታጣቂዎች የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ህይወት በግፍ ማጥፋታቸውን ከሰማን በኃላ ዛሬ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በመንገድ ግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ሰምተናል።

ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ነው።

ጥቃት ተፈፅም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ ያረጋገጡ ሲሆን ጥቃቱ በዞኑ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ "ሎያ ጎዳኔ" ቀበሌ ውስጥ ረቡዕ ሰኔ 09/2013 ዓ.ም አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ መፈፁም ገልፀዋል።

በታጣቂዎች የተገደሉት የፌደራል እና የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ባለሙያ የሆኑ 9 ሰዎች እና የቀበሌው ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ናቸው ብለዋል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት መኪና ውስጥ ከነበሩ 11 የመንገድ ሥራ ባለሙያዎች በሕይወት የተረፉ መኖራቸውንም አክለዋል።

በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች አስከሬን አዲስ አበባ ወደሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ጠቅሰው አስከሬናቸው ዛሬ አርብ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አቶ ዲሪርሳ ፥ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አስራ አንድ የመንገድ ግንባታ ባለሙያዎች መካከል ከግድያው ያመለጡት ሁለቱ "በአካላቸው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤ ደህና ናቸው" ብለዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ጥቃቱን የፈጸመው "ኦነግ-ሸኔ" የተባለው ቡድን እንደሆነ ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-06-18

@tikvahethiopia