TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

ምርጫ ቦርድ ለግል እጩ ተወዳዳሪዎች 50 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከግል እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በተለያየ ግዜ ባደረገው ምክክር መሰረት ቦርዱ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምኖበት ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑን ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫ ቦርድ በግል እጩ ተወዳዳሪነት እውቅና አግኝተው ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ በሙሉ ፦
- ሙሉ ስማቸውን፣
- አድራሻችሁን (ስልክ ቁጥራችሁን፣ ኢሜል)
- የባንክ አካውንታቸውን ለቦርዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስራ ክፍል በአካል ወይም በ politicalparties@nebe.org.et ኢሜል አድራሻ ወይም በስልክ ቁጥሮች +251913551505/ +251929289444 የዋትስ አፕ እና ቴሌግራም እንዲልኩ መልዕክት አስተላልፋል።

@tikvahethioia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#UN

ትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት የኤርትራ ወታደሮች "በቅርቡ" እንደሚወጡ በተባበሩት መንግሥታት (UN) የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ተናገሩ።

አምባሳደሩ "በቅርቡ" ይበሉ እንጂ ትክክለኛውን ቀን አልጠቀሱም።

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ግዛት ለመውጣት የቀራቸው "አንዳንድ ቴክኒካዊና የአፈጻጸም ጉዳዮች ናቸው" ብለዋል።

የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ቁርጠኝነት እንዳለና "በኤርትራውያኑ በኩልም ሁሉ ነገር ግልጽ" ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ይህንን የገለጹት የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በጸጥታው ምክር ቤት ቀርበው "ግጭቱ እንዲቆም ተደርጎ የኤርትራ ወታደሮች ካልወጡ የ1977 አይነቱ የከፋ ረሃብ ተመልሶ ቢከሰት ማንም መደነቅ የለበትም" ብለው ከተናገሩ በኋላ መሆኑን #ቢቢሲ ሮይተርስን እና APን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በተጨማሪ አምባሳደር ታዬ ፦

- የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ሁኔታ መሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት፤
- ስለሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታ፤
- በትግራይ ተፈፅሟል ስለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ እየተደረገ ስላለው ምርመራ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Video Credit : United Nations

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ምርጫ2013

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ : "...መላው ዓለም በምርጫ ቀን ይጋጫሉ ሲለን እኛ ደግሞ እናስተምራቸዋለን”

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በምርጫ ቅስቀሳ የመጨረሻ ቀን በጅማ ከተማ በነበረ ዝግጅት ፥ "መላው ዓለም በምርጫ ቀን ይጋጫሉ ሲለን እኛ ደግሞ እናስተምራቸዋለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ በምርጫው ዕለት መራጮች ድምጽ ከመስጠት ጎን ለጎን ዛፍ በመትከል ለዓለም ትምህርት የሚሆን ተግባር እንዲያከናውኑ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጅማ ዩኒቨርስቲ ስቴድየም በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻችው ተገኝተው ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ በሰኔ 14ቱ ምርጫ ከሚፎካከሩ ኃይሎች መካከል “ኢትዮጵያን የሚወዱ፣ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚፈልጉ፣ የኢትዮጵያ አንድነትን እና ነጻነትን የሚያከብሩ” ላሏቸው ተወዳዳሪዎች መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።

ጠ/ሚር አብይ ዛሬ ባሰሙት ንግግር እምብዛም የምርጫን ጉዳይ አላነሱም።

በተለያዩ ቦታዎች በሚካሄዱ መርሃ ግብሮች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲናገሩ የተደመጡትን “የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነትን” ጉዳይም አልጠቀሱም።

እርሳቸው በንግግራቸው ጉዳዩን ባያነኩትም የጅማውን የስቴድየም መርሃ ግብር ይመሩ የነበሩ መድረክ መሪዎች እና ዘፋኞች ግን አሜሪካንን ጭምር በስም በመጥቀስ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መፈክር ቀመስ መልዕክቶች ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል።

በስቴድየም በተሰበሰበው ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ የተደመሙ የመሰሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ የስቴድየሙን ግማሽ በሩጫ በመዞር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

Video Credit : ጋዜጠኛ ተስፋአለም ወልደየስ

@tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ምዕራብ ህዝበ-ውሳኔ ጳጉሜ 1 እንደሚካሄድ ቦርዱ ዳግም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ-ውሳኔ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ዳግም ገልጿል።

የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ቦርዱ ከዚህ ቀደም ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ አለመኖሩን ነው የገለጹት።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
የተመዘገቡ እጩዎች.pdf
9.4 MB
 #ምርጫ2013

ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምፅ የሚሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ እጩዎች ዝርዝር በየክልሎቹ  እና ከተማ መስተዳድሮቹ ከላይ ተያይዟል።

PDF ፋይሉን ስትከፍቱን ቅደም ተከተሉ በዚህ መልኩ ያለ ነው ፦

- አዲስ አበባ ከተማ : የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና ም/ቤት እጩዎች

- አፋር: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

- አማራ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

- ቤንሻንጉል ጉሙዝ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

- ድሬዳዋ ከተማ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና ም/ቤት እጩዎች

- ጋምቤላ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

- ኦሮሚያ : የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

- ሲዳማ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

- ደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ህዝቦች: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች

(ሁሉንም የተመዘገቡ እጩዎች የያዘው PDF ፋይል 9.4 MB ነው)

@tikvahethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 5,237
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 121
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ 571

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 274,601 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,260 ህይወታቸው ሲያልፍ 252,451 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,962,486 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ማስታወሻ ፦

ከነገ ሀሙስ ጀምሮ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም።

- ሁሙስ
- አርብ
- ቅዳሜ
- እሁድ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም።

ይህ ማለት፦ ፓርቲዎች ማንኛውም አይነት ስብሰባ ማድረግ አይችሉም ፣ ቤት ለቤት እየሄዱ ምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም፣ ወረቀት ፍላየር መበተን አይችሉም፣ የአደባባይና የአዳራሽ ስብሰባ ማድረግ አይችሉም፣ የኢንተርኔት (ኦንላይን) የማህበራዊ ሚዳያ የምረጡኝ ዘመቻ ማድረግ አይችሉም።

#SolianaShimeles #ሰኔ14እመርጣለሁ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በምርጫ ወቅት ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና የሚባሉ ክርክሮች ፦ የመራጮች እና የእጩዎች ምዝገባ ፣ የድምፅ አሰጣጥ ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ የተመለከቱ ናቸው።

እነዚህን ክርክሮች የሚዳኙ ፦

#ተቋማት

- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና በቦርዱ የተቋቋሙ ውሳኔ ሰጪ አካላት
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

#ሕጎች

- የኢፌዴሪ ህገመንግስት
- የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር ፲፩፻፷፪/፳፻፲፩
- የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፩፻፴፫/፳፻፲፩
- አግባባ ያላቸው ሌሎች ሕጎች

#የኢትዮጵያ_የፌዴራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት

@tikvahethiopia
#Ethiopia

- የፀጥት ችግር እና ግጭት
- አንበጣ መንጋ ጉዳት
- የኮሮና ቫይረስ ተፅእኖ
- የትግራይ ክልል ችግር ተደማምረው ኢትዮጵያ ውስጥ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ ታዳጊዎች እና ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች እንዳደረጋቸው ተገለፀ።

ይህን የገለፁት UNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ እና የስውዲን ኤምባሲ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው።

መግለጫው ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ችግር ፣ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ላይ ነው።

በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ችግር እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

የUNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ ተወካይ አደሌ ሆደር የረብሻ እና የፀጥታ ችግር፣ የኮቪድ-19 ተፅእኖ፣ የአንበጣ መንጋ፣ የትግራይ ክልል ችግር ተዳምረው በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ሰብዓዊ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 23.5 ሚሊዮን አድርሶታል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ 12.5 ህፃናት እና ታዳጊዎች መሆናቸው ችግሩን ይበልጥ አክፍቶታል ብለዋል።

ኃላፊዋ ችግሩ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል እንዳለ የገለፁ ሲሆን በተለይ ግን በትግራይ ክልል ያለው ችግር ግን ይበልጥ የከፋ ነው ብለዋል።

አክለውም ፥ "በትግራይ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ 6 ሺህ ህፃናት መረጃ በእጃችን አለ፤ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ ህፃናት ጉዳይ ብዙ አደጋ ያለው ነው ። ለተለያየ ጥቃት ሊዳረጉ ይችላሉ፣ ማንኛውም ነገር ሊደርስባቸው ይችላል፤ ልጆቹ ሊሸጡ፣ ለሌላ ሰው ሊሰጡ ይችላሉ ስለዚህ ለእነዚህ ህፃናት ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Sheger-FM-06-17

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
የኤርትራ ማስተባበያ !

ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ "ተጨባጭ ያልሆኑ ተደጋጋሚ ክሶችን" አቅርበውብኛል ስትል ተቃወመች።

ኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የኤርትራ ወኪል እንዳለው የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በሚወያይበት ጊዜ እንዲገኙ ወይም አስተያየት እንዲሰጡ እንዳልተጋበዙ አመልክቶ "የኤርትራን ገጽታ ለማበላሸት ተገቢ ያልሆነና ግልጽነት የሌለው" ያለውን ዘዴ ተቃውሞታል።

ማክሰኞ በተደረገው የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተመድ የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ ከታሰበው በላይ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረው ነበር።

ማርክ ሎውኮክ ፥ "ሴቶችን እና ታዳጊዎችን በተቀናጀ ሁኔታ በመድፈር ሽብርና ስቃይ እየተፈጸመ ነው። የኤርትራ ወታደሮች ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀሙበት ነው። የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች ይከበባሉ፣ ይደበደባሉ እንዲሁም ማስፈራሪያዎች ይደርሳቸዋል"

ይህንን ተከትሎ ኤርትራ የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን ለምክር ቤቱ የኤርትራ ወታደሮች ይፈጽሙታል ያሉትን ድርጊት አስተባብላለች።

በተመድ የኤርትራ ወኪል ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ፥ "ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ ፈጽሞ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደረስ እገዳ አላደረገችም ብሏል። በተጨማሪ ኤርታራ "ምግብን እንደ ጦር መሳሪያ" ፈጽሞ አልተጠቀመችም፤ እንኳን አሁንና ከኢትዮጵያ ጋር የነጻነት ትግል በሚደረግበትና በድንበር ጦርነቱ ጊዜ እንኳን እንዲህ አይነት ነገር አልተፈጸመም" ሲል አክሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#MizanAman

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና ከተማ ሚዛን አማን ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ይህ የሚዛን አማን የአውሮፕላን ማረፊያ ጉዳይ የረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ መሆኑ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ "ኢትዮጵያን እናልብሳት" የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን እንዳስጀመሩ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል ተባሉ የመብት ጥሰቶችን በይፋ መመርመር እንደሚጀምር ገልጿል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን ምርመራ ፥ የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሥራውን በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው።

በዚህም መሰረት በትግራይ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ አስፈላጊ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላም የጎረቤት ሀገራትን ሁኔታ ለማየት ይሞክራል።

ኮሚሽኑ ለ3 ወራት ሁኔታውን እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ የ3 ወራት ጊዜውም ሊታደስ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት እንዳለው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ግን የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተናጠል ምርመራ አደርጋለሁ ማለቱን ተቃውሟል።

መንግስት ተቃውሞውን የገለፀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተሰጠው መግለጫ ነው።

ሚኒስቴሩ ፥ ኮሚሽኑ ብቻውን በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን እመረምራለሁ ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡

ነገር ግን ኮሚሽኑ ምርመራውን ማድረግ ከፈለገ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ማካሄድ ይችላል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት፤ የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ብቻዬን አካሂዳለሁ ያለውን የምርመራ ሂደት በአስቸኳይ #እንዲያቋርጥ ጠይቋል፡፡

#አል_ዓይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ።

እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ዛሬ ለነበራቸው ቀጠሮ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ጉዳያቸውን ለመከታተል ችሎት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

ጉዳያቸውን የሚመለከተው ፍርድ ቤት እንዳለው "ለተከሳሾች እና ለሰፊው ማኅበረሰብ ደኅንነት ሲባል ተከሳሾች ችሎት ፊት መቅረብ አይችሉም" ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የተዘረዘሩ ተከሳሾች ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀጠሮ ነበራቸው።

የእነ አቶ ጃዋር መሐመድን ጉዳይ እየተመለከቱ ያሉት ዳኞች ባለፉት ጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሆነ የምርጫ ቅስቀሳ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰዋል።

"ለተከሳሾች ከፍተኛ ጥበቃ ነው የሚያስፈልገው" በማለት በምርጫ ወቅት ተከሳሾችን ወደ ችሎት ማምጣቱ አስቸጋሪ ነው ብለዋል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 24ቱ ተከሳሾች ከምርጫው በኋላ ፍርድ ቤት ይቅረቡ ሲል ወስኗል።

ዐቃቤ ሕግ ችሎቱ በዝግ ይከናወን እንዲሁም ምስክሮቼ ከመጋረጃ ጀርባ ቃላቸውን ይስጡ በሚል አሻሽሎ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ተከሳሾች ምላሽ እንዲሰጡ ነበር የዛሬው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ የጸረ-ሸብር እና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ቀጠሮ ተይዞ የነበረው።

ምንም እንኳ በችሎቱ ተከሳሾቹ ባይገኙም ሦስት የተከሳሽ ጠበቆች ተገኝተዋል።

ጠበቆቹም ዐቃቤ ሕግ አሻሽሎ ላቀረበው አቤቱታ "ያዘጋጀነው ምላሽ በተከሳሾች እጅ ስለሚገኝ የምንሰጠው ምላሽ የለም" ብለዋል። ምላሻቸውን በቀጣዩ ቀጠሮ ይዘው እንደሚቀርቡ አስረድተዋል።

ፍርድ ቤቱም በአቶ ጃዋር መዝገብ ሥር የተከሰሱ ተከሳሾችን ጉዳይ ለመመልከት ለሰኔ 21/2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ፎቶ : ዘአፍሪካ ሪፖርት
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ ፥ ለሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጥሪ አቀረቡ። በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ አማካኝነት ለአፋር ህዝብ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ታላቁን የሱልጣን አሊ ሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባት ወደ ስራ ተገብቶ የነበረ ቢሆንም በ "ፖለቲካ አሻጥር" ምክንያት ይህ ፕሮጀክት ግንባታው ከሁለት አስርት አመታት በላይ ቆሟል። የግዙፉን ማዕከል ሙሉ ወጪ…
#Update

ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ የአሳይታውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ቃል መግባታቸው ተገልጿል።

በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ አማካኝነት ለአፋር ህዝብ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ታላቁን የሱልጣን አሊ ሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል እና ሌሎች የልማት ስራዎች አስገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ ተገብቶ ነበር።

የሀገራችን እውቅ ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ብዙ ገንዘባቸውን ውጪ ካደረጉ ቡኃላ በፖለቲካ አሻጥር ምክንያት በክልሉ እያካሄዱ ከነበሩት በርካታ የልማት ስራዎች ተገፍተው እንዲወጡ በማድረግ እና የዚህን ፕሮጀክት ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆሙ በመግፋት ግንባታው እና የልማት ስራዎች እንዲቆም ተደርጓል።

ለሁለት አስርት አመታት ግንባታው የቆመው እና እሳቸው ያስጀመሩት ፕሮጀክት ዳግም ተጠናቆ ህዝቡን እና ሃገርን እንዲጠቅም ለማስቻል እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል።

ከጥቂት ቀናት በፊት አሳይታ ከተማ የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አወል አርባ ፥ ጨምሮ የተለያዩ ታላላቅ ኡለሞች፣ዱዓቶች እና የክልል መጅሊስ አመራሮች የተካፈሉበት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሂዶ ነበር።

በፕሮግራሙ ላይ አቶ አወል አርባ ፕሮጀክቱን ላስጀመሩት እና ከክልሉ በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ለተደረጉት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ በይፋ ወደ ክልሉ ተመልሰው ለህዝባቸው ማድረግ የሚፈልጉትን የልማት ስራዎች ሁሉ ይሰሩ ዘንድ ሁኔታዎችን በሙሉ እንደሚያስተካክሉ ቃል በመግባት ጥሪ አድርገውላቸዋል።

ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ፥ የቀረበላቸው ጥሪ በመቀበል ፕሮጀክቱን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ ቃል መግባታቸውን ተወካያቸው ዛሬ አሳውቀዋል።

ይህን መረጃ የተገኘው ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ካጋሩት ፅሁፍ ላይ ነው።

@tikvahethiopia