TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ አ/አ መርካቶ "ሚሊቴሪ ተራ" አካባቢ በደረሰ የእሣት አደጋ ንብረት ወደመ።

የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዳሳወቀው ሚሊቴሪ ተራ አካባቢ በደረሰው የእሣት አደጋ ከ50,000 ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል።

በእሣት አደጋው ምክንያት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

አደጋው በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰ ሲሆን ቃጠሎ መንስኤ የኤሌክትሪክ ኮንታክት መሆኑ ተገልጿል።

በተደረገው ርብርብ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ማትረፍ ተችሏል።

እሳቱን ለመቆጣጠር 39 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መሳተፋቸውንና 30 ሺህ ሊትር ውሃ ጥቅም ላይ መዋሉን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢዜአ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በካፋ ዞን የውሽውሽ ሻይ ልማት የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል፣ የክልል እንዲሁም የዞን የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ና ሌሎች እንግዶች ወደ ሚዛን በሚሄዱበት ጊዜ የዞኑ ህዝብ ደማቅ አሸኛኘት እንዳደረገላቸው የካፋ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አሳውቆናል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

በመቐለ 400 ኩንታል የእርዳታ እህል ወደ ግለሰብ መጋዘን ሲራገፍ ተያዘ።

የእርዳታ እህሉ መነሻውን ከጅቡቲ አድርጎ በቀጥታ መቐለ አዋሽ ተብሎ ከሚጠራው መጋዘን መራገፍ ሲኖርበት በ2 ግለሰብ መጋዘኖች ሲራገፍ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዟል፡፡

ከእርዳታ እህሉ ጋር የተሽከርካሪው ሹፌርና ረዳቱን ጨምሮ የመጋዘኑ ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል።

በመቐለ ሰሜን ክፍለ ከተማ ላጨ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሁለት መጋዘኖች ሲራገፍ የተያዘው የእርዳታ እህል ትናንት ማምሻውን የገባ ነው፡፡

በትግራይ ክልል ከሳምንት በፊት በወጣ አንድ ሪፖርት ባለፉት ጥቂት ወራት ከ4 ሺ 400 በላይ የእርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia - የፀጥት ችግር እና ግጭት - አንበጣ መንጋ ጉዳት - የኮሮና ቫይረስ ተፅእኖ - የትግራይ ክልል ችግር ተደማምረው ኢትዮጵያ ውስጥ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ ታዳጊዎች እና ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች እንዳደረጋቸው ተገለፀ። ይህን የገለፁት UNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ እና የስውዲን ኤምባሲ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። መግለጫው ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው…
ቁጥራዊ መረጃ #ኢትዮጵያ

ከUNICEF እና ከስውዲን ኤምባሲ መግለጫ :

- 23.5 ሚሊዮን በተያዘው ዩፈረንጆች ዓመት #ሰብዓዊ_እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር (በረብሻ እና ግጭት፣ አንበጣ መንጋ፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የትግራይ ጦርነት ተዳምሮ)

- ከ23.5 ሚሊዮን መካከል 12.5 ታዳጊዎች እና ህፃናት እርዳታ ፈላጊ ናቸው።

- ከ700 ሺህ በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ።

- 6 ሺህ ህፃናት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ (እስካሁን ባለው ብቻ)

- 192.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እስከ አመቱ መጨረሻ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን ችግር ለመደገፍ UNICEF የሚያስፈልገው ተጨማሪ ገንዘብ።

- 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፥ ከእአአ 2011 አንስቶ ስውዲን በUNICEF በኩል በኢትዮጵያ ለሚሰራው ስራ ያደረገችው ድጋፍ።

- 350 ሺህ ትግራይ ውስጥ ለረሃብ ፣ የከፋ ችግር ተጋልጠዋል የተባሉ ሰዎች ቁጥር።

@tikvahethiopia
"... ታላቁ የግብፅ ኢማም የታላቁ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት የሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን ሀቅ ያልተመለከተ እና እውነት የጐደለው ነው"- ቀዳማዊ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ

የግብፁ አለማቀፋዊ እስልምና ተቋም ታላቅ ኢማም የሆኑት ሼክ አልሃዛር - አህመድ ጦይብ የህዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያ ወንዙን በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎች ሀገራት ላይ ጉዳት ለማድረስ እየሰራች መሆኑን መናገራቸው ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ተናገሩ።

ከሰሞኑን አልአዝሀር ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ ትክክል አይደለም፤ ወንዙ የሁላችንም በመሆኑ ሁሉም ሰው ሊቃወመው ይገባል ፤ ግድቡ ግብጽ እና ሱዳን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ አረቦች እና ሙስሊሞች ሁሉ እንዲቃወሙት ሲል ጥሪ አቅርቦ ነበር።

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት መግለጫውን "የኢትዮጵያን ሀቅ ያልተመለከተ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

ኢትዮጵያ ሁሌም ቢሆን ውሃውን በፍትሃዊነት እንጠቀም የሚል አቋምን ስትገልፅ ከርማለች ያሉት የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዚዳንት፣ ግብፅ እና ሱዳንም ይሄንን እውነት ይዘው ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዚዳንት ፥ የአባይ ውሃ ምንጩም ሆነ ተፈሳሱም አፍሪካ ምድር በመሆኑም መፍትሄውም እዚሁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አል ዓይን ነው።

@tikvagethiopia
#ምርጫ2013

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ ዕለታዊ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላትም በቦታው ተገኝተዋል።

ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል።

www.tikvahethiopia.net

@tikvahethiopia
#EMA

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሚዲያዎች የሰጡት ቃለምልልስ ከምርጫ በፊት እንዳይሰራጭ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።

ቃለምልልሱ በዚህ በጥሞና ወቅት መተላለፍ የለበትም ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ ጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም ብለዋል።

የቃለ መጠይቁ መተላለፍ ብዥታ እንዳይፈጥር ሲባል ከምርጫው በፊት መተላለፍ እንደሌለበት አቶ መሀመድ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ቃለ መጠይቁ እንዳይተላለፍ የተፈለገው መንግስት በዚህ ዓመት የተሻለ ምርጫ እንዲካሄድና ፍትሀዊ እንዲሆን ፍላጎት ስላለው መሆኑን ተናግረዋል።

ስለዚህ ቃለ መጠይቁን ለማስተላለፍ ማስታወቂያ እየሰሩ ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ለማስተላለፍ የተዘጋጁ ከወዲሁ #እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል።

መገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በመጠናቀቁ ቅስቀሳ መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ ሊጠነቀቁ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ ዕለታዊ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላትም በቦታው ተገኝተዋል። ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል። www.tikvahethiopia.net @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መጪውን ምርጫ እንዳይታዘብ ተከልክሏል ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር የተጻጻፉትን ደብዳቤ መሰረት ተደረጎ ''የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መጪውን ምርጫ እንዳይታዘብ መከልከሉን'' የሚጠቅሱ ዘገባዎች ወጥተዋል።

ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ''ሁለቱም በመንግስት ገለልተኛ ተቋም ናቸው ተብለው የተቋቋሙ ናቸው እኛ ባጅ የምንሰጣቸው የምንቆጣጠራቸውን ነው'' ሲሉ ገልጸዋል።

በምርጫ ጣቢያዎች እንዲገቡ በቦርዱ የ "ይለፍ ካርድ" እንደሚሰጣቸው በአዋጅ 1162/2011 መጠቀሳቸውን ያነሱት ወ/ሪት ሶሊያና ኮሚሽኑ ከእነዚህ መካከል ባለመሆኑ በምርጫ ጣቢያዎች እንዲገቡ በቦርዱ የይለፍ ካርድ መስጠት እንደማይችል አንስተዋል።

ባጅ ከመስጠትና የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ እንዲገቡ ፈቃድ የሚሰጣቸው በአዋጁ የተጠቀሱ እንዲሁም ቦርዱ ፈቃድ ሊሰጣቸው አስፈላጊ ሲሆንም ይህንን ፈቃዳቸውን ሊሰርዝ የሚችልባቸውን እንጂ ከቦርዱ ጋር ትይዩ ሥልጣን ላላቸው የመንግስት ተቋማት አይደለም ብለዋል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶችን ቦርዱ ከማዕከል ማንቀሳቀስ መጀመሩን አስታወቀ።

ዛሬ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ዕለታዊ መግለጫ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋና ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ዛሬ ቦርዱ በገለጸው መሰረት ፦

- ለኦሮሚያ ክልል 118 (ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ) የምርጫ ክልሎች፤ የምርጫ ቁሳቁሶች ከማዕከል ተልከዋል።

- ለአማራ ክልል በሬሾ 1/3 በሚሆን መልኩ፤

- ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር 47 የምርጫ ክልሎች፤

- ለአፋር ክልል 25 የምርጫ ክልሎች፤

- ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 7 የምርጫ ክልሎች፤

- ለጋምቤላ ክልል 14 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁሶች ለምርጫ ክልሎች ተልከዋል።

ለቀሪ ክልሎች በቀጣይ ቀናት የእሸጋና የስርጭት ሥራዎች የሚሰራ ሲሆን ከምርጫ ክልል ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የሚደረጉ ሥርጭቶች የክልል መንግሥታት እና የከተማ አስተዳድሮች አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ በጹሑፍ ጭምር እንደገለፁ ተጠቅሷል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 5,764
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 174
• ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ከበሽታው ያገገሙ 744

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 274,775 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,262 ህይወታቸው ሲያልፍ 253,195 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,964,005 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ጉዳይ ፦

ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ እና በችግር ላይ ያሉ ዜጎቿን በተለያየ ጊዜ ስትመልስ መቆየቷ ይታወቃል።

ነገር ግን አሁንም በርካታ ዜጎች በሳዑዲ እርስ ቤቶች ውስጥ ታጉረው እንደሚገኙ፣ በርካቶችም በችግር ውስጥ ሆነው ወደሀገራችን መልሱን እያሉ ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች የተለያዩ የመገናኛ ዜዴዎች በመጠቅም ስላሉበት የከፋ ሁኔታ እየገለፁ ነው።

ከሰሞኑን ደግሞ የሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ ኃይል የሚሰራው ስራ በርካታ ዜጎቻችን የሰቀቅን ኑሮን እንዲገፉ ፣ በርካቶችንም ለስቃይ ፣ ለዘረፋ ፣ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው ሰምተናል።

አሁን አመሻሹን በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባሰራጨው መልዕክት ፥ በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ጉዳይ መንግስትን ሲያሳስብ የነበረና መንግስት የዜጎች ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ ሲመክር መቆየቱን ገልጿል።

ኤምባሲው የዜጎች ጥያቄ እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ አረቢያ መንግስት እና የኢፌዲሪ መንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር ጉዳዪ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷል።

በዚህም መሰረት ፦
(1)--በእስር ቤት ያሉ እና
(2)--የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ወደ አገር መመለስ ፈልገው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ ዜጎቻችን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ አገር የመመለስ ስራ ይጀመራል ብሏል።

በሳዑዲያ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንም ኤምባሲው ቃሉን አክብሮ ወደእናት ሀገራቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጋቸው ባገኙት መገናኛ ዘዴ ጥሪ እያቀረቡ ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013 #በምርጫብቻ

ውድ የቲክቫህ አባላት የፊታችን ሰኞ ከሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች፣ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ይኖር ይሆን ?

የምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በቀጥታ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ።

ወ/ሪት ሶሊያና ምላሽ የሚሰጡት #በቀጥታ በ Voice Chat ላይ ነው።

ጥያቄዎቻችሁን ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡ ፤ አንድ አባል ለሚያቀርበው ጥያቄ ሌላ አባል #Reply መስጠት የማችል ሲሆን Reply የሚሰጣጡ አባላትን ከአስተያየት መስጫው ተሳትፏቸውን የምንገድበው ይሆናል።

(ይህ ጥያቄ መቀበያ ነገ ጥዋት 3:00 ይዘጋል)

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 #በምርጫብቻ ውድ የቲክቫህ አባላት የፊታችን ሰኞ ከሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች፣ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ይኖር ይሆን ? የምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በቀጥታ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ። ወ/ሪት ሶሊያና ምላሽ የሚሰጡት #በቀጥታ በ Voice Chat ላይ ነው። ጥያቄዎቻችሁን ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡ…
#ምርጫ2013 #በምርጫብቻ

ውድ የቲክቫህ አባላት ከትላንት ለሊት 6 ሰዓት አንስቶ በምርጫ ዙሪያ ግልፅ ያልሆነላችሁ፣ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ካለ በሚል ጥያቄዎችን ሰብስበባል።

እጅግ በርካታ ጥያቄዎች ከተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ ከሚገኙ አባላቶቻችን ተሰብስቧል።

ተመሳስይነት ያላቸውን ጥያቄዎች አንድ ላይ በማድረግ እና የኢትጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚመለከተውን ብቻ ለኮሚኒኬሽን ኃላፊዋ ወ/ሪት ሶሊያና አቅርበን ምላሽ እንዲሁም ማብራሪያ እንዲሰጥበት፤ እናተም ጋር ብዥታ ካለ የሚጠራበት መንገድን እናመቻቻለን።

መቼ ነው ምላሽ የሚሰጠው ? ቀኑን ሰዓቱን እናሳውቃለን።

ከዚህ ቀደም ምላሽ ያገኙ ጥያቄዎችን ደግሞ ከ #ምርጫው ጋር የተያያዙ የተለዋወጥናቸውን መረጃዎችን መለስ ብላችሁ እንድትመለከቱት በትህትና እንጠይቃለን። ጠቃሚ የሚባሉ ወሳኝ መልዕክቶችን በድጋሚ እንልክላችኃለን።

@tikvahethiopia